- ሀሜተኛ ነው ከዳተኛ
- ሀሜተኛ ያፍራል ሀስተኛ ይረታል
- ሀሜት አይቀር ከድሀም ቤት
- ሀሜትና ጅራት በስተኋላ ነው
- ሀምሌ ቢያባራ በጋ ይመስላል
- ሀምሌና ሙሽራ ሳይገለጡ ነው
- ሀምሌን በብጣሪ ነሀሴን በእንጥርጣሪ
- ሀምሳ ሎሚ ለሀምሳ ሰው ጌጡ ለአንድ ሰው ሸክሙ
- ሀረጉን ሲስቡት ዛፉ ይወዛወዛል
- ሀረጉን ሳብ ዛፉ እንዲሳሳብ
- ሀረግ ለመዳፍ አልጋ ለምንጣፍ
- ሀሰተኛ ምስክር ጉልበት ይሰብር
- ሀሰተኛን ሲረቱ በወንድም በእህቱ
- ሀሰተኛ ሲናገር ይታወቃል ስሱ ሲበላ ይታነቃል
- ሀሰተኛ ሲናገር ይታወቃል በሶ ሲበሉት ያንቃል
- ሀሰተኛ በቃሉ ስደተኛ በቅሉ
- ሀሰተኛ ብርቱ ወንጀለኛ
- ሀሰተኛ ያወራውን ፈረሰኛ አይመልሰውም
- ሀሰት ስለበዛ እውነት ሆነ ዋዛ
- ሀሰት ቢናገሩ ውቃቢ ይርቃል
- ሀሰትና ስንቅ እያደረ ያልቅ
- ሀሰት አያቀላ እውነት አያደላ
- ሀሰት አያድንም መራቆት መልክ አያሳምርም
- ሀስት እያደር ይቀላል እውነት እያደር ይበራል
- ሀስት እያደር ይቀላል እውነትና ውሀ እያደር ይጠራል
- ሀሰት ነገር ክፉ ገሀነም እሳት ትርፉ
- ሀሳቡ ጥልቅ ነገሩ ጥብቅ
- ሀሳብህን ጨርቅ ያድርገው
- ሀሳብና መንገድ ማለቂያ የለውም
- ሀሳብ ከውለታ አይቆጠርም
- ሀሳብ ከፊት አይፈታ ሙት አይመታ
- ሀሳብ ያገናኛል ፍራት ያሸኛኛል
- ሀሳብ ያገናኛል ፍርሀት ያሸኛኛል
- ሀ ሳይሉ ጥፈት ውል ሳይዙ ሙግት
- ሀ ባሉ ተዝካር በሉ
- ሀ ባሉ ደሞዝ በሉ
- ሀብታም ለሀብታም ይጠቃቀሱ ድሀ ለድሀ ይለቃቀሱ
- ሀብታም ለሰጠ የድሀ ሙርጥ አበጠ
- ሀብታም ለሰጠ የድሀ ሙርጥ ያብጣል
- ሀብታም ለሰጠ ደሀ ምንጭሩ አበጠ
- ሀብታም ለሰጠው ደሀ ይንቀጠቀጣል
- ሀብታም ሊሰጥ የደሀ ቂጥ ያብጥ
- ሀብታም ሊሰጥ የደሀው ሙርጥ ያብጣል
- ሀብታም ሊሰጥ ደሀ ምርጥ ያወጣል
- ሀብታም ሲወድቅ ከሰገነት ድሀ ሲወድቅ ከመሬት
- ሀብታም በመመጽወቱ ድሀ በጸሎቱ
- ሀብታም በከብቱ ድሀ በጉልበቱ
- ሀብታም በወርቁ ድሀ በጨርቁ
- ሀብታም በገንዘቡ ድሀ በጥበቡ እርስ በርስ ይቃረቡ
- ሀብታም በገንዘቡ ይኮራል ድሀ በጥበቡ ይከብራል
- ሀብታም ቢሰጥ አበደረ እንጂ አልሰጠም
- ሀብታም ቢያብር ድህነትን ያጠፋል
- ሀብታም ነው መባል ያኮራል ድሀ ነው መባል ያሳፍራል
- ሀብታም እንደሚበላለት ድሀ እንደሚከናወንለት
- ሀብታም ያለ ድሀ አይኮራም ድሀ ያለ ሀብታም አይበላም
- ሀብታም ገንዘቡን ያስባል ድሀ ቀኑን ይቆጥራል
- ሀብት እና እውቀት አይገኝ (ም ) አንድነት
- ሀብት የጠዋት ጤዛ ነው
- ሀኪም ሲበዛ በሽተኛው ይሞታል
- ሀኪም የያዘው ነፍስ ባያድር ይውላል
- ሀኪሞች እስኪመካከሩ በሽተኛው ይሞታል
- ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ
- ሀዘንና ደስታ ጎን ለጎን ናቸው
- ሀዘንን የፈራ በደስታ የተጣራ
- ሀይለኛ ውሀ አሻቅቦ ይፈሳል
- ሀይለኛ ዱቄት ከነፋስ ይጣላል
- ሀይማኖቱ ከጅማት ጉልበቱ ከብረት የጠና
- ሀይማኖት ከግብር ጸሎት ከፍቅር
- ሀይማኖት ያለ ፍቅር ጸሎት ያለ ግብር
- ሀይማኖት የሌለው ሰው ልጓም የሌለው ፈረስ ነው
- ሀጢአት ለሰሪው ምህረት ለአክባሪው
- ሀጢአት ሲደጋገም ጽድቅ ይመስላል
- ሀጢአት ሳያበዙ በጊዜ ይጓዙ
- ሀጢአት በንስሀ በደል በካሳ
- ሀጢአት በንስሀ እድፍ በውሀ
- ሀፍረት ያከሳል ያመነምናል
- ሁለተኛ ደሞ ለዘበኛ ! አሉ
- ሁለተኛ ግፌ ጫንቃዬን ተገርፌ ልብሴን መገፈፌ
- ሁለተኛ ግፍ ልብሴን ይገፍ ጀርባዬን ይገርፍ
- ሁለተኛ ጥፋት ቆሞ ማንቀላፋት
- ሁለተኛ ጥፋት ከገበያ ማንቀላፋት
- ሁለተኛ ጥፋት ከገበያ ቆሞ ማንቀላፋት
- ሁለቱን የተመኘ አንዱንም አላገኝ
- ሁለቱን የተመኘ አንድም አላገኘ
- ሁለቱን ወንበዴ በአንድ ዘዴ
- ሁለቴ ሰላምታ አንዱ ለነገር ነው
- ሁለት ሆነው የተናገሩት በመሬት የቀበሩት
- ሁለት ሞት መጣ ቢለው አንዱን ግባ በለው አለ
- ሁለት ሞግዚት ያለው ህጻን ያለጥርጥር በእሳት ይቃጠላል
- ሁለት ቁና ሰጥቼ አንድ ጥንቅል
- ሁለት ባላ ትከል አንዱ ሲስበር ባንዱ ተንጠልጠል
- ሁለት ባላ ትከል አንዱ ሲነቀል ካንዱ ተንጠልጠል
- ሁለት ብልጥ ኑግ አያደቅ
- ሁለት አይወዱም ከመነኮሱ አይወልዱም
- ሁለት አይወዱ ከመነኩሴ አይወልዱ
- ሁለት አይወዱ ከመነኮሱ አይወልዱ
- ሁለት አገር አራሽ ለባልንጀራው አውራሽ
- ሁለት እግር አለኝ ብሎ ሁለት ዛፍ አይወጡም
- ሁለት እግር አለኝ ብሎ እሁለት ዛፍ አይወጣም
- ሁለት እግር አለኝ ተብሎ ሁለት ዛፍ አይወጣም
- ሁለት አፎች ባይናከሱ ይናቀሱ
- ሁለት ወፎች ባይናከሱ ይናቀሱ
- ሁለት የተመኘ አንድም አላገኘ
- ሁለት የወደደ አንዱን ሳያገኝ ሄደ
- ሁለት ጉድጓድ ያላት አይጥ አትሞትም
- ሁለት ጊዜ ተናገርህ ከፋህ
- ሁለት ጊዜ በላህ ተፋህ
- ሁለት ጊዜ ተናግረህ ከፋህ
- ሁለት ጊዜ በላህ ተፋህ
- ሁለት ጊዜ ነው የዶሮ ልደት አንዱ በእንቁላል አንዱ በጫጩት
- ሁለት ጊዜ ይፈርዱ ጉድ ይወልዱ
- ሁለት ጥፉ ካገር ይጥፉ
- ሁሉ ሄዶ ተበተነ እህና እኔ ቀረነ አለ እያዘነ
- ሁሉ ሄደ ተበተነ እህና እኔ ቀረነ አለ ያዘነ
- ሁሉ ሆነ ቃልቻ ማን ይሸከም ስልቻ
- ሁሉም ሰው መምሰሉ ባይታይ አመሉ
- ሁሉም ሸክሙን ፍቅርም ያዥውን
- ሁሉም በየዘመድህ ቢሉት አክንባሎ ጋጥ ገባ
- ሁሉም አካል ነው ግን እንደአይን አይሆንም
- ሁሉም ከኋላው ያገኘዋል እንደስራው
- ሁሉም ከልኩ አያልፍም
- ሁሉም ወንፈሉን ፈታይም ድውሩን
- ሁሉም ያልፋል እውነት ብቻ ይተርፋል
- ሁሉ በእጄ ሁሉ በደጄ
- ሁሉ ቢናገር ማን ይሰማል
- ሁሉ አማረኝን ገበያ አታውጣት
- ሁሉ አረሰ ማን ይሸምት
- ሁሉ የሚገኝ ከእሱ የሚገኝ የለም ያለእርሱ
- ሁሉን ለእኔ አትበል
- ሁሉን ቢናገሩት ሆድ ባዶ ይቀራል
- ሁሉን አውቆ አሳውን እሾህ ከስጋው ለይቶ
- ሁሉ ያልፋል እስኪያልፍ ያለፋል
- ሁሉም ያልፋል ግን እስኪያልፍ ያለፋል
- ሁሉ ያልፋል እውነት ብቻ ይተርፋል
- ሁሉም በየዘርህ ቢሉት አከንባሎ ጋጣ ገባ
- ሁሉም ያልፋል የሚኮርጅም ቢሆን
- ሁሉ አማረሽን ዲስኮ (disco) አታውጧት
- ሁሉ አማረሽን ገበያ አታውጧት
- ሁል ጊዜ ባሬራ ትበያለሽ ወይ አንዳንድ ጊዜ እንኳ ወጥ አትይሞይ
- ሁል ጊዜ ከመደንገጥ አንድ ጊዜ መሸጥ
- ሂዳ ጉበት ቢነሷት ታናሽ ታላቅ ስደዱልኝ አለች
- ሂዳ ጉበት የነሷት ታናሽ ታላቅ ስደዱልኝ አለች
- ሂዳ ጉበት ይነሷታል ታናሽ ታላቅ ላኩልኝ አለች
- ሂድ አትበለው እንዲሄድ አድርገው
- ሂድ አትበለው እንደሚሄድ አርገው
- ሂድ ካገር ኑር ካገር
- ህልም ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም
- ህልም አለ ተብሎ ሳይተኛ አይታደርም
- ህመሙ ቀርቶ ሞቱን በሰጠኝ
- ህመሙ ቀርቶ ሞቱን በተወኝ
- ህመሙን የሸሸገ መድሀኒት የለውም
- ህመሙን የደበቀ መድሀኒቱም አልታወቀ
- ህመሙን የደበቀ መድሀኒት የለውም
- ህዳር መማረሪያ ሰኔ መቃጠሪያ
- ህያዋን ለነገስታት ሙታን ለካህናት ይገብራሉ
- ህግ ይኖራል ተተክሎ ስርአት ይኖራል ተዛውሮ
- ሆሆሆ ስቄ ልሙት አለ ሰውየው
- ሆቴል ቢያብር ገንዘብ ያስገኛል
- ሆደ ሰፊ ነገር አሳላፊ
- ሆደ ሰፊ ይሻላል ከአኩራፊ
- ሆዱ ሲሞላ ፍቅሩ ሌላ
- ሆዱ ሲጎድል ሰው ያጋድል
- ሆዱ ናረት ሙያው ከጅረት
- ሆዱን የወደደ ማእረጉን የጠላ
- ሆዱን የወደደ ማእረጉን ይጠላል
- ሆዱን ያለ ሆዱን ተወጋ
- ሆዱ ወድዶ አፉ ክዶ ክፉ ለምዶ
- ሆዱ ፈሪ እግሩ ዳተኛ አዳም ሲዋጋ እርሱ ይተኛ
- ሆዳም ሰው እንብርት የለውም
- ሆዳም ቢሸከም የበላ ይመስለዋል
- ሆዳም ቢፈተፍት የጠገበ ይመስለዋል
- ሆዳም ፍቅር አያውቅም
- ሆዴ በጀርባዬ ቢሆን ገፍቶ ገደል በጣለኝ
- ሆዴ ኑር በዘዴ
- ሆዴን በልቶኝ ጎኔን ቢያኩኝ አይገባኝ
- ሆዴ አታጣላኝ ከዘመዴ
- ሆድህና ልጅህ አይጥሉህ
- ሆድህን ጎመን ሙላው ጀርባህን ለጠላት አታሳየው
- ሆዴ ሆዴ የሚለውን ጌታ ያየዋል አይኔ አይኔ የሚለውን ሰው ያየዋል
- ሆድ ሆዴን የምትል ወፍ አለች ምናለች
- ሆድ ለማታ በልቶ ለጠዋት
- ሆድ ለባሰው ማጭድ አታውሰው
- ሆድ ለባሰው ቢላዋ አታውሰው
- ሆድ ለተተባሰው ማጭድ አታውሰው
- ሆድ ሲሞላ ራስ ባዶ ይቀራል
- ሆድ ሲያር ጥርስ ይስቃል
- ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ማታ
- ሆድ ሲያውቅ ዶሮ ጠዋት
- ሆድ ባዶን ይጠላል
- ሆድ ባዶ ይጠላል
- ሆድ ከሁዳድ ይስፋል
- ሆድ ካገር ይስፋል
- ሆድ እንዳሳዩት ነው
- ሆድና ግንባር አይሸሸጉም
- ሆድና ግንባር አይሸሸግም
- ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት ዳገት ላይ ይለግማል
- ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል
- ሆድን በጎመን ቢደልሉት ጉልበት በዳገት ይለግማል
- ሆድ ወዶ አፍ ክዶ ክፉ ለምዶ
- ሆድ ዘመድ ሳይወድ አፍ እህል ሳይለምድ
- ሆድ የኔ ነው ሲሉት ቁርጠት ሆኖ ይገድላል
- ሆድ የሸሸገውን ብቅል ያወጣዋል
- ሆድ ያበላውን ያመሰገናል
- ሆድ ያባውን ብቅል ያወጣዋል
ለ
- ለሀምሳ ጋን አንድ አሎሎ ይበቃል
- ለሀብት መትጋት ሰውነትን ያከሳል ገንዘብን ማሰብ እንቅልፍ ይነሳል
- ለሀጥአን የወረደ ለጻድቃን ይተርፋል
- ለሁሉም ጊዜ አለው
- ለሂያጅ የለውም ወዳጅ
- ለህልም ምሳሌ የለውም
- ለሆዳም ሰው ማብላት ውቅያኖስን ለመደልደል መቃጣት
- ለሆዳም በሬ ገለባ ያዝለታል
- ለሆዳም በሬ ጭድ ያዝለታል
- ለሆዳም በሬ ቫት ተከፈለ
- ለሆዳም በቅሎ ጭድ ያዝለታል
- ለሆዴ ጠግቤ በልብሴ አንግቤ
- ለሆድ ቁርጠት ብላበት ለራስ ምታት ጩህበት
- ለላሙ መንጃ ለሸማው መቅደጃ
- ለላሙ መንጃ ለሸማው መከንጃ
- ለላም ቀንዷ አይከብዳትም
- ለላም ከጥጃዋና ከአላቢዋ ማን ይቀርባታል
- ለላም የሳር ለምለም
- ለላም ጥጃዋ ለአህያ ውርንጭላዋ
- ለሌለው ምን ትለው
- ለሌባ ቅሌት ልብሱ ነው
- ለልደት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ
- ለልጅ ሲሉ ይበሉ ለወዳጅ ሲሉ ይጠሉ
- ለልጅ ሲሉ ይበሉ ለወገን ሲሉ ይጠሉ
- ለልጅ አይስቁለትም ለውሻ አይሮጡለትም
- ለልጅ ከሳቁለት ለውሻ ከሮጡለት
- ለልጅ ጥርስህን ለዝንብ ቁስልህን
- ለልጅ ጨዋታ ለባለጌ ቧልታ
- ለሎሌው ምን ትለው
- ለመሀን እምዬ ለአገልጋይ እትዬ ብርቋ ነው
- ለመሄድና ለመላወስ አዛዥ ራስ
- ለመሄድና ለመመለስ አዛዥ ራስ
- ለመሆኑ ሳይሆን እንዴት ይሆናል ቢሆን
- ለመማር ክፍል መግባት ለመኮረጅ ካሮት መብላት
- ለመማር ክፍል መግባት ለማለፍ ካሮት መብላት
- ለመስማት የፈጠንህ ለመናገርና ለቁጣ የዘገየህ ሁን
- ለመስማት የፈጠንህ ለመናገር የዘገየህ ሁን
- ለመስራት የሚያፍር መብላት አይደፍርም
- ለመስራት ያፈረ ለመብላት ደፈረ
- ለመስጠት አለመቸኮል ከሰጡም ወዲያ አለመጸጸት
- ለመነኩሴ መልካም ሎሌ
- ለመታማት መፍራት
- ለመከራ ያለው መነኩሴ ዳዊቱን ሸጦ አህያ ይገዛል
- ለመከራ የጣፈው ቢነግድ አይተርፈው
- ለሙት የለው መብት
- ለሚመለከት ለሚያየው ሞት ቅርብ ነው
- ለሚስት ያጎርሷል ለተመታ ይክሷል
- ለማረም ማን ብሎት ሲሰራው ግን ግድፈት
- ለማን አለው ፈጣሪ አለው ጠጅ ለሌለው ውሀ አለው
- ለማን ይፈርዱ ለወደዱ አይደለም ለወለዱ
- ለማኝ ቢያብድ ስልቻውን አይጥልም
- ለማኝ አያማርጥም ማር አይኮመጥጥም
- ለማየት የፈለገ አይኑን ይገልጣል
- ለማያቅህ ታጠን ብሎሀል ሀሰን
- ለማያውቅ ፎገራ ዱሩ ነው
- ለማያውቁሽ ታጠኚ
- ለማያውቁሽ ታጥበሽ ቅረቢ
- ለማይሞት መድሀኒት አለው
- ለማይሰጥ ሰው ስጡኝ ማለትን ማን አስተማረው
- ለማይሰጥ ሰው ስጡኝን ማን አስተማረው
- ለማእበል ወደብ ለነፋስ ገደብ የለውም
- ለምሽት መብራት ለመከራ ጊዜ ብልሀት
- ለምክንያት ምክንያት አለው
- ለምን ላለው ፈጣሪ አለው ጠጅ ለሌለው ውሃ አለው
- ለምን ሰርግ ይሄዳል ሰርግ አለ በቤቱ
- ለምን ተክዤ አምላክን ይዤ
- ለምን ያለው ስልቻውን ጫን ያለው ኮርቻውን
- ለምን ያለው ስልቻውን ጫን ያለው ኮርቻውን አያጣም
- ለምን ጊዜው ነቀዝሽ
- ለምኖ ለማኝ ቆቤን ቀማኝ
- ለሞኝ ሰኔ በጋው መስከረም ክረምቱ
- ለሞኝ ንገረው ምን ይሰማ ብዬ ለብልህ ንገረው ምን ይሳተው ብዬ
- ለሞኝ ከሳቁለት ለውሻ ከሮጡለት
- ለሞኝ ጉድጓድ አያሳዩትም ቤት ነው ብሎ ይገባበታል
- ለሞፈር ቆራጭ እርፍ አይታየውም በግላጭ
- ለረዥም ሰው ልብ እና ልብስ ያጥረዋል
- ለረዥም መንገድ አትሩጥበት ለረዥም ነገር አትቸኩልበት
- ለራሱ አያውቅ ነዳይ ቅቤ ለመነ ላዋይ
- ለራሱ አያውቅ ጠንቋይ መድሀኒቱ ላዋይ
- ለራሱ ጥላ ለእግሩ ከለላ
- ለራሱ የማይረባ ለሌላም አይረባ
- ለራሱ የማይረባ ለሰውም አይረባ
- ለራስ ምታት ጩህበት ለሆድ ቁርጠት ብላበት
- ለራሱ አያውቅ ሰው አይጠይቅ
- ለራስ ሲቆርሱ አያሳንሱ
- ለራስ ቢያወሩ ለቅንቅን ይዘሩ
- ለራስ ቢያወሩ ለቅንቅን ይዘሩ አለች ዶሮ
- ለራስ ከበጁ አይታጡ ደጁ
- ለራበው ሰው ቆሎ ለቁልቁለት በቅሎ
- ለራበው ባዶ መሶብ ማቅረብ
- ለራት የማይተርፍ ዳረጎት
- ለርስት ሴቶች ስንኳ ይሞቱበታል
- ለሰማይ ምሰሶ የለው ለባእድ ስር የለው
- ለሰለባ የመጣ ልብስ ቢጥሉለት አይመለስ
- ለሰለባ የመጣ ልብስ ቢጥሉለት አይመለስም
- ለሰበበኛ ቂጥ መረቅ አታብዛበት
- ለሰባቂ ጆሮህን አትስጠው
- ለሰው ልጅ ሲያበሉ ለውሻ ልጅ ያብሉ
- ለሰው ልጅ ከሚያበሉ ለውሻ ልጅ ያብሉ
- ለሰው ልጅ ከማብላት ለውሻ ልጅ ማብላት
- ለሰው ልጅ እውቀት ለጦጣ ብልጠት
- ለሰው ሞት አነሰው
- ለሰው ሞት አነሰው ውሻውንስ ፈሴ መለሰው አለች ቀበሮ
- ለሰው ቢነግሩት ለሰው
- ለሰው ቢናገሩ መልሶ ለሰው ጫር ጫር አድርጌ አፈር ላልብሰው
- ለሰው ብሎ መሞት አምላክነት ያሻል
- ለሰው ብሎ ሲያማ ለኔ ብለህ ስማ
- ለሰው ብትል ትጠፋለህ ለእግዜር ብትል ትለማለህ
- ለሰው እንግዳ ላገሩ ባዳ
- ለሰው እንዴት F አነሰው
- ለሰው ከበሬታው ሰው ለወጥ ማጣፈጫው ጨው
- ለሰው ጠላቱ ይወጣል ከቤቱ
- ለሰው የማይል ሰው ሞትም ሲያንሰው
- ለሰው ብሎ ሲያማ ለእኔ ብለህ ስማ
- ለሴትና ለጉም አይዘነጉም
- ለሰይጣን አትስጠው ስልጣን
- ለእሳት ውሀ ለጸጉር ቡሀ
- ለሴት ልጅ እስከአርባ ቀን ሞቷን ከዚያ ወዲያ ሀብቷን
- ለሴት ምስጢር ማውራት በወንፊት መቅዳት
- ለሴት ምክር አይገባትም
- ለሴትና ለጉም አይዘነጉም
- ለሴት ጠላ ለፈረስ ቆላ
- ለስሟ መጠሪያ ቁና ሰፋች
- ለስሱ ፍትፍት አሳይቶ እበት ያጎርሷል
- ለሸማኔ ማገጃ ስለት ማረጃ
- ለሹመት ካልመከሩለት ለጥርስ ካልነከሩለት
- ለሹመት ካልመከሩለት ለጥርስ ካልከደኑለት
- ለሹመት ያደለው የለማኝ አለቃ ይሆናል
- ለሺ ፍልጥ ማሰሪያው ልጥ
- ለቀላል ምስጢር መንገር በቀዳዳ ጤፍ መቋጠር
- ለቀላል ሰው ምስጢር መንገር በቀዳዳ ጤፍ መቋጠር
- ለቀላል ሰው ምስጢር መንገር በቀዳዳ አቁማዳ ጤፍ መቋጠር
- ለቀማኛ የለውም እጅ ለበቅሎ የለውም ልጅ
- ለቀበጠች አማት ሲሶ በትር አላት
- ለቀባሪው አረዱት
- ለቀን ቀጠሮ ለሴት ወይዘሮ
- ለቀንዳም በሬ ቤት አትከልክለው ቀንዱ ይከልክለው
- ለቀንዳም በሬ ቤት አትከልክለው ቀንዱ ይከለክለዋል
- ለቁንጫ ለምጽ ያወጣል
- ለቁንጫ መላላጫ
- ለቂጡ ጨርቅ የለው ቆንጆ ያባብላል
- ለቅልብልብ አማት ሲሶ በትር አላት
- ለቅሶ ሳለ ከቤት ይሄዳል ጎረቤት
- ለቅናት የለውም ጥናት
- ለቅዘን እግር አንስተውለት ለውሻ ሮጠውለት
- ለቆመ ሰማይ ቅርቡ ነው
- ለቆማጣ አንድ ጣት ብርቁ ናት
- ለበራ ወለባ ለውሻ ገለባ
- ለበጋ ጥጃ ውስ አነሰው ወይ
- ለበግ ደጋ ለምቾት አልጋ
- ለቡናሽ ቁርስ የለሽ ለነገርሽ ለዛ የለሽ
- ለባለጌ ገድሉ ውርደቱ
- ለቤት ሳማ ለውጭ ቄጤማ
- ለቤት ሳንቃ ለሰው አለቃ
- ለቤት ሳንቃ ለነገር ጠበቃ
- ለቤት ባላ ለችግር ነጠላ
- ለብልህ ንገረው ምን ይስተው ብዬ ለሞኝ ንገረው ምን ይገባው ብዬ
- ለብልህ አይነግሩ ለድመት አያበሩ
- ለብልህ አይነግሩ ላንበሳ አይመትሩ
- ለብልህ አይነግሩ ለንጉስ አይመክሩ
- ለብልህ አይነግሩም ለንጉስ አይመክሩም
- ለብልህ አይነግሩ ካልጠየቀ በስተቀር
- ለተማሪ ቆሎ ለወታደር በቅሎ
- ለተሟጋች መዘዘኛ የዳኛ ትእግስተኛ
- ለተረታው ያበደረ እሳት ጨመረ
- ለተራበ ግብር ለተበደለ ነገር
- ለተራበ በግብር ለተበደለ በነገር
- ለተራበ ቂጣ ለተጠማ ዋንጫ
- ለተሸሸገ ምግብ የተሸሸገ ሆድ አይጠፋለትም
- ለተሾመ ይሟገቱለታል ለተሻረ ይመሰክሩበታል
- ለተሾመው ይመሰክሩለታል ለተሻረው ይመሰክሩበታል
- ለተሾመ ይመሰክሩለታል ለተሻረ ይመሰክሩበታል
- ለተቀማጭ ሰማይ ቅርቡ ነው
- ለተባባሰው ማጭድ አታውሰው
- ለተንኮለኛ ሲሉ ይሰበስባሉ ለቅን ይፈርዳሉ
- ለተወገረ የማያዝን እንብርት የለውም
- ለትኋን ልጓም ማጉረስ ላፈኛ ሰው መመለስ
- ለትኋን ልጓም ማጉረስ ላፈኛ ሰው መመለስ አይቻልም
- ለቸኮለ ሰው ዋንጫ አስጨብጠው
- ለችግር የፈጠረው ቢነግድ አይተርፈው
- ለነገረኛ ሰው ጀርባህን ስጠው
- ለነገረኛ ነገር ተውለት ለሆዳም እህል አቅርብለት
- ለኔ ነግ በኔ
- ለንጉስ የማይገዛ ለእግዚአብሄር አይገዛ
- ለንጉስ ያልረዳ ከባህር የማይቀዳ
- ለንጉስ ያልረዳ ከባህር ያልቀዳ
- ለንፉግ ሰው የገበያ መንገድ ይጠበዋል
- ለንፉግ ሰው የገበያ መንገድ ይጠበው
- ለአህያ ማር አይጥማትም
- ለአምላክ ልንገረው ለማያስቀረው
- ለአበባ የለው ገለባ
- ለአቤቱታ የለው ይሉኝታ
- ለአንበሳ አታበድር ካበደርክ አትጠይቅ
- ለአንተ ያለውን እንጀራ ይሻግታል እንጂ ማንም አይበላውም
- ለአኩራፊ ምሳው እራት ይሆነዋል
- ለአይነ ስውር መስተዋት
- ለአይንና ለወዳጅ ጥቂት ይበቃል
- ለአይን የሚከፋ ለአፍንጫ ይከረፋ
- ለአዋጅ ነጋሪት ለጥጥ ልቃቂት
- ለአገሩ እንግዳ ለሰው ባዳ
- ለአፈ ግም አፍንጫ ድፍን ያዝለታል
- ለአፉ ለከት የለውም
- ለአፍታ የለውም ፋታ
- ለአፍ ዳገት የለውም
- ለእሳት እንጨት ካልነሱት አይጠፋም
- ለእሳት እንጨት ካልነፈጉት አይጠፋም
- ለእሳት ውሀ ለጸጉር ቡሀ
- ለእሳት ፍላት ለጮማ ስባት
- ለእበጥ ፍላት ለእንጨት እሳት
- ለእባብ እግር የለው ለሞኝ መላ የለው
- ለእብለት ስር የለው ለእባብ እግር የለው
- ለእብለት ስር የለውም ለእባብ እግር የለውም
- ለእበጥ ፍላት ለእንጨት እሳት
- ለእኔ እናት ምን ደላት ያም አፈር ያም ድንጋይ ጫነባት
- ለእውር ዝማሜ ለመላጣ ጋሜ
- ለእጅ ርቆ ለአይን ጠልቆ
- ለእግሩ የተጠየፈ ለቂጡ አተረፈ
- ለእግር የፈሩት ለቂጥ ይተርፋል
- ለእግዚአብሄር የቀነቀነ ለጽድቅ ለጌታ የቀነቀነ ለወርቅ
- ለእውነት ማማ ለውሸት ጨለማ
- ለከለላ ጥላ ቢርብህ ብላ
- ለከሳሽ የለው መላሽ
- ለካህን ጥምቀት ለገበሬ ግንቦት
- ለክፋት ያደለው አሳዳጊ የበደለው
- ለኮ መሳቢያ ወፍጮ ማላሚያ
- ለወሬ ሞትሁ
- ለወሬ ሞትሁ ለእህል ሰለፍኩ
- ለወሬ ወዳጁ ወሬ ለመነኩሴ ጥሬ
- ለወሬ የለው ፍሬ
- ለወሬ የለው ፍሬ ለአበባ የለው ገለባ
- ለወሬ የቸኮለ እናቱን በመንገድ ይረዳል
- ለወርቅ ያሉት አንገት ላሽክት
- ለወታደር ሰፊ መንደር ለወዲላ መልካም ዱላ
- ለወይዘሮ መልካም ዶሮ
- ለወደላ መልካም ዱላ
- ለወዳጅ የማር ወለላ ለጠላት አሜኬላ
- ለወዳጅና ለአይን ትንሽ ይበቃዋል
- ለወጡም እዘኑለት ከእንጀራውም ጉረሱለት
- ለወጡ ጊዜስ ከደረቁም
- ለወጡም እዘኑለት ከደረቁም ብሉለት
- ለወጥ የሚሻል ቅልውጥ
- ለዋንጫ ቡሽ ለውሀ ጉሽ የለውም
- ለዋስ አፍ የለው ለጉንዳን ደም የለው
- ለውሻ ምሳ የለው ራት ብቻ
- ለውሻ ሞት ፊት አይነጩለትም
- ለውሻዬ ያልሁትን ልጄ ቢበላብኝ አልወድም
- ለውሽማ ሞት ፊት አይነጩለትም
- ለውጡኝ ባይ የሚሻለውን አውቆ
- ለዘመዴ ያዝናል ሆዴ
- ለዚህ ሆዴ ጠላኝ ዘመዴ
- ለዝናም ጌታ ውሀ ነሱ
- ለዝናም ጌታ ውሀ ነሱት
- ለዝንብ ከትላንት ወዲያም ድሮ ነው
- ለይቶ እንደፈፋ አንጓሎ እንዳረፋ
- ለይቶት አባ ንጉሷ
- ለደህና ሰው ዋጋ አነሰው
- ለደህና ሰው ውሸት ለጅብ እሸት
- ለደብተራ መቋሚያና ጭራ
- ለደደብ ማስረዳት ድንጋይ ቅቤ መቀባት
- ለደግ ንጉስ እለት እለት ማልቀስ
- ለዳርቻው ሲሳሱ መካከሉን ተነሱ
- ለዳርቻው ሲሳሱ ከነመሀሉም ተነሱ
- ለዳባ ለባሽ ነገርህን አታበላሽ
- ለዳኛ አመልክት እንዲሆን መሰረት
- ለዳኛ የነገሩት በርጥብ ያቃጠሉት
- ለዳኛ ዳኛ አለው ለአንበሳ ተኩላ አለው
- ለድሀ ማን ሰጠው ውሀ
- ለድህነት የፈጠረው ቢነግድ አይተርፈው
- ለድህነት የፈጠረው ቢነግድ አያተርፍም
- ለድሪ ያሉት አንገት ለአሸንክታብ
- ለድሪ ያሉት አንገት ላሽክት
- ለድካም የጣፈኝ ብነግድ አይተርፈኝ
- ለዶሮ ሲነገሩ ምጥማጥ ይሰማል
- ለጆሮ ጥርስ ለሆዳም ስስ
- ለገላጋይ ደም የለውም
- ለገበሬ መልካም በሬ
- ለገቢህ ተንገብገብ
- ለገና ጨዋታ አይቆጡም ጌታ
- ለገደለ ጎፈሬ ላረጋገጠ ወሬ
- ለገዳም የረዳ አይጎዳ
- ለጉንዳን ደም የለው ለዝንብ ቤት የለው
- ለጉንዳን ደም የለው ለገንዘብ ቤት የለው
- ለጋስ ቢለግስ አበደረ እንጂ አልሰጠም
- ለጋስ ቢለግስ አበደረ እንጂ እንዲያው አልሰጠም
- ለእግዜር የተቀናቀነ ጽድቅ ለንጉስ የተቀናቀነ ወርቅ
- ለጎበዝ ስጠው ሰንጋ ፈረስ
- ለጠላትህ እንደ ዳቦ እስኪገምጥህ አትመቸው
- ለጠቢብ አንድ ቃል ይበቃል
- ለጠጪ ሰው የመጠጥ ወሬ አውራው
- ለጥልና ለዳኛ ያለው ገንዘብ አፋፍ ይቆያል
- ለጥርጣሬ ምንጣሬ
- ለጥቅም ሲታጠቁ ከጎን ይጠንቀቁ
- ለጥቅምት ያልሆነ ቀሚስ ይበጣጠስ
- ለውጠኝ ባይ የሚሻለውን አውቆ
- ለጨለማ ጊዜ መብራት ለመከራ ጊዜ ብልሀት
- ለጨቅጫቃ ሰው ከማበደር ይሻላል በጄ ማደር
- ለጭሰኛ መሬት ለሳር ቤት ክብሪት
- ለጾም ግድፈት ለበአል ሽረት
- ለጾም ግድፈት ለባል ሽረት
- ለፈረስህ አንገት ለጋሻህ እንብርት
- ለፈሪና ለንፉግ እያደር ይቆጨዋል
- ለፈሪ ሜዳ አይነሱም
- ለፈሪ ምድር አይበቃውም
- ለፈሪ ይበቃል ፍርፋሪ
- ለፈሪ ስጠው ፍርፋሪ
- ለፋሲካ የተዳረች ሁል ጊዜ የፋሲካ ይመስላታል
- ለፍቅር ብተኛት ለጠብ አረገዘች
- ለፍቅር የለውም ድውር
- ለፍየል ቆላ ለሙክት ባቄላ
- ለፍየል ህመም በሬ ማረድ
- ለፍየል ስም አውጣ ቢለው ሞት አይደርስ አለው
- ሊበሉዋት ያሰብዋትን አሞራ ይሏታል ጂግራ
- ሊወጋ የመጣ ጌታዬ ቢሉት አይመለስም
- ሊያልፍ ውሀ አደረገኝ ድሀ
- ሊያስቡት አይገድም
- ሊጣላ የመጣ ሰብብ አያጣም
- ላህያ ፈስ አፍንጫ አይዙለትም
- ላህያ ማር አይጥማት
- ላህያ ያልከበደው ለመጫኛ ከበደው
- ላለው ቅንጭብ ያረግዳል
- ላለው ይጨመርለታል
- ላለፈ አይጸጸቱም ለሚመጣው አይበለጡም
- ላለፈው አይጸጸቱም ለሚመጣው አይበለጡም
- ላለፈው ክረምት ቤት አይሰራለትም
- ላለፈው ክረምት ውሀ ማቆር አይቻልም
- ላለፈው ጸሎት ከንቱ ጩኸት
- ላሊበላ ሄደሽ ከህንጻው ብትሰፍሪ አይገኝም ጽድቅ አለ ባህሪ
- ላሊበላ አደራውን አይበላ
- ላሊበላ የቃሉን አይበላ
- ላሊበላን ካላጠገቡት ይጮሀል ሎሌም ካልሰጡት ይከዳል
- ላላየ ልጅ ዳቦ ፍሪዳው
- ላላየው የሚያስገርም ለሰማው የሚያስደንቅ
- ላላዩ ልጅ ዳቦ ፍሪዳው
- ላላወቀው ፎገራ ዱር ነው
- ላመት ልብስ ለእለት ጉርስ
- ላሜ ቦራ የልጆቼን ነገር አደራ
- ላም ሲበዘበዝ ጭራዋን ያዝ
- ላም ቀንዷ አይከብዳትም
- ላም በረቱን የሰው ልጅ አባቱን አይረሳም
- ላም ባልዋለበት ኩበት ለቀማ
- ላም አለኝ በሰማይ ወተትዋንም አላይ
- ላም አለኝ በሰማይ ገመድ እፈልጋለሁ
- ላም እሳት ወለደች እንዳትልሰው ፈጃት እንዳትተወውም ልጅ ሆነባት
- ላም ከወንዝ ልጅ ከቦዝ
- ላንተ መምከር ጥቁር ድንጋይ ላይ ውሀ ማፍሰስ ነው
- ላንቺ ቁምነገርሽ በሶብላ ወጥሽ
- ላንቺ ብርቅሽ በሶቢላ ወጥሽ
- ላያዘልቅ ጸሎት ለቅስፈት
- ላይቀርልኝ እዳ በጊዜ ልሰናዳ
- ሌባ ላመሉ ቅድመ እውቅና አገኘ
- ሌባ ላመሉ ንግድ ይላል
- ሌባ ላመሉ ዳቦ ይልሳል
- ሌባ እናት ልጇን አታምንም
- ሌባን ሌባ ቢሰርቀው እንዴት ይደንቀው
- ልባም ሴት ለባልዋ ዘውድ ናት
- ልብስህን በውሀ ገንዘብህን በድሀ
- ልብ ካላየ አይን አያይም
- ልብ ካላየ አይን አይፈርድም
- ልትደርቅ የደረሰች ምንጭ ጭልጭል ትላለች
- ልትሰራ ሂዳ ተላጭታ መጣች
- ልጅም ከሆነ ይገፋል ድንችም ከሆነ ይጠፋል
- ልጅ ለናቷ ምጥ አስተማረች
- ልጅ ምን ቢሮጥ አባቱን አይቀድምም
- ልጅ ሳለህ አጊጥ ሞል ሳይዘጋ ሸምት
- ልጅ ቢያኮርፍ ቁርሱ እራት ይሆናል
- ልጅና እሳት ባለቤቱ ያጠፋዋል
- ልጅን አሳዳጊ እሳትን ውሀ ያጠፋዋል
- ልጅና ወረቀት የያዘውን አይለቅም
- ልጅና ጦጣ ውሀ ይጠጣ
- ልጅ ያቦካው ለእራት አይሆንም
- ልጅ ይወለዳል ከቦዝ ላም ይገዛል ከወንዝ
- ልጅ ደረሰ ቤት ፈረሰ
- ልግመኛ ባሪያ መጇን ትደብቃለች
- ልግመኛ አጋዥ ብታገኝ መጅ ደበቀች
- ልግመኛን መምከር ውሀ በወንፊት ማኖር
- ልፋት ቢያምርህ መሬት ግዛ ችግር ቢያምርህ ልጅ አብዛ
- ልፋ ያለው ሊስትሮ እግር ስር ይውላል
- ልፋ ያለው ምረጡኝ አለ
- ልፋ ያለው በህልሙ ሲሸከም ያድራል
- ልፋ ያለው አንድ እንጨት ያስራል
- ልፋ ያለው በሬ ቆዳው ለከበሮ
- ልፋ ያለው ቢን ላደንን ይፈልጋል
- ልፋ ያለው አንድ እንጨት ያስራል
- ሎሌ ለስህተት ጌታ ለምህረት
- ሎሌ ሲከብር ጌታውን ይከሳል ሙክት ሲሰባ ሾተሉን ይልሳል
- ሎሌ ያገለገለውን ይቆጥራል ጌታ ያስቀየመውን ያስባል
- ሎሌና አሞሌ ካዘዙት ይውላል
- ሎሚ ካልመጠጡት እምቧይ ነው
- ሎሚ ካልመጠጡት እምቧይ ዳቦ ካልገመጡት ድንጋይ
- ሎሚና ትርንጎ ሞልቶልህ ባገር እንቧይ ታሸታለህ የድሀ ነገር
- ሎሚና ትርንጎ ሞልቶ ባገር እንቧይ ያሸታል አወይ የድሀ ነገር
- ሎሚ ቢያብብ ቢኖርና መልካም ሽታ ቢሰጥ መኮምጠጡን አይተውም
መ
- መሄድ በጋ ነው መቀመጥ ክረምት ነው
- መሄጃ የሌለው መውጫውን ያበስራል
- መልከ ጥፉ በስም ይደግፉ
- መልከ ጥፏ ቆንጆዋን አስናቀች
- መልካም ባል መጥፎ ሴት ይገራል
- መልካም ሴት ለባሏ ዘውድ ናት
- መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይውላል
- መልካም ስም ከመቃብር በላይ ይቆማል
- መልካም አባት ለልጆቹ እጁን ኪሱ ይከታል
- መልካም ባል መጥፎ ሴት ይገራል
- መልኳ ባያምር አመሏ ይመር
- መልክ ታጥቦ አይጠጣ ወይ አይበላ
- መልክ ስጠኝ እንጂ ሙያ ከጎረቤቴ እማራለሁ
- መመራመር ያገባል ከባህር
- መሞት የፈለገ ግልገል ቀበሮ ቤት ሄዶ ይጨፍራል
- መራጭ ይወድቃል ከምራጭ
- መቀመጥ በአልጋ ታላቅ ደጋ
- መቅረቧን ሳታውቅ እጇን ታጠበች
- መብላቷን ሳታውቅ እጇን ታጠበች
- መተው ነገሬን ከተተው
- መቼ መጣሽ ሙሽራ መቸ ቆረጠምሽ ሽንብራ
- መካር የሌለው ንጉስ አለ አንድ አመት አይነግስ
- መንገድ ካገር ልጅ ምክር ከጨዋ ልጅ
- መወለድ ቋንቋ ነው
- ሚስቱ ክፉ ባቄላ እራቱ ብሳና እንጨቱ ሀዘን ነው እቤቱ
- ሚስቱ ደግ ስንዴ እራቱ ወይራ እንጨቱ ደስታ ነው እቤቱ
- ሚስቱን ጠልቶ ካማቱ ልጁን ከሶ ካባቱ
- ሚስቱን ገድሎ አማቱ ቤት ተሽሽገ
- ሚስት ባታብል ባሏን ትወልዳለች
- ሚስት ከፈቷት ባዳ ማሽላ ከተቆረጠ አገዳ
- ሚስትህ አመዳም ጎራዴህ ጎመዳም
- ሚስትህ አረገዘች ወይ ቢለው ማንን ወንድ ብላ አለው
- ሚስትህን ስደድ በሬህን እረድ ይላል የባለጌ ዘመድ
- ሚስትና ዳዊት ከብብት
- ሚስት ፈትቶ ካማት መቀለብ በእንፉቅቅ መሄድ
- ሙቅ ውሀና የሰው ገንዘብ አይጠቅምም
- ሚስጥርህን ለባእድ ለምን አዋየኸው ወንፊት ወሀ ይዞ የት ሲደርስ አየኸው
- ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ
- ማር በበላሁበት በጣፈጠው አፌ ጎመን ጎረስኩበት አይ አለማረፌ
- ማሽላ ሲያር ይስቃል
- ማሽላ እየፈካ ያራል
- ማቅ ይሞቃል ጋቢ ይደምቃል ገቢውን ባለቤት ያውቃል
- ማን ሙሽራ ቢልሽ ትኳያለሽ
- ማን ያውራ የነበረ ማን ያርዳ የቀበረ
- ማን ያውራ የነበረ ማን ይጨፍር የሰከረ
- ማእድ ጠፋና አንድ ላይ በላን
- ማግባቱ ቀርቶብኝ በታጨሁ
- ማጣት ከሰማይ ይርቃል
- ምላጭ ቢያብጥ በምን ይበጡ ውሀ ቢያንቅ በምን ይውጡ
- ምን ያመጣ ድሀ ምን ያገሳ ውሀ
- ምን ቢያርሱ እንደጎመን አይጎርሱ
- ምንም ቢጠም መንገድ ምንም ቢከፋ ዘመድ
- ምን ቢፋቀሩ አብረው አይቀበሩ
- ምከረው ምከረው እንቢ ካለህ መከራ ይምከረው
- ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር
- ሞት ቢዘገይ ሲኦል ስለሞላ ነው
- ሞት ቢዘገይ ነው የምሄደው
- ሞት ቢዘገይ የቀረ ይመስላል
- ሞት የሰጠው ቀባሪ አያሳጣውም
- ሞኝ ሲስቁበት የሳቁለት ይመስለዋል
- ሞኝ እከኩን እያየች ስትስቅበት ወደደችኝ ብሎ ይፈነድቃል
- ሞኝና ወረቀት ሊደራደሩ ነው
- ሞኝና ወረቅት ኢንተርኔትን ናቁ
- ሞኝና ወረቅት የያዘውን አይለቅም
- ሞኝ ውሀ ሲወስደው ይስቃል
- ሞኝ ዘመድ ከልጅህ እኩል አድርገኝ ይላል
ረ
ሰ
- ሰለሞን ሳባን ውሀ ባያስጠማት ኖሮ የሱ ጥም ባልበረደ ነበር
- ሰውን ፈላጊ በምርጫ ይሽነፋል
- ሰማይ አትረስ ንጉስ አትክሰስ
- ሰርገኛ መጣ በርበሬ ቀንጥሱ
- ሰባት አመት ባይማሩ ሰባ አመት ይደንቁሩ
- ሰነፍ ሴት ያገባ በሬው በሰኔ ገደል የገባ
- ሰነፍ በዓል ያበዛል
- ሰነፍ ቢመክሩት ውሀ ቢወቅጡት
- ሰነፍ ገበሬ በሰኔ ይሞታል
- ሰነፍ ገበሬ ክረምት በጋው በጋው ክረምቱ
- ሰኔ መቃጠሪያ ህዳር መገናኛ
- ሰኔ ሰላሳ የለውም ካሳ
- ሰኔና ሰኞ
- ሰኔን በዘራዘር ሃምሌን በጎመን ዘር
- ሰካራም ቤት አይሰራም
- ሰካራም ዋስ አያጣም
- ሰው መሳይ በሸንጎ
- ሰው በዋለበት ውሀ በወረደበት
- ሰው ቢማር ቄስ እንጂ መላክ አይሆንም
- ሰው ባለው ይሰለፋል
- ሰውን ማመን ቀብድ ተቀብሎ ነው
- ሰውን ሰው ናቀው የራሱን ሳያውቀው
- ሰውን ሰው ያሰኘው እቁብ ነው
- ሰውን ሲወዱ ከነንፍጡ እና ልጋጉ
- ሰውን ሲያማ ለእኔ ብለህ ስማ
- ሰው አለብልሀቱ ገደል መግባቱ አለጉልበቱ ውሀ መግባቱ
- ሰው አለወንዙ ብዙ ነው መዘዙ
- ሰው እንደ እውቀቱ ነው
- ሰው ከሞተ የለ ንስሀ ከፈሰሰ አይታፈስ ውሀ
- ሰውየው ውሀ ሲወስደው እኔም ወደ ቆላ እወርዳለሁ ብዬ ነበር አለ
- ሰው ያመነ ውሀ የዘገነ
- ሰው ያስገድላል አባይ ውሀ ያስጮሀል ድንጋይ
- ሰው ያለስራው የተሰረቀ አህያ ይነዳል
- ሰው ጥራ ቢሉት መራራን ጠራት
- ሰው ጥራ ቢሉት እራሱ መጣ
- ሰዶ ማሳደድ ቢሻህ ዶሮህን ለቆቅ ለውጥ
- ሰዶ ማሳደድ ካማረህ ዶሮህን በቆቅ ለውጥ
- ሲሉ ስምታ ዶሮ ሞተች ዋና ገብታ
- ሲመክሩት ያልሰማ ሲያጮሉት ይሰማ
- ሲመች ያማት ተዝካር ይወጣል ሳይመች ያባት ይቀራል
- ሲሞቱ ብታይ አንቀላፋች
- ሲሮጡ የታጠቁት ሲሮጡ ይፈታል
- ሲሮጡ የፈቱት ሲቀመጡ ለማስተካከል ቀላል ነው
- ሲሮጥ የመጣን አህያ አጥብቀህ ጫነው
- ሲሰርቀኝ ያየሁትን ቢጨምርልኝ አላምነውም
- ሲስሟት ትታ ሲስቧት
- ሲስሟት እንቢ ብላ ሲጎትቷት
- ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል
- ሲበሉ አድርሰኝ ሲጣሉ አርቀኝ
- ሲበሉ አድርሱኝ ሲጣሉ መልሱኝ
- ሲቃ የቀስቀስው ነቅቶ አይተኛም
- ሲታጠቡ እስከ ክንድ ሲታረቁ ከሆድ
- ሲቸኩሉ የታጠቁት ለወሲብ አይመችም
- ሲቸግር ጤፍ ብድር
- ሲያውቀኝ ናቀኝ
- ሲያዩት ያላማረ ሲበሉት ያቅራል
- ሲያደርጉ አይታ ዶሮም ጡት መያዣ ገዛች
- ሲጠሩት ወዴት ሲልኩት አቤት
- ሲጠባ ያደገ ጥጃ ቢይዙት ያጓራል
- ሲገደገድ ያልበጀው ሲወቀር እሳት ፈጀው
- ሳል ይዞ ስርቆት ቂም ይዞ ጸሎት
- ሳትወልድ ብላ
- ሳያሽ የበላ ዝንጀሮ ሲስል ያድራል
- ሳያውቁ የቆረጡት አበባ የፈለጉት ቀን ይደርቃል
- ሳያጣሩ ወሬ ሳይገሉ ጎፈሬ
- ሳይርቅ በቅርቡ ሳይደርቅ በቅርቡ
- ሳይሰሙ ወሬ ሳይገሉ ጎፈሬ
- ሳይቃጠል በቅጠል
- ሳይተርፋት አበድራ ሳትቀበል ሞተች
- ሳይቸግር ጤፍ ብድር
- ሳይቸግር ጤፍ ብድር መከበር በከንፈር
- ሳይቸግር ጤፍ ብድር በስተርጅና ሙሽርና
- ሳይከካ ተቦካ
- ሳይደግስ አይጣላም
- ሳይጠሩት አቤት የሰይጣን ጎረቤት
- ሳይጠሩት ወይ ባይ ሳይሰጡት ተቀባይ
- ሴቱ ሲበዛ ጎመን ጠነዛ
- ሴትና ዶሮ ዱር ከሄዱ ቤታቸውን ይክዳሉ
- ሴት ከወንድ እህል ከሆድ
- ሴት ለቤት ወፍጮ ለዱቄት
- ሴትና መሬት የማይችሉት የለም
- ሴት ማገዶ ሲቸግራት ምሰሶ ትነቅላለች
- ሴት ሲበዛ ልማት ይፋጠናል
- ሴት ሲበዛ ወንዶች ይፈራሉ
- ሴት በማጀት ወንድ በችሎት
- ሴት በጳጳስ ኳደሬ በንጉስ
- ሴት ብታውቅ በወንድ ያልቅ
- ሴት ሲያፏጩላት ያረሱላት ይመስላታል
- ሴት ታውቅ በወንድ ያልቅ
- ሴት አማት የመረዘው ኮሶ ያነዘዘው
- ሴት አግብተው ሴት ቢወልዱ የት አለ ንግዱ
- ሴት ከወንድ እህል ከሆድ
- ሴት ከጠላች በቅሎ ከበላች አመል አወጣች
- ሴት ካላበለች ባልዋን ትወልዳለች
- ሴት ካልወለደች ቋንጣ አትጠብስም
- ሴት ካልዋሸች ባልዋን ትወዳለች
- ሴትና መሬት የማይችሉት የለም
- ሴት የወደደ ጉም የዘገነ
- ሴት ያመጣው ጠብ አይበርድም
- ሴት ይወዷል ማጀት ያንጎዳጉዷል
- ሴትና ቄስ ቀስ
- ሴትና በቅሎ እንደገሪዋ ነው
- ሴትና አህያ በዱላ
- ሴትና አህያ ዱላ ይወዳል
- ሴትና ድመት ወደ ሞቀበት
- ሴትና ዶሮ ሳይጣላ አይውልም
- ሴትና ድስት ወደ ማጀት
- ሴትና ዶሮ ሳያብድ አይውልም
- ሴትና ፈረስ እንደኩሬ ውሀ እያደር ማነስ
- ሴትና ፈረስ የስጡትን ይቀምስ
- ሴትን ያመነ ጉም የዘገነ
- ሴት የላከው ምልክቱን አይረሳም
- ሴት የላከው ሞት አስፈራራው
- ሴት የላከው ሞት አይፈራም
- ሴት የላከው በር አያንኳኳም
- ሴት የላከው አልቃይዳን አይፈራም
- ሴት የላከው ጅብ አይፈራም
- ሴት የላከው ፓርላማ ይገባል
- ሴትየዋ እንደፈራሁት ተቀደደብኝ አለች
- ስለ ጨሰ አይነድም ስለዳመነ አይዘንብም
- ስልቻ ቀልቀሎ ቀልቀሎም ስልቻ
- ስምህ ማነው ላገር አይመች ማን አወጣልህ ጎረቤቶች
- ስምሽ ማነው ሲሏት ቂጤ ትልቅ ነው አለች
- ስምን መላክ ያወጣዋል
- ስም ከመቃብር በላይ ይቆማል
- ስም ያለው ሞኝ ነው
- ስም ይወጣል ከቤት ይሄዳል ጎረቤት
- ስም ይወጣል ከቤት ይከተላል ጎረቤት
- ስራ ለሰሪው ምርጫ ለመራጭ
- ስራ ለሰሪው እሾህ ላጣሪው
- ስራ ከመፍታት ምርጫ መወዳደር
- ስራ ከምፈታ ልጄን ላፋታ
- ስራ ያጣ መለኩሴ አደገኛ ቦዘኔ ተባለ
- ስራ ያጣ መነኩሴ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል
- ስራ ያጣ መነኩሴ "አደገኛ ቦዘኔ" ተብሎ ታሰረ
- ስራ ያጣ መነኩሴ የምርጫ ቅስቀሳ ጀመረ
- ስራ ያጣ ቄስ ቆቡን ቀዶ ይሰፋል
- ስብ ሊያርዱ ጉፋያ ይነዱ
- ስትወልድ የምትበላውን በርግዝናዋ ጨረስችው
- ስትግደረደሪ ጾምሽን እንዳታድሪ
- ስደትና አግዳሚ ሁሉንም እኩል ያረጋል
- ስጋ ቁጠር ቢሉት ጣፊያ አንድ አለ
- ስጋው ያሳማ እንኳን ለበላው ለሰማው ገማ
- ስጋው ያሳማ ከበላው የሰማው ገማ
- ሶስቴ ከመፍሳት አንዴ መቅዘን
ሸ
- ሸማ ለብሶ ስልቻ በቅሎ ጭኖ ለብቻ
- ሸማ ማዋስ ለባላገር በቅሎ ማዋስ ለወታደር
- ሸማ በውሀ ሰው በንስሀ
- ሸማን በውሀ ሰውነትን በንስሀ
- ሸማ በየፈርጁ ይለበሳል
- ሸማና ምስጥ ወደ ውስጥ
- ሸማኔ በመኑ ጠይብ በከሰሉ
- ሸማኔ በድሩ ጠይብ በመንደሩ
- ሸማኔ ድውሩን ባለስልጣን ክብሩን
- ሸማን ጠምዞ ያሰጧል እህልን አላምጦ ይበሏል
- ሸምበቆ በመርዘሙ አይሆንም ምሰሶ
- ሸምበቆ በመርዘሙ ምሰሶ አይሆንም
- ሸርሙጣ ስታረጅ አቃጣሪ ትሆናለች
- ሸርሙጣን የወደደ ልብሱን ጥሎ አበደ
- ሸርሙጣን የወደደ ልብሱን ጥሎ ያበደ
- ሸኚና ጥላ ቤት አይገባም
- ሸኚ ቤት አያደርስም
- ሸኝ ቤት አይገባም
- ሸክላ ቢጥሉት ገለባ
- ሹመት ላወቀው ይከብደዋል ላላወቀው ያሳብደዋል
- ሹመት ሲገኝ ዘመድ አይገድም
- ሹመት ሺህ ሞት
- ሹመት በተርታ ስጋ በገበታ
- ሹመት የለመደ ወንዝ ዳር ይወርዳል
- ሹመትና ቁመት ከልኩ አያልፍም
- ሹመትና ቁመት አይገኝም በምኞት
- ሹም ለመነ አዘዘ
- ሹም ለሹም ያወርሳል ጉም ተራራ ያለብሳል
- ሹም ለሹም ይጎራረሳል ድሀ ለድሀ ይለቃቀሳል
- ሹም መክሰስ ወጀድ ማረስ አይቸግርም
- ሹም ሲቆጣ ማር ይዞ እደጁ ደስ ሲለው ማር ይዞ እደጁ
- ሹም ቢሞት ሀምሳ የሹም ልጅ ቢሞት መቶ ሀምሳ
- ሹም ቢሞት ቀባሪው ሀምሳ የሹም ልጅ ቢሞት መቶ ሀምሳ
- ሹም ያዛል ቄስ ይናዝዛል
- ሹምና ማር እያደር ይከብዳል
- ሹምና የጋማ ከብት በጊዜ ይከተት
- ሹምና ጥጥ እያደር ይከብዳል
- ሹምና ጥጥ እያደር ይከዳል
- ሹሩባ ትሰራ ሄዳ ጠጉሩዋን ተላጭታ መጣች
- ሹክሹክታ የጠብ ወለምታ
- ሺ መት ሺ ሞት
- ሺም ታለበ አንድ ያው በገሌ
- ሺ በመከረ አንድ በወረወረ
- ሺ በመከር አንድ በወረወር
- ሺ አውል ሲሞት ሺህ ይሙት
- ሺ አውል ከሚሞት ሺ ይሙት
- ሺ አውል ኪሞት ሺ ይሙት
- ሺ ይሙቱ ሺ አውል አይሙት
- ሺ ዝንብ መሶብ አይከፍትም
- ሺህ ቢታለብ አንድ በገሌ አለች ድመት
- ሺ ቢታለቡ ከገሌ አላልፍም አለች ድመት
- ሺ ቢያጩሽ አንድ ያገባሽ
- ሺ ያጭሽ አንድ ያገባሽ
- ሻማ ራሱ ነዶ ራሱ ብርሀን ይሰጣል
- ሻሽ ይደምቃል ማቅ ይሞቃል የሚበጀውን ባለቤቱ ያውቃል
- ሻጭ ገዥ ሆኖ ይገምታል
- ሽልም እንደሆን ይገፋል ቂጥም እንደሆን ይጠፋል
- ሽል ከሆነ ይገፋል ቂጣም ከሆነ ይጠፋል
- ሽል እንደሆን ይገፋል ቂጣም እንደሆን ይጠፋል
- ሽመልና ዘንግ ቂልና በግ
- ሽማግሌ ሳለ ምክር አይጠፋም ጎልማሳ ሳለ ላም አይነዳም
- ሽማግሌ በምክሩ አርበኛ በሰናድሩ
- ሽማግሌ ካለበት ነገር አይናቅበት
- ሽማግሌ ካለበት ነገር አይሰረቅ ጎበዝ ካለበት በትር አይነጠቅ
- ሽማግሌ ካልሞተ ስንዴ ካልመረተ
- ሽማግሌ ካልሞተ ስንዴ ካልሸተ
- ሽማግሌ ይገላግላል የተጠቃ አቤት ይላል
- ሽማግሌና ስልቻ ሳይሞሉ አይቆሙም
- ሽማግሌና ጅብ በላላባት ይገባል
- ሽማግሌን ከምክር ከመለየት ከምግብ መለየት
- ሽሮን ሲሸውዷት ፕሮቲን ነሽ አሏት
- ሽሽት ከኡኡታ በፊት
- ሽበት ምን ታረግ መጣህ ቢሉት እኖር ብዬ አለ
- ሽበት እኖር ብዬ መጥቻለሁ አለ
- ሽታና ግማት ላልሰማ ማውራት
- ሽንብራ መኖር በመከራ
- ሽንኩርት አንድም በሉት ገማ ደገሙትም ገማ
- ሽንኩርት የባህሪውን ይሸታል
- ሾላ በድፍን
- ሾተልን ወደ ሰገባህ ቁጣህን ወደ ትእግስት
- ሾተልን ወደ አራዊት ቁጣህን ወደ ትእግስት
- ሾተልን ወደ አፎት ቁጣን ወደ ትእግስት
- ሽሮ ቢደነፋ እንጀራ እስኪቀርብ ነው
ቀ
- ቀለም ሲበጠበጥ ብርእ ሲቀረጥ
- ቀለም በቀንድ ውስጥ ጨለማ ነው ሲፃፍ ግን ብርሃን ነው
- ቀለም ሲበጠበጥ ብርእ ቅረጹልኝ
- ቀለበት ለቆማጣ ሚዶ ለመላጣ
- ቀሊል አማት ሲሶ በትር አላት
- ቀላጅ የሰይጣን ወዳጅ
- ቀላዋጭ ወጥ ያውቃል
- ቀልብ የሌለው ውሻ ጠዲቅ አምጡልኝ ይላል
- ቀልድና ቅዘን ቤት ያጠፋል
- ቀልደኛ አልቅሶ ካልተናገረ የሚያምነው የለም
- ቀልደኛ ገበሬ ሲያስቀን አደረ
- ቀልደኛ ገበሬ ናይት ክለብ ከፈተ
- ቀልደኛ ጎረምሳ እያራ ያፏጫል
- ቀልድና ቅዘን ቤት ያበላሻል
- ቀሙን ላይቀር ከነጫማቸው
- ቀማኛና ሽፍታ ጭለማና ማታ
- ቀርቀሬ ወርጄ ማር ስልስ ማር ልከፍል
- ቀስ በመቀስ አንቁላል በአግሩይሂዳል
- ቀስ እንዳይደፈረስ
- ቀስ እንዳይፈስ
- ቀስ በቀስ እንቁላል በእግሩ ይሄዳል
- ቀስ በቀስ አባይም ዝናብ ይሆናል
- ቀበሮ ናት የገጠሩዋ ሚዳቋ ናት የሰፈሩዋ
- ቀበሮ የበሬ ቆለጥ ይወድቅልኛል ብላ ስትከተል ዋለች
- ቀበቶ ለማፈኛ ሰንሰለት ለማቆራኛ
- ቀበኛ ማሰሪያውን በልቶ ያሳጥራል
- ቀበኛ ከብት ዋጋውን ያደርስ
- ቀባሪ በፈጣሪ
- ቀብረው ሲመለሱ እግዜር ይማርዎ
- ቀብሮ የሚመለስ የሚመለስ አይመስለውም
- ቀኑ የጨለመበት መንገዱ ዘንግ ነው
- ቀና ሲታጣ ይመለመላል ጎባጣ
- ቀና ቢታጣ ይመለመላል ጎባጣ
- ቀናውን ብነግራት ውልግድግዱን አለች
- ቀን ስው መስሎ ማታ ጅራት አብቅሎ
- ቀን ሲከፋ በግ ይነክሳል
- ቀን ሲጥለው ሁሉ ይጠላው
- ቀን ሲገለበጥ ውሀ ወደ ላይ ይፈሳል
- ቀን ሲደርስ አምባ ይፈርስ
- ቀን ሳይቆጥሩ ውሻ ሳይጠሩ ደረሰ በእግሩ
- ቀንበር ታርቆ ጣውንት ታርቆ ምን ይሆናል
- ቀንበር ታንቆ ጣውንት ታርቆ ምን ይሆናል
- ቀን በበቅሎ ማታ በቆሎ
- ቀን በቅሎ ማታ ቆሎ
- ቀን ቢረዝም ልብ ያደክም
- ቀን ቢረዝም ልብ ይደክም
- ቀን ቢቆጥሩ ውሻ ቢጠሩ ደረሰ በእግሩ
- ቀን ቢቆጥሩ ውሻ ቢጠሩ ይደርሳል በእግሩ
- ቀን ባጀብ ሌት በዘብ
- ቀን አይጥለው የቀለም ሰረገላ አያሰናክለው
- ቀን አይጥለው ጠጅ አያስክረው
- ቀን አይጥለው ጠጅ አያሰክረው የለም
- ቀን እስኪወጣ ያባቴ ገበሬ ያግባኝ
- ቀን እስኪያልፍልሽ ያባትሽ ሎሌ ያግባሽ
- ቀን እስኪያልፍ ያለፋል
- ቀን እስኪያልፍ ያባቴ ባሪያ ያግባኝ
- ቀን እስኪያልፍ ያባቴ ባሪያ ይግዛኝ
- ቀን እንደተራዳ ሌት እንደ ግርግዳ
- ቀን ከህዝብ ሌት ከጅብ
- ቀን ከጣለው ሁሉ ይጥለው
- ቀን ካልለቀሙ ሌት አይቅሙ
- ቀን ካለቀሙ ሌት አይቅሙ
- ቀን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል
- ቀን የጎደለበት ጠገራ አይጥ ይበላዋል
- ቀን ይነዳ እንደ ፍሪዳ
- ቀንና ጨርቅ እንደምንም ያልቅ
- ቀንና ጨርቅ ያልቃል ብልህ ያውቃል
- ቀንዳምን በሬ ቀንድ ቀንዱን
- ቀንዱ ሰማይ ጠቀስ ጭራው ምድር አበስ
- ቀንድ ካላት ላም ጎዳ ትከፋለች
- ቀንድና ጅራት ለዋንጫ አለፉ
- ቀንድ እገባበት ጅራት አይቀርም
- ቀንድ ውስጥ ገብቶ ጅራት አይቀርም
- ቀኝም ሰገሩ ግራም ሰገሩ መገናኛው ኮሩ
- ቀድሞ ነበር እንጂ መጥኖ መደቆስ አሁን ምን ያደርጋል ድስት ጥዶ ማልቀስ
- ቀድሞ ነበር እንጂ ተራምዶ ማለፍ አሁን ምን ይሆናል ተይዞ መለፍለፍ
- ቀይ ምላሱ ጥቁር እራሱ
- ቀይ ሰው መልክ አይፈጅም
- ቀይ እንደበርበሬ ጥሩ እንደ ብርሌ
- ቀዳዳ ያፈሳል ግቢ ያፈርሳል
- ቀድሞ ሰኞን አለመሆን ነው
- ቀድሞ የሸተውን ወፍ ይበላዋል ቀድሞ የሚናገረውን ሰው ይጠላዋል
- ቀድሞ የሸተውን ወፍ ይበላዋል ቀድሞ የተናገረውን ሰው ይጠላዋል
- ቀዶ ያለበሰ ቆርሶ ያጎረሰ
- ቀጥኜ ቢያየኝ ጅማት ለመነኝ
- ቀጥኜ ቢያዩኝ ጅማት ለመኑኝ
- ቀጥኜ ቢያዩኝ ሞዴል ነሽ አሉኝ
- ቁልቢጥ የላት ቁና አማራት
- ቁልቢጥ የላት ድርጎ አማራት
- ቁመህ ተከራከር ዙረህ ተመካከር
- ቁመህ ተናገር ዙረህ ተመካከር
- ቁመቷ ቢያጥር እንደ ድምብላል ውዷ ክፉ ነው ይደበልላል
- ቁም እንደአላማ ቁረጥ እንደጫማ
- ቁም እንዳላማ ጥልቅ እንደጫማ
- ቁም ነገረኛ መምሰል የተለመደ አመል
- ቁም ነገር ይዞ ተረት ቂም ይዞ ጸሎት
- ቁራ ሲነጣ አህያ ቀንድ ያወጣ
- ቁራ ስሙን የጠራ
- ቁርበት ምን ያንቋቋሀል ቢሉት ባያድለኝ ነው እንጂ የነጋሪት ወንድም ነበርኩ አለ
- ቁርበት ምን ያንጓጓሀል ቢሉት ባያድለኝ ነው እንጂ የነጋሪት ወንድም ነበርኩ አለ
- ቁርጥማት ቢያብር አልጋ ላይ ያማቅቃል
- ቁርጥ ያጠግባል ተስፋ ያታልላል
- ቁቅም ከፈስ ተቆጠረች
- ቁና ለመስፈሪያ ብርብራ ለማስከሪያ
- ቁንጥጫ ይሻላል ከግልምጫ
- ቁንጫ ለትልቅ ሰው ይበረታል ይባላል
- ቁንጫ መሄድ ሳትማር መዝለል ትማራለች
- ቁንጫ ሞኝ ናት ቀን ትበራለች ተለቃቅማ ታልቃለች
- ቁንጫ ውሀ ወረጅ ቢሏት ስፈናጠር የሰው ዶጮ እሰብር አለች
- ቁጥቋጦም ሲያድግ ዛፍ ይሆናል
- ቁጥቋጦ ሲያድግ ዛፍ ይሆናል
- ቁጥቋጦ ያለዛፍ አይሆንም
- ቁጩና ብስጩ አልማችሁ ፍጩ
- ቁጭትና መረቅ ለጊዜው ይጣፍጣል
- ቁጭትና መጠጥ ለጊዜው ይጣፍጥ
- ቁፍ ቁፍ አሰኘሽ እንደቄብ ዶሮ ለመከራ ላሳርሽ ኖሮ
- ቂል ሲረግሙት የመረቁት ይመስለዋል
- ቂል አይሙት እንዲያጫውት
- ቂልን ለብቻው ስደበው ራሱን ባደባባይ እንዲሰደብ
- ቂልን አንድ ጊዜ ስደበው ሲሰደብ ይኖራል
- ቂልን ድንጋይ ተማትቶ ጌታና ሎሌ ተሟግቶ የማይሆን ነው ከቶ
- ቂል ከጠገበበት አይወጣም
- ቂል ያገኘው ፈሊጥ ውሻ የደፋው ሊጥ
- ቂምህን አትርሳ የወደቀን አንሳ
- ቂም ይዞ ጸሎት ሳል ይዞ ስርቆት
- ቂም ይዞ ጸሎት ጭድ አዝሎ ወዘት
- ቂጡን የተወጋ ውሻ እንደልቡ አይጮህም
- ቂጡ የቆሰለ ውሻ እንደልቡ አይጮህም
- ቂጥ ቢወድል ፈስ አያድን
- ቂጥ ቢያብጥ ልብ አይሆንም
- ቂጥኛም ከውርዴ ይማከራል
- ቂጥኛም ከውርዴ ይውላል
- ቂጥ ገልቦ ክንብንብ
- ቂም ቂም ያሰኘሽ እንደዶሮ ለካስ ለመከራሽ ላሳርሽ ኖሮ
- ቂፍ ቂፍ ያሰኘሽ እንደ ቄብ ዶሮ ለመከራሽ ላሳርሽ ኖሮ
- ቃልህ ሳይዘጋ እግርህ ሳይዘረጋ
- ቄሱም ዝም መጽሀፉም ዝም
- ቄስ ለኑዛዜ ፍቅር ለሚዜ
- ቄስ ምን ይሻል ጠላ ነገር ምን ይሻል ችላ
- ቄስ ኤርክሶን መምህሩ እናት አያስቀብሩ
- ቄስ እበር አረመኔ ከማህበር
- ቄስ ካናዘዘው እድሜ ያናዘዘው
- ቄስ ካፈረሰ ዲያቆን ከረከሰ
- ቄስና ንብ እያዩ እሳት ይገባሉ
- ቄስና ንብ እያየ እሳት ይገባል
- ቄስ ያዘዘህን አድርግ እንጂ ቄስ ያደረገውን አታድርግ
- ቅል ባገሩ ድንጋይ ይሰብራል
- ቅል ባገሩ ደንጊያን ይሰብራል
- ቅልና ድንጋይ ተማትቶ ሎሌና ጌታ ተሟግቶ
- ቅልና ድንጋይ ተማትቶ ሎሌና ጌታ ተሟግቶ የማይሆን ነው ከቶ
- ቅልና ድንጋይ ተማትቶ ጌታና ሎሌ ተሟግቶ የማይሆን ነው ከቶ
- ቅልውጥ አሳስቦ ይጥላል ዘመቻ
- ቅምሙ የበዛበት ወጥ አይፋጅ አይኮመጥጥ
- ቅማል እንኳን ካቅሟ ጥብጣብ ታስፈታለች
- ቅማል ውሀ ውረጅ ቢሏት ስንዳሰስ ለመቼ ልደርስ ቁንጫ ውሀ ውረጅ ቢሏት ስፈናጠር የሰው ዶጮ እሰብር አሉ
- ቅማል በጥፍር ቢድጧት ራስ ደህና አለች
- ቅማል ከአካላት ምስጢር ከቤት
- ቋንጣና ባለሟል ሳያር አይቀርም
- ቅዝምዝም ወዲያ ፍየል ወዲህ
- ቅርብ ያለ ጠበል ልጥ ይነከርበታል
- ቅርናታም ለቅርናታም ሰንቡሌ ሰንቡሌ ይባባላል
- ቅርንጫፉ እንደዛፉ
- ቅቤ መዛኝ ድርቅ ያወራል
- ቅቤ ሲለግም ወስፌ አይበሳውም
- ቅቤ ተነጥሮ ለመብላት ያባት የናት
- ቅቤና ቅልጥም ወዴት ግጥምጥም
- ቅቤ ይፍሰስ ከገንፎ አይተርፍ
- ቅቤ ይፍሰስ ከገንፎ አይለፍ
- ቅብጥና ቅልጥ አንድ ላይ ሲሄዱ ቅልጥ ብላ ቀረች ሶራስ ክመንገዱ
- ቅል በአገሩ ድንጋይ ይሰብራል
- ቅናት ያደርሳል ከሞት
- ቅናት ጥናት አያገናኝ ካባት ከናት
- ቅናት ጥናት አይገኝም ከናት ካባት
- ቅና ያለው በአባቱ ከረባት ይቀናል
- ቅና ያለው በናቱ ብልት ይቀናል
- ቅን በቅን ከማገልገል ፊት ለፊት ማውደልደል
- ቅንቡርስ የት ትሄዳለህ መተማ ትደርሳለህ ልብማ
- ቅንነት ለነፍስ መድሀኒት
- ቅንድብ ለአይን ጥቅሻ አስተማረች
- ቅዝምዝም ሲወረወር ጎንበስ ብለህ አሳልፈው
- ቅዠት ተፈርቶ ሳይተኛ አይታደርም
- ቆላና ደጋ እመቤትና አልጋ
- ቆሎ ለዘር እንዶድ ለድግር አይሆንም
- ቆሎን ቢቆረጥሙት እንጂ ቢያሹት አያልቅም
- ቆመው የሰቀሉትን ቁጭ ብለው ለማውረድ ይቸግራል
- ቆማጣ ቤት አንድ ጣት ብርቅ ናት
- ቆማጣ ብለው ያው ቁምጥና ነው ሌላ ምን ይመጣል አለ
- ቆማጣን ቆማጣ ካላሉት ገብቶ ይፈተፍታል
- ቆሩ መቀበሪያው ያው ፈሩ
- ቆሩ በማን ምድር ትለፋ
- ቆርሶ ያላጎረሱትን ቀዶ ያላለበሱትን ብላቴና ማዘዝ አይገባም
- ቆቅ ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ
- ቆንጆና እሸት አይታለፍም
- ቆዳ ማንጓጓቱን ስሱ መጓጓቱን
- ቆዳ ማንጓጓቱን ስሱ መጓጓቱን አይተውም
- ቆዳ ሲወደድ በሬህን እረድ
- ቆጥሮ የማይሰጥ ሌባ ቆጥሮ የማይቀበል ሌባ
በ
- በሃምሌ ጎመንና አሞሌ
- በሀምሌ ጤፍ ይዘሩ ቤት ይሰሩ
- በለፈለፉ በአፍ ይጠፉ
- በልቶ የማይበርደው የሰው ነገር የማይከብደው ሁለቱ አንድ ነው
- በልጁ ቆዳ ተጠቅልሎ የተቀበረ የለም
- በመስከረም ሊያብድ ያለ ክረምቱ ላይ ጨርቁን ይጥላል
- በሙቅ ውሀ የታጠበ በሰው ገንዘብ የቸረ
- በማን ላይ ቆመሽ እግዜርን ታሚያለሽ
- በሞኝ ክንድ የዘንዶ ጉድጓድ ይለኩበታል
- በራቸውን ክፍት ትተው ሰውን ሌባ ነው ብለው ያማሉ
- በሬ ሆይ በሬ ሆይ ሞኙ በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ እልም ካለው ገደል ወደቅክብን ወይ
- በሬ ቅባቱን በቅልጥሙ ይዞ ይኖራል ለምንህ ቢሉት ኋላ ለገዛ ቁርበቴ ማልፊያ ይሆነኛል አለ
- በሬ ካራጁ ቢላ ተዋሰ
- በሬ ካራጁ ይውላል
- በርበሬን ከላመ ከሞተ አግኝተሽው ዋጥ ስልቅጥ አድርገሽ ከምኔው ጨረሽው
- በሰው ምድር ልጇን ትድር
- በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት
- በሰፈሩት ቁና መሰፈር አይቀርም
- በሴትና በውሀ የማይርስ የለም
- በስራህ ደሀ አትበድል ነጋሪት ባይኖረው እንባ አለው ውሀ ሆኖ ቢኮል ያለ ሞረድ የተሳለ ነው
- በሽታውን የደበቀ መድህኒት አይገኝለትም
- በሽታውን የደበቀ መፍትሄ አያገኝም
- በሽታውን የደበቀ ተፋተሽ
- በሽታውን የደበቀ ቫይረሱ አለበት
- በቅሎ ማሰርያዋን በጠሰች ለራስዋ አሳጠረች
- በቅሎ አባትህ ማነው ቢሉት እናቴ ፈረስ ነች አለ
- በቅሎ ገመድ በበጠሰች በራሷ አሳጠረች
- በቅሎ ግዙ ግዙ አሞሌ ላያግዙ
- በቅርብ ያለ ጠበል ልጥ መንከሪያ ይሆናል
- በቆፈሩት ጉድጓድ መቀበር አይቀርም
- በበጋ እሞኝ ቤት ተንጋጋ በክረምት እቤትህ ተከተት
- በባዶ ቢቆጡ በጨለማ ቢያፈጡ
- በቤቷ ቀጋ በውጪ አልጋ
- በትር ለገና ነገር ለዋና
- በትር ለገና ውሀ ለዋና
- በአህያ ቆዳ የተሰራ ድንኳን ጅብ ሲጮህ ይፈርሳል
- በአንድ ጣት ፊት አይታጠብም
- በአደባባይ ወተት በቤት ውስጥ ጉጠት
- በአጎረስኩኝ ተነከስኩኝ
- በአጎረስኩኝ እጄን ተነከስኩኝ
- በአፉ ቅቤ አይሟሟም
- በአፍ ይበሉበታል እንጂ ክፉ አይናገሩበትም
- በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ
- በእውር ቤት አንድ አይና ብርቅ ነው
- በእውር አገር ጠንባራ ንጉስ ነው
- በእውሮች ከተማ አንድ አይና ንጉስ ነው
- በእጅ ያለ መዳብ እንደወርቅ ይቆጠራል
- በእጅ ያለ ወርቅ እንደ መዳብ ነው
- በእጅ ያለ ወርቅ ከመዳብ ይቆጠራል
- በካፊያ የሚርስ
- በክረምት በርኖስክን አታውል እቤት
- በወተት ላይ ውሀ መጠጣት ያበዛዋል ያነጣዋል
- በውሻ ሆድ ቅቤ አያድርም
- በዘጠና ገዝቶ በዘጠና መሸጥ ትርፉ እንዘጥ እንዘጥ
- በየወንዙ ሀሌ
- በደረቅ አበሳ እርጥብ ይነዳል
- በደንባራ በቅሎ ቃጭል ተጨምሮ
- በጅብ ቆዳ የተሰራ ከበሮ ቅኝቱ እንብላው እንብላው ነው
- በጅብ ቆዳ የተሰራ ከበሮ ሲመቱት እንብላው እንብላው ይላል
- በጋለሞታ ቤት ሁሉ ይጣላበት
- በግ ከበረረ ሞኝ ካመረረ አይመለስም
- በጠራ ተሻገር በተሳለ ምተር
- በጥቅምት አንድ አጥንት
- በጫጩት ፊት ስለ ፈንግል አይወራም
- ቡና እና ማሽላ እየሳቀ ያራል
- ቡዳ በወዳጁ ይጠናል
- ቡዳ ቤት ሰላቢ ገባ
- ቢዋደዱ ጾም ገደፉ ቢጣሉ ተዋረፉ
- ቢደፏት ቂጥ የላት ቢገለብጧት ጡት የላት
- ቢጠሩሽ አትሰሚ ቢጠቅሱሽ አታዪ ረጋ ብለሽ ሂጂ ብር ብር አትበዪ
- ባህታዊ እንደናፈቀ ይሞታል
- ባህያ ማገር የተሰራ ቤት ይበጣጠሳል ጅብ የጮኸ ለት
- ባህያ ቆዳ የተሰራ ቤት ብትንትን ይላል ዥብ የጮኸ ለት
- ባለቤቱን ካልናቁ ሚስኮል አያደርጉ
- ባለቤቱን ካልናቁ አጥሩን አይነቀንቁ
- ባለቤቱን ካልናቁ ውሻውን አይነኩ
- ባለቤቷን ያመነች በግ ላቷን ውጭ ታሳድራለች
- ባለቤቱ ያቀለለውን ባለእዳ አይቀበለውም
- ባለቤት ያቀለለውን አሞሌ ባለእዳ አይሽከመውም
- ባለቤት ካልጮኸ ጎረቤት አይረዳም
- ባለጌን ተነስ አይሉትም
- ባለጌን ከወለደ የገደለ ጸደቀ
- ባለጌ ያለበት ሸንጎ ዝንብ የገባበት አርጎ
- ባለጌ ያለዉ ቻት ሩም እሾህ ያለዉ አሳም ነገሩም ልዋጥህ ቢሉት እሺ አይልም
- ባለጌ የጠገበ እለት ይርበው አይመስለውም
- ባቄላ አለቀ ቢሉ ፈስ ቀለለ
- ባለፈ ክረምት ቤት አይሰራም
- ባሏን እጎዳው ብላ መንታ ልጅ ወለደች
- ባሏን እጎዳው ብላ እንትኗን በእንጨት ወጋች
- ባል ሳይኖር ውሽማ
- ባልሽ ቆላ ወርዶ ሰማይ ሰማይ ሲያዪ አንቺ ከኔ ጋራ ሰበር ሰካ በዪ
- ባልና ሚስት ካንድ ባህር ይቀዳል
- ባልና ሚስት ከአንድ ባህር ይቀዳሉ
- ባልበላው ልበትነው አለች ዶሮ
- ባለጌ ባለሟል ልብስ ገልቤ ልይ ይላል
- ባል ነበር ይቻል ነበር
- ባልና ሚስት ሊተዋወቅ የሰርገኛ ልብ ይውለቅ
- ባልና ሚስት ከአንድ ባህር ይቀዳል
- ባልን ወዶ ምጥን ፈርቶ
- ባርያና ቃርያ ጌታውን እንዳቃጠለ ይኖራል
- ባጎረሰኩ እጄን ተነከስኩ
- ባጎረስሁኝ ጣቴን ተነከስኩኝ ባፍ ይጠፉ በለፈለፉ
- ባልዋን ጎዳሁ ብላ ትምህርት ቤት ገባች
- ባልዘፈንሽ ከዘፈንሽም ባላሳፈርሽ
- ባልዘፈንሽ ከዘፈንሽም ባላፈርሽ
- ባለጌን ካሳደገው የገደለው ይጽድቃል
- ቤተ ሰሪ የተሰረቀ ቦታ አይገዛም
- ብላ ያለው ቀርቦ ተሽከም ያለው ተከማችቶ ይጠብቀዋል
- ብልህ ሚስት ለባሏ አክሊል ናት
- ብልጥ ለብልጥ አይን ብልጥጥ
- ብልጥ ሲለግም አመድ በዱቄት ይለውጣል
- ብርሌ ከነቃ አይሆንም እቃ
- ብርቅና ድንቅ አላንድ ቀን አይደምቅ
- ብርድ ቢያብር ለቁርጥማት ይዳርጋል
- ብቀጥንም ጠጅ ነኝ
- ብቻውን የበላ ብቻውን ይሞታል
- ብዙ ከብት ለማርባት አልቅትን ጠብቆ ውሀ ማጠጣት
- ብድሩን የማይመልስ ልጅ አይወለድ
ተ
- ተሁለት ዛፍ የወደቀ
- ተሁሉም ያው ወንድም ቢከፋም ቢበጅም
- ተለመደና ዶሮ መከሽከሽ እኝህ እናትሽ ሀሙስ ከች
- ተለማማጭ አልማጭ
- ተለማበት የተጋባበት
- ተለጣጭ የጎረቤቷን ድልህ ሟጣጭ
- ተለጣጭ የጎረቤቷን ድልህ አሟጣጭ
- ተላም የዋለ በሬ ተሴት የዋለ ገበሬ
- ተላም የዋለ በሬ ከጋለሞታ የዋለ ገበሬ
- ተሌባ ሌባ ቢሰርቀው ምን ይደንቀው
- ተልባ መስሎሽ ሰናፍጭ ትቀምሽ
- ተልባ በቅባ ኑግ ለሰሚው ግራ ለበይው መልካም ነው
- ተልባ በጥባጭ ሳለች ጎመን ቀንጣሹዋን ምች መታት
- ተልባ በጥባጭ እያለች ጎመን ቀንጣሹዋን ምች መታት
- ተልባ ቢንጫጫ ባንድ ሙቀጫ
- ተመልከት አላማህን ተከተል አለቃህን
- ተመልከኛ ዳኛ መልካም ፈራጅ
- ተመምሩ ደቀመዝሙሩ
- ተመመራመር ይገኛል ነገር
- ተመመራመር ይገኛል ቁምነገር
- ተመሞት ይሻላል መስንበት
- ተመረቅሁ ብለህ ተተረገመ አትዋል
- ተመረቅሁ ብለህ ከተረገመ አትዋል
- ተመርቄያለሁ ብለህ ከተረገመ አትዋል
- ተመሮጥ ማንጋጠጥ
- ተመሮጥ ማንጋጠጥ ይሻላል
- ተመንግስት አመልጣለሁ ለሞት እድናለሁ ማለት ዘበት
- ተመክሮ ልብ ተሸምቶ ድልብ አይሆንም
- ተመዋረድ ጌታን መውደድ
- ተሟጋች - እኔ እረታ ይመስለኛል ሰውም ይመለከተኛል
- ተሙጃ መሀል የወጣች ቄጤማ ወይ ለወፍ ወይ ለባላ
- ተማሪ ዘኬ ለቃሚ
- ተማሪ ውሻ ቀባሪ
- ተማሪና ዶሮ በሞቱ ክብሩ ነው በቁመናው እራቱ ጥሬ ነው
- ተማሪና ዶሮ በሞቱ ክቡር ነው በቁመናው እራቱ ጥሬ ነው
- ተማክረው የፈሱት ፈስ አይገማም
- ተማክሮ የፈሱት ፈስ አይገማም
- ተምሮ የማይጽፍ አክፍሎ የማይገድፍ
- ተምሮ ያላስተማረ ዘርቶ ያላጠረ
- ተሞተች ሚስቴ ምን አለኝ ካማቴ
- ተሞኝ ደጅ ሞፈር ይቆረጣል
- ተረታን እንዳይሉ ይግባኝ ይላሉ
- ተረቴን መልስ አፌን በዳቦ አብስ
- ተረት ለነገር ይሆናል መሰረት
- ተራራ ለጥናት ውሀ ለጥማት
- ተራስ በላይ ንፋስ
- ተራጋሚ ራሱን ደርጋሚ
- ተርጅናና ተሞት ቢሸሹ አያመልጡ
- ተሰብሮ ቢጠገን እንደነበረ አይሆን
- ተሰብሮ ቢጠገን እንደድሮው አይሆን
- ተሰው አለሁ ብዬ ከጅብ ተዳብዬ
- ተሰው አለሁ ብዬ ከጅብ ጋር ተዳብዬ
- ተሰግዳዳ ቦታ ታዳጊ ጌታ
- ተስስታም አንድ ያንቀው አንድ ይወድቀው
- ተስፋ መስጠት እዳ መግባት
- ተስፋ መስጠት እያዩ እዳ መግባት
- ተስፋ ርቆ የተሰቀለ ዳቦ ነው
- ተስፋ ቆርጦ አንድ ላይ ከመቆም ይሻላል በተስፋ ሲጓዙ መክረም
- ተስፋ ያልቆረጠ መነኩሴ ምናኔ ሲሄድ ሴቲቱን ይሰናበታል
- ተስፋ ያድናል ክህደት ያመነምናል
- ተስፋ የተሰቀለ ዳቦ ነው
- ተሸፋፍኖ ቢተኙ ገልጦ የሚወጋ ጌታ አለ
- ተሸፋፍኖ ቢተኙ ገልጦ የሚያይ አምላክ አለ
- ተሹሞ ከመታለል ጥሎ መከብለል
- ተሺ ምስክር የታቦት እግር
- ተሻገር ከወንዙ ጉድ እንዳያበዙ
- ተቀመጥ በወንበሬ ተናገር በከንፈሬ
- ተቀማጭ አፉ ምላጭ
- ተቀማጭ የሌለው ተሟጋች ስልቻ የሌለው ቧጋች
- ተቀማጭ የሌለው ተሟጋች ስልቻ የሌለው አንጋች
- ተቀምጠው የሰቀሉት ቆመው ለማውረድ ያስቸግራል
- ተቀባሪ ወዲያ ማን ያርዳ
- ተቀዳዳ ይሻላል ጨምዳዳ
- ተቁመቱ ማጠር የልቡ መጠጠር
- ተቁመትህ ማጠሩ ሆድህ መጠጠሩ
- ተቁም ዶሮ ከሸክላ ማሰሮ
- ተቂል አትጫወት አይንህን ያወጣል በእንጨት
- ተቅበላ ጥጋብ የስቅለት ጦም ማደር ይሻላል
- ተቆብ ላይ ሚዶ
- ተበድሮ ቅቤ ታርዞ ጎፈሬ
- ተባለ ቀትር አትቀታተር
- ተባቄላ አይጠፋም ዲቃላ ከጠላ አይታጣም አተላ
- ተተሳለ የማይበርድ ተታዘለ የማይወርድ
- ተተናገረ አያባራ አፋቸው ከያዘ አይለቅ ምንቸታቸው
- ተተናገረ አያባራ አፋቸው ከያዘ አይለቅ እጃቸው
- ተተያዙ ብዙ ነው መዘዙ
- ተተያዙ ወዲያ ቄስ ጥሩልኝ ማለት ላያደላድሉ በሺ ብር ጭነት
- ተታመሙ መክሳት ካጡ መንጣት
- ተናት ቀን ይሻላል
- ተናካሽ ውሻ የጅብ መቋደሻ
- ተናካሽ ውሻህን ተዋጊ በሬህን እሰር
- ተናካሽ ውሻ የጅብ መደገሻ
- ተናዞ ይሞቷል አምኖ ይሟገቷል
- ተናገር በከንፈር ተቀመጥ በወንበር
- ተናግሮ አናገረኝ ይወደኝ ይመስል ሄዶ ተናገረ የላክሁት ይመስል
- ተናግሮ አናገረኝ ይወደኝ ይመስል ሄዶ ተናገረ የላኩት ይመስል
- ተናግሮ አናግሮ የሆድን ጨርሶ ጠላት ይሆናል ወዳጅ ተመልሶ
- ተናግሮ ከማሰብ ተከንፈር መሰብሰብ
- ተናግሮ ከማሰብ ከንፈርን መሰብስብ
- ተናግሮ ከመጨነቅ የቀልቀሎዬን አፉን እንቅ
- ተናግሮ ያጣ ሰው ሶስት ጊዜ ሞቱ ነው
- ተንከትክተሽ ስትስቂ የጥርስሽ ወገብ እንዳይቀጭ
- ተንኮለኛ መበለት በጾም ዶሮ በፋሲካ እልበት
- ተንኮለኛ የሰይጣን አርበኛ
- ተንኮለኛ ተሰባብሮ ተኛ
- ተንኮለኛ ናቸው አርቃችሁ ቅበሩዋቸው
- ተንኮለኛ ገደል ዝንጀሮ ይጥላል በሬ ያሳልፋል
- ተንጋሎ ቢተፉ ተመልሶ ካፉ
- ተኚ ብልሽ አትነሺ አልኩሽ(ን)
- ተኛ ወዲያ ጎራሽ እህል አበላሽ
- ተከበሩ ሰው አይፈሩ
- ተከብሮ ያደርጋል ደንቆሮ
- ተከብት እንስት ተሀብት ርስት
- ተከተማ ወደዱር ተአልጋ ወደምድር
- ተከናንቦ የሚበላውን ተጎንብሰህ ግባበት
- ተከፈት ያለው ጉሮሮ ጦም አያድርም
- ተኩላ እንደ አንበሳ እጮህ ብላ ተተረተረች
- ተኩላ ፍየል በላ
- ተኩሶ ጣለ ወጋ ነቀለ
- ተኳሽ በሁለት አይኑ አያነጣጥርም
- ተክፉ ተወልጄ ስፈጭ አደርኩ
- ተክፉ ጎረቤት አይሰሩም ደህና ቤት
- ተኮሰ ጣለ ወጋ ነቀለ
- ተወደዱ ወዲያ ገደሉ ሜዳ
- ተወገብ በላይ ታቦት ከወገብ በታች ጣኦት
- ተወገብ በላይ ጥጋብ ተወገብ በታች ራብ
- ተወጭት አፍ የወንጭት አፋፍ
- ተወጭት አፍ ተወንጭት አፋፍ
- ተወፈሩ ፈጣሪን አይፈሩ ሰውን አያፍሩ
- ተዋርዶ ከማግኘት ኮርቶ ማጣት
- ተዋቅሶ ወዳጅነት የቂም ጠባሳ ባንገት
- ተዋሰኝ ግዝት ይሆነኝ አበድረኝ አይማረኝ
- ተዋጊ በሬ ተጭድ ይጣላል
- ተዋጊ በሬህን ተናካሽ ውሻህን ያዝ
- ተው አትርሳ ተሰርቶልሀል የሳት ገሳ
- ተው ፈረሴን ለጉም አይዘነጉም ለሴትና ለጉም
- ተዝካር ያየ ተማሪ ሸቀጥ ያየ አጣሪ
- ተዝካር ያየ ተማሪ ሸቀጥ ያየ አጣሪ አይን የለውም
- ተይዛ ትዘፍን ጦጣ
- ተይዞ ከመለማመጥ አርፎ መቀመጥ
- ተደርቦ መጣላት ስራ ማጣት
- ተደብቃ ትጸንሳለች ሰው ሰብስባ ትወልዳለች
- ተደብቃ ትጸንሳለች በሰው ስብሳብ ትወልዳለች
- ተድረው ቢመለሱ የውሀ መንገድ ረሱ
- ተድረው ቢመለሱ የውሀን መንገድ ረሱ
- ተዳኛ ተሟግቶ ታዲያማ ተዋግቶ
- ተዳኛ ተሟግቶ ላያደማ ተዋግቶ
- ተጀመሩ መጨረስ ካራገዱ ማልቀስ
- ተጄ በጉንጬ
- ተገናኝተናል መሳ ለመሳ አንቺም እውር ነሽ እኔም አንካሳ
- ተገናኝተው ሳሉ ምን ጊዜ እንገናኝ ይላሉ
- ተገዳዩም ሟቹ ይጣደፋል
- ተጋበዙና ብሉ ሀይ በሉ ከልክሉ
- ተጋፊ ውሀ ሽቅብ ይሄዳል
- ተጋፊ ውሀ አሻቅቦ ይፈሳል
- ተግደርዳሪ ጦም አዳሪ
- ተግደርዳሪ በልቶ ሽሮ ተበዳሪ
- ተግደርዳሪ ቀላዋጭ ቀባጣሪ
- ተጎሽ እበት ተንጨት ሽበት
- ተጎንብሶ የሚበላን ተኝተህ ቀላውጠው
- ተጠማኝ ቢሰነብት ባለርስት ይሆናል
- ተጠንቀቅ ወደል እንዳትገባ ገደል
- ተጥዶ የማይፈላ ተሹሞ የማይበላ
- ተጥዶ የማይፈላ ተሹሞ የማይበላ የለም
- ተጦረኛ ስንቅ አይደባልቁ
- ተጦጣ የዋለ ጉሬዛ እህል ፈጅቶ ገባ
- ተጨንቆ ኩራት ተንጠራርቶ ራት
- ተጫውቶ መማረር አለ ጉዳይ መብረር
- ተፈጣሪ ሙርጥ ጫሪ
- ተፈጣሪ ይበልጣል ቂጥ ጫሪ
- ተፈጥሮን ተመክሮ አይመልሰውም
- ተፈጭቶ ያልተነፋ ዱቄት ተበራይቶ ያልተመረተ ምርት
- ተፈጥሮ ሞት ተሾሞ ሸረት
- ተፈጥሮን ተመክሮ አይመልሰውም
- (ጠያቂ) ታድያስ (መላሽ) አለን በአዲዳስ ያውም ሳንዋስ
- ታጥቦ ጭቃ
- ታላቅ ወንድም እንደ አባት ይቆጠራል
- ታላቅ ጦር ባይወጉበት ያስፈራሩበት
- ታለቀ መቆጠብ ተሞተ መንጠብጠብ
- ታላረፉ መከራ ነው ትርፉ
- ታላቁን ነገር እየተመኘሁ ቢከፍቱት ተልባ ሁኘ ቀረሁ
- ታላወቀ ዘዴ በለው በጎራዴ
- ታልተናገሩ አይከፈት በሩ
- ታልቸኮሉ ቀስ በቀስ ይገኛል ሁሉ
- ታሞ የተነሳ እግዜርን ረሳ
- ታሞ የተነሳ እግዚሄርን ረሳ
- ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ መጠንቀቅ
- ታረጁ ወዲያ ጎፈሬ አዝመራ የሳተው ገበሬ
- ታልጠገቡ አይዘሉ ካልዘለሉ አይሰበሩ
- ታረጁ አይበጁ
- ታሪክን የረሳ ስህተት መድገሙ አይቀርም ይባላል
- ታርቄ ተመርቄ ታጥቤ ተለቃልቄ
- ታርቆ ሙግት በልቶ ስት
- ታሳጭ ማራኪ ይሻላል
- ታሳጭ መካሪ ይሻላል
- ታስሮ ከመማቀቅ ይሻላል መጠንቀቅ
- ታቀበት በረዶ ተቁልቁለት ዘንዶ
- ታባ ቁፍር እሸት ተበልቶለት
- ታባቱ የተረፈ ተጠለፈ
- ታቦተ ክፉ አጸደ መልካም
- ታቦት በራሱ ቃጭል በጥርሱ
- ታከረሩት ይበጠሳል
- ታየው ትመለከተው ትታነቀው ትሞተው
- ታዝበው ኪጠሉህ ታዝበው ይውደዱህ
- ታዝበው ሲጠሉህ ታዝበው ይወደዱህ
- ታዳጊ ያለው በግ ላቱን በውጭ ያሳድራል
- ታጉል ጉልበት እዩልኝ ስሙልኝ ማለት
- ታጉል ጥንቆላ የጨዋ ልጅ መላ
- ታጥቦ ጭቃ
- ታጥቀህ ታገል እንዳትንገላታ አስተውለህ ተሟገት እንዳትረታ
- ትለብሰው የላት ትከናነበው አማራት
- ትላንት ልጄን ዛሬ እናቴን ምን ይበጃል ዘንድሮ አለ አውራ ዶሮ
- ትልቁ አሳ ትንሹን አሳ ይውጣል
- ትልቁ ዳቦ ሊጥ ሆነ
- ትልቅ ብልሀት ለንጉስ መገዛት
- ትልቅ ብልሀት ለትምህርት መትጋት
- ትልቅ ጥቃት ለምኖ ማጣት
- ትልና መጋዝ በሽተኛና ጓዝ
- ትምህርትም እንደ ኮት ፋሽኑ አለፈበት
- ትምህርት በልጅነት አበባ በጥቅምት
- ትምህርትን ለፈጠረ ጥይት በርጫን ላገኘ ገነት
- ትምህርት ከሚሉት ነቀርሳ ኤድስ ከሚሉት በሽታ ያውጣን
- ትምሀርት የማያልቅ ምርት
- ትምህርት የማያልቅ ሀብት
- ትሻልን ትቼ ትብስን አገባሁ
- ትተውት የማይሄዱትን ባልንጀራ አይቀድሙትም
- ትናንሽ ልጆች ትናንሽ ሀብቶች
- ትንሳኤ ትንሳኤ ቢሉኝ ጸሎተ ሀሙስ መሰለኝ
- ትንሽ ምላጭ አገር ትላጭ
- ትንሽ ሰው ትንሽ ነው
- ትንሽ ስጋ እንደ መርፌ ትወጋ
- ትንሽ ሽሮ ባገኝ ጨው የለኝም እንጂ ተበድሬ ወጥ እሰራ ነበር
- ትንሽ ልጅ ከሰራው ሽማግሌ የጎበኘው
- ትንሽ ቆሎ ይዞ ካሻሮ ጠጋ
- ትንሽ ቆሎ ያደርሳል ካሻሮ
- ትንሽ አበላሽ
- ትንሽ ሰው ትንሽ ነው
- ትንሽ ጎልማሳ ትቢያ ታነሳ
- ትንቢት ይመራል ልጓም ይገራል
- ትንኝም ለሆዱ ዝሆንም ለሆዱ ወደ ወንዝ ወረዱ
- ትንኝም ለሆዱ ዝሆንም ለሆዱ ተያይዘው ወደ ወንዝ ወረዱ
- ትንሽ በመናገር እውነት ትከበር
- ትኩስ ሬሳ ደረቁን አስነሳ
- ትንሽ ጭላንጭል ታስይዛለች ምንጭር
- ትእቢትን ከስስት ምን አገናኝቶት
- ትእግስተኛ ከፈለገበት ይደርሳል
- ትእግስት ፍራቻ አይደለም
- ትካዜ ሲመጣ መከፋት ጓዝ ይሆናል
- ትገርም ሻሸመኔ ትብስ ኮፈሌ
- ትጸድቅ ትኮነን ቢለው ቆይ መክሬ አስታውቅሀለሁ አለ
- ትፈጭ የነበረች ማንጓለል አቃታት
- ትፈጭ የነበረች ማንጓለል ተሳናት
- ቶሎ ቶሎ ቢቆጡ አብረው አይቀመጡ
- ቶፋ በማን ምድር ትለፋ
- ቶፋ መቀበሪያው ያው ፈፋ
ቸ
- ቸር ተመኝ ቸር እንድታገኝ
- ቸርን ቢያጠቁት ቢስ ይሆናል
- ቸር ይመጸውታል ጠላት ያጠፋል
- ቸኩለው ያፈሱታል ተቀምጠው ይለቅሙታል
- ቸኩሎ ከተጠቀመ ዝግ ብሎ የተጎዳ ይሻላል
- ቻቻታ የለመደ ሰው አባይ ዳር ቅበሩኝ ይላል
- ችኩል ሰው ጠንቋይ ይጠይቃል
- ችኩል ቅቤ ያንቀዋል
- ችኩል አደንጓሬ ሳይበሉት ሆድ ያማል
- ችኩል አፍ ሞትን ይጠራል
- ችኩል እግር ከዘንዶ ጉድጓድ ይገባል
- ችኮ የጦም ስጋ
- ችግረኛ ሲናገር ውሸት ሲደነፋ እውነት
- ችግር ለወዳጅ ሲያዋዩት ይቀላል
- ችግር በቅቤ ያስበላል አለች ዉሻ
- ችግር ነው ጌትነት
- ችግር የገረፈው ውጤቱ ያማረ ካልተንቀባረረ
ነ
- ነቅናቂ ሳለ ማን ጥሩ ይጠጣል
- ነበረ እንጂ ይኖራል የሚባል ፍጡር የለም
- ነበርንበት አትኩሩበት
- ነቢያት በመደመዱ ሀዋርያት ገደገዱ
- ነቢያት በቀየሱ ሀዋርያት ገሰገሱ
- ነቢይ ቢኖር በከበረ ነበር
- ነቢይ ባገሩ አይከበርም
- ነብር ቢያንቀላፋ ዝንጀሮ ጎበኘው
- ነብር ባየለበት ዘመን ድመት ይበረታል
- ነብር ባየለበት ዘመን ድመት ይኮርታል
- ነብር ሳይገድል ቆዳውን ያስማማል
- ነብር አየኝ በል
- ነብር አይኑን ታመመ ፍየል መሪ ሆነ
- ነብር የሞተ እለት ፍየል ልጅዋን ትድራለች
- ነዋሪ ለዘላለም አለ አምላክ የለም
- ነውር ለባለቤቱ እንግዳ ነው
- ነገረኛ ሰው ከቤቱ አይሞትም
- ነገረኛ ታሞ አይተኛ
- ነገረኛ ናቸው አርቃችሁ ቅበሩዋቸው
- ነገረኛ ናቸው አጥልቃችሁ ቅበሩዋቸው የተነሱ እንደሆን ብዙ ነው ጣጣቸው
- ነገረኛ ዝንጀሮ ውሻ ታረባለች
- ነገሩ ነገር ነው ውስጡ ጥቅንጥቅ ነው
- ነገሩ ነገር ነው ውስጡ ጉራንጉር ነው
- ነገሩ ነው እንጅ ቢላዋ ሰው አይጎዳም
- ነገሩ ነው እንጅ ጩቤ ሰው አይጎዳም
- ነገሬ በሆዴ መንገዴ ባመዴ
- ነገሬ በከንፈሬ
- ነገር ለበለጠ ውድማ ለመለጠ
- ነገር ለበለጥ ውድማ ለመለጥ
- ነገር ለሰሚ ውሀ ለሎሚ
- ነገር ለጀማሪው እሳት ለጫሪው
- ነገር ሲበዛ ይሆናል ዋዛ
- ነገር ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ
- ነገር ሲያመልጥ ራስ ሲመለጥ አይታወቅም
- ነገር ሲያመልጥ እራስ ሲመልጥ አይታወቅም
- ነገር ሲጀመር እህል ሲከመር
- ነገር ሳያውቁ ሙግት ሳይጎለብቱ ትእቢት
- ነገር ሳያውቁ ሙግት አቅም ሳይኖር ትእቢት
- ነገር ስንት ነው ሁለት ምን ያበዛዋል ውሸት
- ነገር በሆዴ መንገድ በአመዴ
- ነገር በሆዴ እየተመኘሁ ቢከፍቱት ተልባ ሆኜ ተገኘሁ
- ነገር በለዛው ጥሬ በለዛዛው
- ነገር በልክ ሙያ በልብ
- ነገር በመልከኛ ጠላ በመክደኛ
- ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ
- ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ መዝሙር በሀሌ
- ነገር በምሳሌ ጠጅ በብርሌ ዜማ በሀሌ
- ነገር በቀጠሮ ዘፈን በከበሮ
- ነገር በትኩሱ ጨዋታ በወዙ
- ነገር በነገር ይጠቀሳል እሾህ በእሾህ ይነቀሳል
- ነገር በእርቅ መንገድ በድርቅ
- ነገር በእርቅ ወይፈንን በድርቅ
- ነገር በወቀሳ በደል በካሳ
- ነገር በዋስ እህል በነፋስ
- ነገር በዋና ሚዶ በእረኛ
- ነገር በዋና ሜዳ በእረና
- ነገር በዋና ዘፈን በገና
- ነገር በዋናው ንብ በአውራው
- ነገር በዳኛ ሚዶ በእረኛ
- ነገር ቢሳሳት ከጥንቱ ሰይፍ ቢመዘዝ ካፎቱ
- ነገር ቢሳሳት ከጠዋቱ ጥጃ ቢሳሳት ከእናቱ
- ነገር ቢበዛ ባህያ አይጫንም
- ነገር ባዋቂ ብረት በጠራቂ
- ነገር አለኝ ከማለት ስራ አለኝ ማለት
- ነገርን አድምጦ እህልን አላምጦ
- ነገር እንደዛፉ ዛፉ እንደቅርንጫፉ
- ነገር ከመጀመሪያው እህል ከመከመሪያው
- ነገር ከመጀመሪያ ፍለጋ ከመሻገሪያ
- ነገር ከመጀመሪያው ውሀ ከመሻገሪያው
- ነገር ከስነበተ ቅራሪ ከሆመጠጠ
- ነገር ካምጩ ውሀ ከምንጩ
- ነገር ከስሩ ውሀ ከጥሩ
- ነገርን ከስሩ ውሀን ከጥሩ
- ነገር ከእብድ ይገኛል
- ነገር ከእጅ ይገኛል
- ነገር ከዋስ ምላስ ከጥርስ
- ነገር ከዋስ ምላስ ከጥርስ አያልፍም
- ነገር ከውሉ ጋሻ ከንግቡ
- ነገር ከግቡ ጋሻ ከእንግቡ
- ነገር ከፊቱ ዱቄት ከወንፊቱ
- ነገር ካንሹ ስጋ ከጠባሹ
- ነገር ካንሺው ስጋ ከጠባሺው
- ነገር ካጀማመሩ እሀ ል ካከማመሩ
- ነገር ወዳድ ሰው ከመንገድ ዳር ቅበሩኝ ይላል
- ነገር ወዳጅ ሰው ከመንገድ ዳር ቅበሩኝ ይላል
- ነገር ወዳጅ ከቤቱ አይሞትም
- ነገር ወዴት ትሄዳለህ ጎንደር መጨረሻህ ታገር
- ነገር ያለዳኛ ትብትብ ያለመጫኛ
- ነገር የሚከረው ጎንጓኙን ሲያገኝ ነው
- ነገር የሻ ዳኛ አምጡ ይላል የዶሮ ሻኛ
- ነገር የዋለበት ዳኛ ያውቃል ከብት የዋለበት እረኛ ያውቃል
- ነገር የፈራ ይቃጠራል አውሬ የፈራ ያጥራል
- ነገር ያለዳኛ ተረት ሰማይ ያለ ደመና ብረት
- ነገር ፈጣሪውን እሾህ አጣሪውን
- ነገር ነገርን ያነሳል ጥጋብ ሞትን ያስረሳል
- ነገርህና ነገሬ ልክ ነው ሰው መስማቱ ትርፍ ነው
- ነገር ነገርን ያመጣል ድግር አፈር(ን) ያወጣል
- ነገርህን በጠጄ ርስትህን በልጄ
- ነገር በነገር ይወቀሳል እሾህ በሾህ ይነቀሳል
- ነገርም ይበረክታል ባለጋራም ይታክታል
- ነገርኩት መስዬ እንዲመስለው ብዬ
- ነገር መጫኛ እንዳሳጠሩት ወይም እንዳስረዘሙት ነው
- ነገርና ገመድ አለውሉ አይፈታም
- ነገርን በእርቅ ወይፈንን በድርቅ
- ነገር እንዲጠፋ ዳኛውን ግደል
- ነገር ነገርን ይወልዳል
- ነጋሪ የሌለው ይታማ አይመስለው
- ነጋዴ ወረቱን ዘላን ከብቱን ገበሬ ምርቱን
- ነጋዴን ተዘማች ምን አቀላቀለው
- ነጻነት ያኮራል ስራ ያስከብራል
- ነጭ ሽንኩርት በመሽተቱ እራሱን ቀብሮ ይኖራል
- ነጭ ድሀ ነጭ ማር ይከፍላል
- ነጭ እንደሸማ ትክል እንደትርሽማ
- ነጭ እንደሸማ ትክል እንደአክርማ
- ነፋስ በተነሳበት ጊዜ እሳት አይጭሩም
- ነፋስ ሲነሳ እሳት አይጫርም
- ነፍጥ ቢያጓራ የጌታውን ጎን ይሰብር
- ነፍጥ ቢያጓር የጌታውን ጎን ይሰብር
- ነፍስ በፈጣሪዋ ሴት ባሳዳሪዋ
- ኑር ባገር ጥፋ ካገር
- ኑሮ በዘዴ አቶ ዘወልዴ
- ኑሮ በዘዴ ጾም በሁዳዴ
- ኑሮ በደጋ መተኛት ባልጋ
- ኑሮ ቢያምርህ ችላ ጥጋብ ቢያምርህ ባቄላ
- ኑሮ ከማናደድ ሄዶ መመስገን
- ኑሮ ከማናደድ ሄዶ መናፈቅ
- ኑሮ ካሉት መቃብር ይሞቃል
- ኑሮ ካሉት የጤፍ ቅጠል ሁለት ሰው ያስተኛል
- ኑሮ ካሉት ፍሪጅ ይሞቃል
- ኑሮ ካሉት ፍሪጅ ይሞቃል አለ የቢራ ጠርሙስ
- ኑ ባይ ከባሪ እንቢ ባይ ቀላይ
- ኑሮ ኑሮ ከመሬት ዙሮ ዙሮ ከቤት
- ኑሮ ኑሮ ከመሬት ዙሮ ዙሮ ከቤት አይቀርም
- ኑሮ ያኗኑራል ህግ ያከባብራል
- ናቂ ወዳቂ
- ና ብላ ሳይሉት ከወጡ አውጡልኝ
- ና ያሉት እንግዳ እራቱ ፍሪዳ
- ናዳ መጣልህ ቢሉት ተከናንቤአለሁ አለ
- ናዳ መጣልህ ቢሉት ተከናንቤአለሁ ልቀቀው አለ
- ንቡን አባሮ ማሩን
- ንብ ላጥር ሳያረዳ አይሄድም
- ንብ ሲሰማራ አጥሩን ተመልከት
- ንብ ቢሄድ ካጥር ሰው ቢሄድ ካገር
- ንብ ቢሄድ ካጥር ሰው ቢሰደድ ካገር
- ንብ ባውራው ገበሬ ባዝመራው
- ንብን አይተህ ተገዛ ብሎዋል እግዜር
- ንካ ያለው አይቀርም
- ንዳማ ቢአጭዱት ክምር አይሞላም
- ንጉሱ በድንኳናቸው እኔ በጎጆዬ
- ንጉሱ በድንኳናቸው እኔ በጎጆዬ ንጉስ ነን አለ ድሀ
- ንገስ ቢሉት ሳልዋጋ አልነግስ አለ
- ንጉስ ለብያኔ አቡን ለኩነኔ
- ንጉስ በመንግስቱ እግዜር በመለኮቱ ጎልማሳ በሚስቱ
- ንጉስ በመንግስቱ ጎልማሳ በሚስቱ አምላክ ባምላክነቱ
- ንጉስ በግንቡ ይታማል
- ንጉስ በግንቡ ገበሬ በርስቱ ቢገቡባቸው ቀናተኞች ናቸው
- ንጉስ ከግንቡ ውጭ ይታማል
- ንጉስ በዘውዱ ድሀ ባመዱ
- ንጉስ ቢቆጣቀስ ብለህ ውጣ
- ንጉስ ሲቆጡ ቀስ ብላችሁ ውጡ
- ንጉሱ ቢሞቱ ከማን ይሟገቱ
- ንጉስ ቢያተርፍ ሁሉ ይተርፍ
- ንጉስ ሲሞት ግንቡን ብልህ ሲሞት ልቡን
- ንጉስ አንጋሹን ቤተክርስቲያን ቀዳሹን
- ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ
- ንጉስ አይከሰስ ሰማይ አይታረስ አባት አይወቀስ
- ንጉሱ ከሾመው ማረሻ የሾመው
- ንጉስ ከተነፈሰ አይን ከፈሰሰ
- ንጉስ ከተነፈሰ ውሀ ከፈሰሰ
- ንጉስ ይተክላል ንጉስ ይነቅላል
- ንጉስ የቆረጠው እጅ ካለ ይቆጠራል
- ንጉስ የፈረደበት መርከብ የተሰበረበት
- ንጉስ የፈረደበት መርከብ የተሰበረበት (አንድ ነው)
- ንጋትን ዶሮ ያውቃል ወፍ ያረጋግጣል
- ንጋትን አውራ ዶሮ ያውቃል ወፍ ያረጋግጣል
- ንጋትና ጥራት እያደር ይታያል
- ንጉስ የሰቀለው አንበሳ የሰበረው
- ንፉግ ለግሶ ቢሰጥ እጁ ይንቀጠቀጥ
- ንጉስ የወደደው ዘመን የወለደው
- ንጉስ ያላቸው ንቦች ማር ይበላሉ ንጉስ የሌላቸው ዝንቦች ጥንብን ይልሳሉ
- ንጉስ ይሞግትልህ ንጉስ አይሞግትህ
- ንግግር ሲበዛ ይጠፋል ማር ሲበዛ ያስተፋል
- ንፍጥ ለባለቤቱ ቅቤ ነው
- ኖረሽ አልጠቀምሽን ሞተሽ አለቀቅሽን
- ኖሮ ኖሮ ከሞት ዞሮ ዞሮ ከቤት
አ
- አህያ የሌለው በቅሎ ይንቃል
- እብድና ዘበናይ የልቡን ይናገራል
- እብድና የዘመኑ ፖሊስ ህግ አያቅም
- እብድ የያዘው መልክ አይበረክትም
- እብድ ለእብድ ቀን ይባጅ
- እብድ ቀን አይመሽም
- እታከል ተግመል
- እተካከል ተግመል
- እቴ ከሆንሽ ካለስሜ አታልቅሽ
- እቺን ዘዴ ለጋሽ ዘውዴ
- እቺውም ቂጥ ሆና ተፈሳባት አሉ የኔታ
- እቺም ቂጥ ሆና ስንጥቅ ተበጀላት
- እቺ እንጣጥ እንጣጥ አምፖል ለማዉለቅ ነዉ
- እናቱ የሞተችበትና ውሀ የወረደችበት እኩል ያለቅሳሉ
- እናቱ የሞተችበትና ገበያ የሄደችበት እኩል አለቀሱ
- እናቲቱን አይተህ ልጅቷን አግባ
- እናቲቱ ዶሮ ልጅዋን ይዛ ጓሮ ለጓሮ
- እናቴ ቤት ጠላ እጠጣለሁ ብላ የቤቷን ውሀ ትታ ወጣች
- እናቴን ላህል ዘጠኝ ወር ቀረኝ አለች
- እናቴን ሳይ ሴት ማግባቴ ቤትን ሳይ ትምባሆ መጠጣቴ
- እናቴን ያገባ ሁሉም አባቴ ነው
- እናት ለልጇ ነቢይ ናት
- እናት ለልጄ ልጅ ለነገዬ
- እናት ትረገጣለች እንደ መሬት
- እናትዋን አይተህ ልጅቷን አግባ
- እናት የሌለው ልጅ ቀላል እንደ ጌሾ ሳይበላ የበላ ሳይናገር ዋሾ
- እናት የሌለው ተጓዳጅ እርሻ የሌለው ጠላ ወዳጅ
- እናትየዋን ሲከጅሉ ልጅቷን ይስማሉ
- እናቴ ቤት ጠላ እጠጣለሁ ብላ የቤቷን ውሀ ትታ ወጣች
- እናቷ ዘንድ ሄዳ ከመጣች ከእንብላው በቀር ስራ አጣች
- እናንተ ቤት ያለው እሳት እኛ ጋርም አለ
- እናያለን ሲሉ ይታያሉ እናማለን ሲሉ ይታማሉ
- እኔ ልብላ አንተ ጦም እደር
- እኔ ሙቼ እኔው ቄስ ጠርቼ
- እኔም አለኝ ቁስል ያንተን የሚመስል
- እኔም አራዳ አንቺም አራዳ ምን ያጣላናል በሰው በረንዳ
- እኔም ፈጣጣ አንቺም ፈጣጣ ምን ያጣላናል በሰው ሰላጣ
- እኔ በልጄ ሳዝን ልጄ በልጁ ያዝን
- እኔ ባልኩ ይልኩና ይላኩ
- እኔ ሳጣ ልጄ ጥርስ አወጣ
- እኔ ከሞትኩ ሀብቴ ለከዝኔ
- እኔ ከሞትኩ ማዘር ታብዳለች
- እኔ ከሞትኩ ምርጫው ይሰረዛል
- እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አለች አህያ
- እኔ ከሞትኩ እቃ እንዳታውሽ
- እኔን ሲፈጀኝ ልጄን ያቃጥለው
- እኔን አይተህ ተቀጣ በጉድህ እንዳትወጣ አለ ሌባ
- እኔን የወደደ ካንጀት ልጄን የወደደ ካንገት
- እኔን ያለ ካንገቱ ልጄን ያለ ካንጀቱ
- እኔ አለኝ ቁስል ያንቱን የሚመስል
- እኔ አይገባኝ አር ላይ ቁጭ ብሎ ፈስ ገማኝ
- እኔ እበላው ሳጣ ልጄ ጥርስ አወጣ
- እኔ እውነት እናገራለሁ ሌላውን አስኮንናለሁ
- እኔ የምሞተው በእለት ህልሜ የሚደርስው በአመት
- እኔ የምበላው ሳጣ ልጄ ጥርስ አወጣ
- እኔው ሞቼ እኔው ቄስ ጠርቼ
- እኔው ሞቼ እኔው ቄስ ጠርቼ አለች ሴትዮ ቢመራት
- እኔው ተቀርድጄ እኔው ተቀቅዬ ባወጣሁት ነፍስ ተንጎራደደብኝ ባለ ዘጠኝ ልብስ
- እኔ ያለሁት እዚህ አንተ ያለኸው ሽሬ በምን አውቀህ በወሬ
- እኔ የምሞተው ዛሬ ማታ ገብሱ የሚደርሰው ለፍልሰታ
- እንብላም ካላችሁ እንብላ አንብላም ካላችሁ እንብላ አለች አያ ጅቦ
- እንብዛም ብልሀት ያደርሳል ከሞት
- እንብዛም ስለት ይቀዳል አፎት
- እንቁራሪት ዝሆን አክል ብላ ተሰንጥቃ ሞተች
- እንስራዋን ረስታ ውሀ ወረደች
- እንስራዋን ጥላ ወንዝ ወረደች
- እንቅልፍ ታበዥ ከነብር ትፋዘዥ
- እንቅልፍና ሞት እሬትና ሀሞት
- እንቅልፍ የጠላ ውሻ ያሳድጋል
- እንበለ ገንዘብ መዝናናት ያመጣል ውርደት
- እንባ ሲሻኝ አይኔን ጢስ ወጋኝ
- እንኳን ለሙቅ ለገንፎም አልደነግጥ
- እንኳን ለራሱ ለሰው ይተርፋል እሱ
- እንኳን ለቤቱ ይተርፋል ለጎረቤቱ
- እንኳን ለእህቴ ለሌላውም ይዘፍናል አንገቴ
- እንኳን ለገንፎ ለሙቅም አልደነግጥ
- እንኳን ሊያበሉኝ ገርፈው ሰደዱኝ
- እንኳን መሞት ማርጀት አለ
- እንኳን ተልባ ሽቶሽ እንዲያም ዘጠኝ ቂጣ ትፈጃለሽ
- እንኳን እመነኩስ አልከናነብም
- እንኳን እናቴ ሙታ እንዲያውም አልቅስ አልቅስ ይለኛል
- እንኳንስ ዘንቦብሽ እንዲያውም ጤዛ ነሽ
- እንኳን ዘንቦብሽ ድሮም ጤዛ ነሽ
- እንኳን ከፎከረ ያድናል አምላክ ከወረወረ
- እንኳን ከፎከረ ያድናል ከወረወረ
- እንኳን እስቀው አገጠው የለኝ
- እንኳን የሸመተ ያረሰም አይችልሽ
- እንኳን ይችን የዝምብ ጠንጋራ እናውቃለን
- እንኳንስ ዘንቦብሽ እንዲየውም ጤዛ ነሽ
- እንኳንስ ዘንቦብሽ እንዲየውም ጤዛ ነሽ አሉ እትዬ ዘነቡ
- እንደ ልብ የለም ነዳጅ እንደ ልብ የለም በራጅ
- እንደ ልጅ በቀለበት እንደ ድመት በወተት
- እንደ መረብ ሸፍኖ እንደ እንቁላል ደፍኖ
- እንደ እናቴ እንጂ እንደ ሚስቴ ሀሳብ አታውለኝ
- እንደ ርግብ የዋህነት እንደ እባብ ብልህነት
- እንደ ሰው ትመጪ እንደ አውሬ ትሮጪ
- እንደ ሳር ነጭቶ እንደ ውሀ ተጎንጭቶ
- እንደ ሸሸ ተነጥፎ እንደ ቅጠል ረግፎ
- እንደ ሽመላ በሁለት ይበላ
- እንደ ቆጫት ተነስታ የሰው ለቅሶ አጠፋች
- እንደ በሶ አንቆ እንደ እርጉዝ አስጨንቆ
- እንደ ተተከለ ትርሽማ እንደ ተሰጣ ሸማ
- እንደ አባት ስቆ እንደ ንጉስ አውቆ
- እንደ አገሩ ይኖሩ እንደ ወንዙ ይሻገሩ
- እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ
- እንደ አጤ ስርአት እንድ አብርሀም እራት
- እንደ አጥር እንደ ቅጥር
- እንደ አይን ፈሪ እንደ እግር ደፋር የለም
- እንደ እንቁላል ድፍን እንደ መረብ ሽፍን
- እንደ እሸት ፈልፍዬ እንደ ዘንግ መልምዬ
- እንደ እንግዳ ደራሽ እንደ ውሀ ፈሳሽ
- እንደ እንግዳ ጥልቅ እንደ ውሀ ፍልቅ
- እንደ እውር አፍጣጭ እንደ ጎግ ቀላዋጭ
- እንደ ካህን ናዝዞ እንደ ንጉስ አዝዞ
- እንደ ንብ ቀስሞ እንደ ወጥ ቀምሞ
- እንደ ንጉሱ አጎንብሱ
- እንደ ወርቅ አንከብሎ እንደ ሸማ ጠቅሎ
- እንደ ወንድማማች ተበዳደሩ እንደ ባእዶች ተቆጣጠሩ
- እንደ ወይን መልምዬ እንደ እንጨት ተክዬ
- እንደ ውሀ ይፈስ እንደ ጋዝ ይነፍስ
- እንደ ውሌ ደጃዝማች ባሌ
- እንደ ዝንጀሮ በአፋፍ እንደ ጦጣ በዛፍ
- እንደ ዳኛ በውል እንደ ምሰሶ በመሃል
- እንደ ገና ይመታል በገና
- እንደ የቤቱ ብዙ ነው ብልሀቱ
- እንደ ጸሀይ የሞቀ እንደ ጨረቃ የደመቀ እንደ አበባ ያሸበረቀ
- እንደ ጴጥሮስ ብጽላሎተ ርእስ እንደ ጳውሎስ በዘፈረ ልብስ
- እንደ ፈረስ ጆሮ እንደ ሰላጢን ጉሮሮ
- እንደ ፈታሂነቱ ሁላችን እንኮነናለን እንደ መሃሪነቱ ሁላችን እንማራለን
- እንዲህ ሊታረፈን ለሚስቴ ነፈግኋት
- እንዲህ ልጠግብ በሬዪን አረድኩት
- እንዲህ ነድጄ ልሙት የፊቱን በኋላ አድርጎት
- እንዲያውም በመላ ፈስ ዳለቻ ነው
- እንዲያው ብትመለሺ የገንፎ እንጨት ላሺ
- እንዲያው ከምትቀሪ ምንቸቱን አንቅሪ
- እንዳልበላ በአፌ እንዳልበር በክንፌ
- እንዳልተወው ወለድኩ እንዳልሰው ነደድኩ አለች ላም
- እንዳትበላ ለጎሟት እንዳትሄድ ቀየዷ ት
- እንዳትሄድ ቀየዳት እንዳትበላ ለጎማት
- እንዳየን ጤፍ አጋየን
- እንዳዩ መብላት ሆድ ያሰፋል
- እንዳዩ መጉረስ እድህነት ያደርስ
- እንዳያማህ ጥራው እንዳይበላ ግፋው
- እንዳያማ ጥራው እንዳይበላ ግፋው
- እንዳይወልዱ ይመነኩሱ እንዳይጸድቁ ይልከሰከሱ
- እንዳገሩ ይናገሩ
- እንዶድ በገርነቱ ውሀ ወሰደው
- እንዴት ዋልሽ ለእህቱ ግንድ ለሚስቱ
- እንጀራ ለራብ ድንጋይ ለካብ
- እንጀራ ለባእድ መከራ ለዘመድ
- እንጀራ ምን ይጨርሰዋል መጉረስ
- እንጀራ በማየት አያጠግብም
- እንጀራ በሰፌድ አሞሌ በገመድ
- እንጀራን ከባእድ መከራን ከዘመድ
- እንጀራ የለም እንጂ በወተት አምገህ ትበላ ነበር
- እንጀራ ያለወጥ ቤት ያለ ሴት ከብት ያለበረት
- እንጀራ ያለው ክቡድ እንጀራ የሌለው እብድ
- እንጀራ ይጋግሩዋል እማድ ቤት መላ ያማክሩዋል ለሴት
- እንጀራው ሳይኖር ከወጡ አስነኩልኝ
- እንጃ በሰማያት በምድርስ የለም ምክንያት
- እንግዲህ ነገሬን በከንፈሬ
- እንግዳ ደራሽ ውሀ ፈሳሽ
- እንግዳ ሆነህ ብትመጣ ሳይሰለቹህ ውጣ
- እንግዳ ሲወደስ ባለቤቱን ያጎርስ
- እንግዳ ሲያዘወትር ቤተሰብ ይሆናል
- እንግዳ ሲያፍር ባለቤት ይጋብዛል
- እንግዳ ይጋብዛል ባለቤት ሲያፍር
- እንግዳ ደራሽ ውሀ ፈሳሽ
- እንግዳ ፊት ወርቅ ኋላ ብር ኋላ ብረት
- እንግዳ ፊት ወርቅ ኋላ ብር ኋላ ብረት ኋላ ጨርቅ
- እንግዳና ሞት በድንገት
- እንጎቻ የበላ ከራት ይታገሳል
- እንጣጥ እንደ ፌቆ ሙልጭ እንደ ስብቆ
- እንጥስ ቢሉ ቅንጥስ
- እንጨት ሞልቶ ዛቢያ አይገኝበት
- እንጨት ቢጠርቡት ይቀጥናል ሰው ቢበልጡት ይቀናል
- እንጨት ቢያነዱት አመድ ቃጫ ቢፈትሉት ገመድ
- እንጨት አይሸከሙ ላመድ አሮጊት አያገቡም ላትወልድ
- እንጨት አይሸከሙም ላመድ አሮጊት አያገቡም ላትወልድ
- እንጨት ካልነሱት እሳት አይጠፋም
- እንጨት ካልነፈጉት እሳት አይጠፋም
- እኖራለሁ ብለህ እጅግ አትበርታ እሞታለሁ ብለህ ስራ አትፍታ
- እኖር ባይ ተጋዳይ
- እኖር ባይ ተጋዳይ እድን ባይ ተከላካይ
- እኛ ባገራችን ዳቦ ፍሪዳችን
- እኛ ያልፈሳንበት ዳገት የለም አለች አሉ አህያ
- እኛ ምን አገባን በሰው ፖለቲካ እኛንም አይንኩን እኛም ሰው አንነካ
- እኛ ባገራችን ዳቦ ፍሪዳችን
- እከከኝ ልከክህ
- እከክ የሰጠ ጌታ ጥፍሩን አይነሳም
- እከክን ያመጣ ጥፍርንም አላሳጣ
- እከክ የሰጠ ጥፍር አይነሳም
- እከሌ እባብ ነው መሄጃው አይታወቅም
- እኩሉ በዶሮ እኩሉ በሽሮ
- እኩሉን ተላጭታ እኩሉን ተቀብታ
- እካስ ያለ ታግሶ እጸድቅ ያለ መንኩሶ
- እወቁኝ ደብቁኝ
- እወቁኝ ያለ ደብቁኝ
- እወቅ ያለው ባርባ ቀኑ ያውቃል አትወቅ ያለው ባርባ ዘመኑ
- እወደዋለሁ እንጂ ይወደኛል አትበል
- እወዳለሁ እያለ የሚጠላ እጾማለሁ እያለ የሚበላ
- እውር ምን አይቶ ደንቆሮ ምን ሰምቶ
- እውር ምን ይሻል ብርሀን ነጋዴ ምን ይሻል መዳን
- እውር ምን ይሻል ብርሀን በሽተኛ ምን ይሻል መዳን
- እውር ሲቀናጣ ምርኩዙን ወርውሮ ይፈልጋል
- እውር ሲቀናጣ ምርኩዙን ወርውሮ ፍለጋ ይገባል
- እውር ሲቀናጣ ምርኩዙን ይጥላል ብሬክ ይደንሳል
- እውር ሲወበራ በሸማው ላይ አራ
- እውር ሲወበራ በትሩን ይጥላል
- እውር ሲወበራ ከመሪው ይጣላ
- እውር ሲጠግብ ከመሪው ይጣላል
- እውር ነገ አይንሽ ይበራል ቢሏት ዛሬን እንዴት አድሬ አለች
- እውር በበዛበት አንድ አይና ይነግሳል
- እውር በዘንጉ ነጋዴ በወርቁ
- እውር ቢሸፍት ከጓሮ አያመልጥ
- እውር ቢጠግብ ዘንጉን ይወረውር
- እውር ቢፈርዱ እውር ይወልዱ
- እውር ተመሪው ሞኝ ተመካሪው
- እውር ተመሪው ሞኝ ተመካሪው ይጣላል
- እውር ተመሪው ሞኝ ተመካሪው አይጣላም
- እውር ከመሪው ሞኝ ከመካሪው
- እውርን እውር ቢመራው ተያይዞ ገደል
- እውር አያፍር ፈሪ አይደፍር
- እውር እውርን ቢከተል ተያይዘው ገደል
- እውር አያፍር ፈሪ አይደፍር
- እውሻ ሆድ ቅቤ አያድርም
- እውነተኛ ሚስት ባሏን ትወዳለች
- እውነቱን ተናግሮ የመሸበት ማደር
- እውነት ለግዜር ውሸት ለሳጥናኤል
- እውነት ትዘገያለች እንጂ አትቀርም
- እውነት የተናገረ በመርከብ የተሻገረ
- እውነት የሀሰት ባህር ብትሰምጥ ትሟሟለች እንጂ አትጥፋም
- እውነት ይመስላል ልብን ያቆስላል
- እውነትና ሀቅ እያደር ይጠራል እንደ ወርቅ
- እውነትና ንጋት እያደር ይታያል
- እውነትና ንጋት እያደር ይጠራል እንደወርቅ
- እዚያው ሞላ እዚያው ፈላ
- እዚያው ዘንቦ እዚያው ያባራ
- እዛም ቤት እሳት አለ
- እየሰለሉ እድሜ መቁጠር
- እየቆሉ ጥሬ
- እየቆረጣችሁ አንበሳውም ሄደ ነብሩም ሞተላችሁ
- እየበለቱ ሳይሆን እየቧለቱ
- እየቤትህ ግባ እየራስህ ተቀባ
- እየተፈጨ እየተቦካ እየሞተ እየተከካ
- እየታጠቡት ያድፋል እየመከሩት ያጠፋል
- እየወገንህ ቢሉት የመቶ አመት ቆዳ ከብት ተራ ቆመ
- እየወገንህ ቢሉት አክንባሎ ጋጥ ገባ
- እየነገርናቸው እያረጉት ዋዛ ከተለበለበው የተላጠው በዛ
- እዩኝ እዩኝ ያለች ደብቁኝ ደብቁኝ ታመጣለች
- እዩኝ እዩኝ ያለ ደብቁኝ ደብቁኝ ይላል
- እየጠጡ ዝም የጋን ወንድም
- እየፈለገው እወቀኝ ብሎ መጣ
- እየፈለገው እወቀኝ እወቀኝ ብሎ መጣ
- እየፈጩ ጥሬ
- እያለው የማይከፍል ጭኖ የማያደላድል
- እያወቁ ቢስቱ ምንድር ነው መድኃኒቱ
- እያጫወትኳት ታንቀላፋለች
- እያየህ ተናገር እየዋኘህ ተሻገር
- እያየኋት የምታስቀኝ ሚስት አገባሁ
- እያየኋት የምታስቅ ሚስት አገባሁ
- እያደር ይቃቃር
- እያደፈ በእንዶድ እየጎለደፈ በሞረድ
- እዬዬም ሲዳላ ነው
- እዬዬ ሲደላ ነው
- እዬዬ ሲዳላ ነው
- እደ ልቡና ለጸሎት እደ ሰብእና ለመስዋእት
- እደን ገብተህ አምሳያህን ቁረጥ
- እዳ ለቤት ምስጢር ለጎረቤት
- እዳሪ ሳያወጣ የበላ እዳውን ሳይከፍል ጎታውን የሞላ
- እዳሪ ያረሰ ለልጁ አጎረሰ
- እዳ ሰርጉ ነውር ማእረጉ
- እዳ ቢያምርህ ዋስትና ኩነኔ ቢያምርህ ግብዝና
- እዳ ከሜዳ ሲለኝ አደረ
- እዳ አለብኝ ብለህ አትቸገር እዳ የለብኝም ብለህ አትከበር አይታወቅም የአምላክ ነገር
- እዳውን ከፍሎ የከተተ ጌታውን የተሰናበተ
- እዳው ዶሮ መጋቢያው ዳወሮ
- እድለ ቢስ ሲዳር ውሀ ይሞላል በጥር
- እደለ ቢስ አሞራ አንበጣ ሲመጣ አይኑ ይጠፋል
- እደለ ቢስ አሞራ አሸን ሲመጣ አይኑ ይጠፋል
- እድላም አሞሌ በቅሎ ይለውጣል
- እድላም አሞሌ በዶላር ይሸጣል
- እድላም አሞሌ የምርጫ ምልክት ነው
- እድል ተርታውን እጣ ፈንታውን
- እድል የሌለው የሚለፋው ለሰው
- እድል ፈንታ ጥዋ ተርታ
- እድሜ ለንስሀ ዘመን ለፍስሀ
- እድሜ ያልመከረው ሽማግሌ ከውሀ የገባ አሞሌ
- እድሜ ካላነሰው ጊዜ አለው ለሰው
- እድሜና መስታወት አይጠገብም
- እድሜና ቁረንጮ ተበጣጥሶ ያልቃል
- እድሜና ጨርቅ ሲበጣጠስ ያልቅ
- እድሜና ጨርቅ በደህና አያልቅ
- እድር እስከ በጌምድር
- እጁ ተበትር አፉ ከነገር
- እጁን በሰንሰለት እግሩን በብረት
- እጄን በእጄ ቆረጥኩት
- እጄ ከበትር አፌ ከነገር
- እጅ ለነግር ያግዛል ልብ እንደ ንጉስ ያዛል
- እጅ ላፍ ሚዛኑ ነው ባፍ የገባ ለእጅ ሀይሉ ነው
- እጅ ሲነድ ልብ ይነድ
- እጅ እሾህን ይነቅሰዋል ጥጋብ ሞትን ያስረሳዋል
- እጅ እያጠቡት ያድፋል ልጅ እየነገሩት ያጠፋል
- እጅ ከልብስ ምላስ ከጥርስ
- እጅ ከበትር አፍ ከነገር (ይቆጠብ)
- እጅ ይዘው ያስገቡት እጅ ይዞ ያስወጣል
- እጅህን ከባህር አግባ ብታገኝ አሣን ታወጣለህ ባታገኝ ታጥበህ ትወጣለህ
- እጅና አፍ አይተጣጡም
- እጅና አፍ አይተጣጣም
- እጅና ጭራ አፍና እንጀራ
- እጅና ጭራ ስጋና አሞራ
- እጅግ ማግኘት ያመጣል ትእቢት
- እጅግ ስለት ይቀዳል አፎት
- እጅግ ብልሀት ያደርሳል ከሞት
- እሪ በከንቱ ማን ሊሰማ ነው ጩኸቱ
- እገሌን ሲያማ ለኔ ብለህ ስማ
- እገሌ የዋለበት ሸንጎ አይጥ የገባበት እርጎ እርጎውንም ለውሻ እርሱንም ለውርሻ
- እግረ መንገዳቸውን ይሸጣሉ በሬአቸው
- እግረ ቀጭን እንደ ሰሳ ልበ ሙሉ እንደ አንበሳ
- እግረ ቀጭን ይሞታል ሲሉ እግረ ወፍራም ይሞታል
- እግረ ቀጭን ይሞታል ሲሉ እግረ ደንዳና ይሞታል
- እግሩን ለጠጠር ግንባሩን ለጦር
- እግሩ ለጠጠር ግንባሩ ለጦር
- እግር ሄዶ ሄዶ ካር ጉድጓድ ይገባል
- እግር ሲደርስ እግት ይመለስ
- እግር ቢሳሳት ከአንጋዳ አፍ ቢሳሳት ከእዳ
- እግር ተርካብ እጅ ተዛብ
- እግር ከእርካብ እጅ ከዛብ
- እግር ከሸሸ ልብ ሸሸ
- እግር የላት ክንፍ አማራት
- እግር ዜጋ ነው
- እግርህን በፍራሽህ ልክ ዘርጋ
- እግርና እራስ እኔ እለብስ እኔ እለብስ ይጣላሉ
- እግርህን ለጠጠር ደረትን ለጦር
- እግዚአብሄር ለፍጥረቱ ሰው ለሰውነቱ
- እግዚአብሄር ለፍጥረቱ ሰው ለሰውነቱ ያስባል
- እግዜር ሲስጥ እንጀራ በወጥ
- እግዜር ሲቆጣ በዝናብ አር አመጣ
- እግዜር ሲቆጣ በዝናብ አር ያመጣ
- እግዜር በትር ሲቆርጥ ቆላ አይወርድም
- እግዜር ሲጥል እናት አታነሳም
- እግዚአብሄርን ያህል ጌታ ገነትን ያህል ቦታ
- እግዜር በመለኮቱ ጎልማሳ በሚስቱ
- እግዜር ባወቀ ሰማይን አራቀ
- እግዜር እባብን ልቡን አይቶ እግር ነሳው
- እግዚአብሄር የተናገረውን አያስቀር የማያደርገውን አይናገር
- እግዜርን ሳይጨምር የቆጠረ ሁልጊዜ ሲቆጥር ይኖራል
- እግዚሄር ያመነውን ማን ይችለዋል ንጉስ የተከለውን ማን ይነቅለዋል
- እጠጣ ሲል ይዋኛል እበላ ሲል ይዳኛል
- እጣ ያስታርቃል ሙግት ያዳርቃል
- እጣ ያስታርቃል እንጂ አይፈርድም
- እጭን ያለ ኮርቻውን እለምን ያለ ስልቻውን
- እጸድቅ ብየ ባቅፋት አንቀላፋች
- እጸድቅ ብዬ ባዝላት አንቀልባውን በጥርሷ በጠሰችው
- እጸድቅ ብዬ ባዝላት ተንጠልጥላ ቀረች
- እጸድቅ ብዬ ባዝላት ተኝታ ቀረች
- እፍረት ያከሳል ያመነምናል
- እፍኝ ቆሎ ይዘህ ከአሻሮ ተጠጋ
- ኧረ ሳቄ ናልኝ ጥርሴስ አመሉ ነው
- ኧረ ጉዴ ባሌ ገደለ በጎራዴ
ከ
- ከህጻን ጋር አትብላ ድንች ድንቹን ይለቅምብሀል
- ከልብ ካለቀሱ ነጻ ምርጫ ይካሄዳል
- ከልብ ካለቀሱ እንባ አይገድም
- ከልጅ አትጫወት ንፍጥ ይለቀልቅሀል
- ከልጅ ጋር አትጫወት ይወጋሀል በእንጨት
- ከልጅ ጋር አትጫወት አይንህን ያወጣዋል በእንጨት
- ከመሞት መሰንበት
- ከመሸም ጋዝ አለ
- ከመቶ ሀምሳ ዳዊት የልብ ቅንነት
- ከመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል
- ከመደብደብ ይሻላል ማደብ
- ከማትረባ ጉልበት በህግ አምላክ ይሻላል
- ከማን ጋር እንደምትውል ንገረኝ አንተ ማን እንደሆንክ እነግርሀለሁ
- ከማያቁት ወዳጅ የሚያቁት ጠላት ይሻላል
- ከማያውቁት መልአክ የሚያውቁት ስይጣን ይሻላል
- ከማይረባ ቁርስ የጠዋት ጸሃይ ይሻላል
- ከሜዳ ወዲያ ፈረስ ካርባ ወዲያ ቄስ
- ከምኔው ሞትሽና አፈር አፈር ሸተትሽ
- ከምድር ውስጥ ልቃቂት አይወጣም
- ከሞኝ ደጃፍ ሞፈር ይቆረጣል
- ከራስ በላይ ነፋስ
- ከርሞ ጥጃ አድሮ ቃሪያ ታጥቦ ጭቃ
- ከሰው ቀለብላባ ከመሬት ገብጋባ
- ከሰው ክፉ ደባል ከጭነት ክፉ አላል
- ከሰጠሽ ስጪኝ ካልፈለግሽ ፈግጪው ተቀምጠሽበት ከምትደፈጥጪው
- ከቁራ ጋር የዋለች እርግብ ላባዋ ባይጠቁርም ውስጧ ጠቁሮ ትመለሳለች
- ከቁርባን ውጭ ክርስትና
- ከቁንጫ መላላጫ ያወጣል
- ከበሉ አይቀር እንክት ከገሙ አይቀር ጥንብት
- ከበሮ በሰው ላይ ታምሪያለሽ ሲይዙሽ ታደናግሪያለሽ
- ከበሮ በሰው እጅ ታምር ሲይዙዋት ታደናገር
- ከባለቤቱ (በላይ) ያወቀ ቡዳ ነው
- ከባልሽ ባሌ ይበልጣል ማይክሮዌቭ አበድሪኝ
- ከባልሽ ባሌ ይበልጣል ሽሮ አበድሪኝ
- ከባልሽ ጋር ሁኚ ቢሏት የተለመነች መሰላት
- ከባቄላ አይጠፋም ዲቃላ
- ከባእድ የጠጡት ኮሶ ይወጣል ደም ጎርሶ
- ከተኛ አንበሳ ዞርዞር ያለ ቀበሮ ይሻለል
- ከነገረኛ ሰው ስንቅ አይደባልቁም
- ከነገሩ ጾም እደሩ
- ከነገሩ ጾም ይደሩ
- ከኑግ ጋር የተገኘ ሰሊጥ በጣም ይጣፍጣል
- ከናትዋ ልጅዋ ትብስ ባቄላ አሮባት እጅዋን ትልስ
- ከኔ ከወሰድሽው ተቀምጠሽ ልበሽው
- ከወንድም ደረቅ ከወጥ መረቅ
- ከዘመድ አጠገብ የተዳረች ልጅ ትዳር አትይዝም
- ከጠጅ ወዲያ አስካሪ ከባለቤት ወዲያ መስካሪ
- ከኛ ወዲያ ጎራሽ እህል አበላሽ
- ከኛ ወዲያ ፉጨት አፍ ለማሞጥሞጥ
- ከአህያ የዋለች ሳር መጋጥ ትማራለች
- ከአህያ የዋለች ጊደር ለከፋ ጀመረች
- ከአህያ የዋለች ጊደር ፈስ ተምራ መጣች
- ከአህያ የዋለች ጊደር ፈስ ተምራ ትመጣለች
- ከአማት መኖር መጋማት
- ከአባቱ ፊት የሚናገር አፍ ለምጽ ይሆናል
- ከአብሮ አደግህ ጋር አብረህ አትሰደድ
- ከአጋም የተጠጋ ቁልቋል ዘላለም ሲያለቅስ ይኖራል
- ከአፈርኩ አይመልሰኝ
- ከአፍ የወጣ አፋፍ
- ከአፍ የወጣ ቃል ከእጅ የወደቀ እንቁላል
- ከዘላለም ፈስ ያንድ ቀን ቅዘን ይሻላል
- ከዝንጀሮ ቆንጆ ምን ይመራርጡ
- ከዝንጀሮ ቆንጆ አንዷ ውድድሩን አሸነፈች
- ከዳቦ የተገኘ ወጥ አብረህ ግመጥ
- ከገሙ አይቀር መጠንባት ነው
- ከገሙ አይቀር ቅርንት ነው
- ከጦጣ የዋለ ጉሬዛ እህል ፈጅቶ ገባ
- ከፈሳም ቤት ቅዘናም ገባበት
- ከፍትፍቱ አጉርሱኝ
- ከፍትፍቱ አጉርሱኝ ከመረቁ ጾመኛ ነኝ
- ከፍትፍቱ ፊቱ
- ኩላሊት ካላየ አይን አያይም
- ካለመናገር ደጃዝማችነት ይቀራል
- ካለቀ መቆጠብ ከመሽ መንጠብጠብ
- ካለቀሰ አይቀር በደንብ ምታው
- ካለቃና ከጠገራ ፊት ዞር በል
- ካለ ፈጣሪ አሟጠሽ ጋግሪ
- ካላት ከፍላ ኑ ቅመሱ የምትል ናት ተቃመሱ
- ካልቀበጡ አይዘሉ ካልዘለሉ አይሰበሩ
- ካልበሉበት ደጀ ሰላም ከበሉበት ቤት ነው
- ካልታዘልኩ አላምንም አለች ሙሽራ
- ካልደፈረሰ አይጠራም
- ካልደፈረሰ አይጠራም ካልጠራ አይጠጣም
- ካልፈላ አይገነፍል ካልተጣደ አይበስል
- ካረገዘች ክታብ ያዘች ፈሷን ፈስታ ቂጧን ያዘች
- ካረጁ አይበጁ
- ካረጁ አይባጁ
- ካንቺ የተሻለች ሴት ባላገኝ ሌላ እንዳታገቢ ጠብቂኝ
- ካንድ ልጃገረድ ይገኛል ሁለት ዘመድ
- ካንዠት ካለቀሱ እንባ አይገድም
- ካያያዝ ይቀደዳል ካነጋገር ይፈረዳል
- ካገሩ የወጣ አገሩ እስኪመለስ ቢጭኑት አህያ ቢጋልቡት ፈረስ
- ኳስ ለራስሽ ስተይ ጎል ግቢ አለዚያ ፎሪ ብለው ይጠልዙሻል
- ካንጀት በላይ ፍቅር እያደር ያቃቅር
- ካንጀት ነው ካንገት
- ካዋቂ ጠያቂ
- ክረምት ከጭቃ በጋ ከግጫ
- ክረምትና በጋ ቆላና ደጋ
- ክረምትና ኮሶ ቤት በምሰሶ
- ክረምትና ወላድ ሲጠሉት ያከብራል
- ክረምትን የፈጀ በጋ እዳውን የፈጀ ዜጋ
- ክፉ ሴት በኑሮ ላይ ከባድ ሬሳ ትሆናለች
- ክፉ ሴት ጠዋት ወተት ማታ ሬት
- ክፉ ባይኖር የመልካም ዋጋ አይታወቅም
ወ
- ወልዶ አይስም ዘርቶ አይቅም
- ወረቱን የተቀማ ነጋዴ ዋግ የመታው ስንዴ
- ወሬኛ ሚስት ዘርዛራ ወንፊት
- ወራጅ ውሀ አይውሰድህ ሟች ሽማግሌ አይርገምህ
- ወሬ ቢነግሩህ መላ ጨምር
- ወሬ ቢያበዙት ባህያ አይጫንም
- ወርቅ የያዘ ቀበዝባዛ እህል የያዘ ፈዛዛ
- ወርቅ የጫነች አህያ ስትገባ የማይፈርስ ግርግዳ የለም
- ወስፌ ቢለግም ቅቤ አይወጋም
- ወንዝ ለወንዝ መቀደስ ያረፈ ሰይጣን መቀስቀስ
- ወንዝ ለወንዝ ሩዋጭ የሰው በግ አራጅ
- ወንድ ልጅ ተወልዶ ካልሆነ እንዳባቱ ስጡት አመልማሎ ይፍተል እንደናቱ
- ወንድ ልጅ እና ቢላዋ ጮማ ይወዳሉ
- ወንድ ሊበላ የሴት ሌባ
- ወንድ ልጅ በተሾመበት ሴት ልጅ ባገባበት
- ወንድ ልጅ ለፈረስ ሴት ልጅ ለበርኖስ
- ወንድ ልጅ አንድ ቀን እንደ አባቱ አንድ ቀን እንደ እናቱ
- ወንድ ባለ በእለት ሴት ባለች በዓመት
- ወንድ እንደያዙት ነው
- ወንድ ከዋለበት ከብት ከተስማራበት
- ወዛም ገማ ቢለው የነጭ ወሬ ነው አለው
- ወይ አበዳሪ ወይ ተበዳሪ ይሞታል
- ወይ አታምር ወይ አታፍር
- ወይዘሪትነት ያንድ ቀን ርቀት
- ወይ ዘንድሮ ! አለች ቀበሮ
- ወይኖ አረሰው ወይኖ ጎረሰው
- ወደሽ ከተደፋሽ ቢረግጡሽ አይክፋሽ
- ወደሽ ነው ቆማጢት ንጉስ ትመርቂ
- ወደቀ ሲሉ ተሰበረ ነው
- ወደው የዋጡት ቅልጥም ከብርንዶ ይጥም
- ወዳጅ ይመጣል ከራያ ጠላት ይወጣል ከጉያ
- ወገኛ ቀበሌ ወረዳ (ከፍተኛ) መሆን ያምራታል
- ወግ ነው ሲዳሩ ማልቀስ
- ወጠጤ ለወጠጤ ቢማከሩ እንዳይታረዱ
- ወጡ ሳይወጠወጥ ወስከምቢያው ቂጥጥ
- ወጣ ወጣና እንደ ሸንበቆ ተገነደሰ እንደ ሙቀጫ
- ወጥን ማን ያውቃል ቢሉ ቀላዋጭ
- ወጥን የሚጨርስ መጎራረስ ሴትን የሚያስመታት መመላለስ
- ወጪ ያዘዘባት ጥቁር ሴት አንገቷን ትነቀሳለች
- ወጭትና ሴት ሲከናነቡ ይሻላል
- ወፍ እንዳገርዋ ትጮሀለች
- ወፍጮና ሴት መቼም አይሞላለት
- ዋቢ ያለው ያመልጣል ዋቢ የሌለው ይሰምጣል
- ውሀ ለሚወስደው ሰው በትርህን እንጂ እጅህን አትስጠው
- ውሀ ለቀደመ ግዳይ ለፈለመ
- ውሀ ለወሰደው ካሳ አይከፍልም
- ውሀ ለወሰደው ፍለጋ የለውም
- ውሀ ሊያንስ ሲል ይገማል ሰው ሊያንስ ሲል ይኮራል
- ውሀ ላነቀው ባለቤቱ ላላወቀው መድሀኒት የለውም
- ውሀ ልትቀዳ ሄዳ እንስራዋን ረስታ መጣች
- ውሀ መልሶ ውሀ ቀልሶ
- ውሀ መመለስ ወደ ሌላ ማፍሰስ
- ውሀ ምን ያስጮኸዋል ድንጋይ
- ውሀ ምን ያገሳ ድሀ ምን ያወሳ
- ውሀ ሲወስድ እያሳሳቀ ነው
- ውሀ ሲደርቅ ይሸታል ሰው ሲከዳ ይወሸክታል
- ውሀ ሲጎድል ተሻገር ዳኛ ሲገኝ ተናገር
- ውሀ በለዘብታ ድንጋይ ይፈነቅላል
- ውሀ በብልሀት ይቆላል በእሳት
- ውሀ በእሳት ሰስ በዳገት
- ውሀ ቢወቅጡት መልሶ እንቦጭ ነው
- ውሀ ቢወቅጡት እንቦጭ
- ውሀ ቢደርቅ አሳ ያልቅ
- ውሀ ቢጠቅምህም ማእበሉን አትመኝ
- ውሀና ገደል እያሳሳቀ ይወስዳል
- ውሀና ጠጅ እኩል ይጠጣሉ
- ውሀን መመለስ ወደ ሌላ ማፍሰስ
- ውሀን ምን ያስጮኸዋል ድንጋይ
- ውሀ አያንቅ ነገር አያልቅ
- ውሀ እድፍን ያጠራል ትምህርት ልብን ያጠራል
- ውሀ ከነቁ አባባ ከአጽቁ
- ውሀ የሚወስደው ሰው አረፋ ይጨብጣል
- ውሀ የጥቅምት ነበርሽ ታዲያ ማን ይጠጣሽ
- ውሀ ጭስ ክፉ ሴት ሰውን ያበራሉ ከቤት
- ውሀ ጭስና ክፉ ሴት ሰውን ያባርራሉ ከቤት
- ውሀውም እንዳይደርቅ አሳውም እንዳያልቅ
- ውሀውም እንዳይደርቅ አሳውም እንዳያልቅ አድርጎ ነው እርቅ
- ውል አያወላውል ምላት አያሻግር
- ውል ያዋውላል ታንኳ ያሻግራል
- ውል ያዋውላል ታንኳ ያሻግራል አቧራ ያስላል
- ውስጥ ውስጡን ድመትም አውሬ ነች
- ውሻ ምን አገባት እርሻ
- ውሻ በሰፈሩ ጅብ ነው
- ውሻ በቀደደው ድመት ተከተለች
- ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል
- ውሻ በበላበት ይጮሀል
- ውሻን በርግጫ ማለት እንካ ስጋ ማለት
- ውሻ የጌታውን ጌታ አያውቅም
- ውሽማዋን ብታይ ባልዋን ጠላች
- ውጣ ያለው ብር ግርግዳ ሲፍቅ ያድራል
- ውጣ ያለው ገንዘብ ግርግዳ ሲቧጥጥ ያድራል
- ውጣ ያለው ገንዘብ ግርግዳ ሲጭር ያድራል
ዘ
- ዘላለም ከመፍሳት አንዴ መቅዘን
- ዘመነ ግልምቢጥ ውሻ ወደ ሰርዶ አህያ ወደ ሊጥ
- ዘመነ ግርምቢጥ ውሻ ወደ ሰርዶ አህያ ወደ ሊጥ
- ዘመን እንደንጉሱ አውድማ እንደንፋሱ
- ዘመን የሚወልደውን ንጉስ የሚፈርደውን
- ዘመን የሚወልደውን ንጉስ የሚፈርደውን የሚያውቅ የለም
- ዘመን የሰጠው ቅል ድንጋይ ይሰብራል
- ዘመን የወለደው ንጉስ የወደደው
- ዘመን ያነሳው ቅል ድንጋይ ይሰብራል
- ዘመደ ብዙ ጠላሽ ቀጭን ነው
- ዘመደ ብዙ ጠላው ቀጭን ነው
- ዘመዱን ያማ ገማ
- ዘመዱን ያማ ለራሱ ገማ
- ዘመዱን ያማ እራሱ ገማ
- ዘመድ ሲጣላ ያረክሳል
- ዘመድ ሲፈራ ላሊበላ ሲኮራ
- ዘመድ በዘመዱ አይጨክንም ሆዱ
- ዘመድ ቢረዳዳ ችግርም ባልጎዳ
- ዘመድ ቢረዳዳ ችግርም አይጎዳ
- ዘመድና መድሀኒት የተቸገሩ ለት
- ዘመድና መድሀኒት በተቸገረ ቀን ይፈለጋል
- ዘመድና ሚዛን ከወገብ ይይዛል
- ዘመድና እሳት በሩቅ
- ዘመድና ሳንቲም ከመንገድ ወድቀው ሳንቲሙን አነሱ ዘመድን ጥለው
- ዘመድና ዋንጫ እያለቀሰ ይመጣ
- ዘመድና ገንዘብ ሳያስቡት ይገኛል
- ዘመድና ፍየል ቤት አጥፊ ነው
- ዘመድን ከዘመድ ጋር ማማት ዳቦ እንደመግመጥ ነው
- ዘመድን ከዘመድ ጋር ማማት ጮማ እንደመቁረጥ ይቆጠራል
- ዘመድን የሚወጉበት ጦር ጀንፎው አይለቀቅም
- ዘመድን የሚወጉበት ጦር ጅንፎው አይለቀቅም
- ዘመድ ከዘመዱ አህያ ካመዱ
- ዘመድ ያረጀ በልቶ ያፈጀ
- ዘመዶችዋ ሁሉ ይሏታል ግንድ አልብስ
- ዘምቶ ተወረሰ
- ዘምቶ ያረጀ በልቶ ያፈጀ
- ዘረፋና ቀን ካልተሻሙበት ያልቃል
- ዘሩ የጣቴ ምድሩ ያባቴ
- ዘር ልትበደር ሂዳ እህል ሲሸት መጣች
- ዘር ከልጓም ይስባል
- ዘር ከልጓም ይጠቅሳል
- ዘር ከልጓም ይስባል
- ዘር ከበረከት ትውልድ ከምርቃት
- ዘርቶ መቃም ወልዶ መሳም
- ዘርቶ ያልበላ አምላክን ጠላ
- ዘር የጣቴ ምድሩ ያባቴ
- ዘባራቂ ላባ ቀረሽ እብድ አስተኔ
- ዘባራቂ ይወዳል ምራቂ
- ዘቅዝቀው ቢቀብሩት ቀና ብሎ አደገ
- ዘንዶ የዳገት በረዶ
- ዘንጋዳ ከቆረጡት አገዳ ሚስት ከፈቷት እዳ
- ዘንጋዳ ተቆረጡት አገዳ እዳኛ ከደረሱ እዳ
- ዘንጋዳና ወታደር በመከር ጊዜ ይታይ ነበር
- ዘንጋዳ የገለበጠ አባቱን የገላመጠ
- ዘንዶ የዳገት በረዶ
- ዘንግ ከተተከለ ልብ ተከፈለ
- ዘኬውን ሲቋጥር አነቀው ነብር
- ዘጠኝም ቢታለብ ለኔ ያው ገሌ ነው
- ዘጠኝ ሞት መጣ ቢሉት አንዱን ግባ በለው
- ዘጠኝ ሞት መጣ ቢሉት አንዱን ግባ በለው አለ
- ዘጠኝ ሞት መጣ ቢሉት አንዱን ግባ በለው አለው
- ዘጠኝ ጠጥቶ አስረኛውን የወደደ በሙሉ ነደደ
- ዘጠኝ ጠጥቶ አስር የወደደ በሙሉ ተናደ
- ዘጥ ዘጥ አቁማዳ ቂጥ
- ዘገየች ከረመች ቆይታ መጣች
- ዘፈን በበገና ነገር በዋና
- ዘፈን በከበሮ አዋጅ በደበሎ
- ዘፈን በገና ነገር በዋና
- ዘፈን አለ በገና ነገር አለ በዋና
- ዘፈን አለ በገና ነገር አለ ዋና
- ዘፍኖ አያምር እንኳን አልቅሶ
- ዛሬ ጠምቃ ፈጀችው ጠልቃ ጠልቃ
- ዛሬ የትላንት ነገ ነበረች ዛሬ ደግሞ የነገ ትላንት ትሆናለች
- ዛር ልመና ሳይያዙ ገና ከተያዙ ብዙ ነው መዘዙ
- ዛብ የሌለው ፈረሰኛ ምሳ የሌለው ኮሰኛ
- ዛፍ ሲወድቅ ከግንዱ ሰው ሲቸገር ከዘመዱ
- ዛፍ በሌለበት እንቧጮ አድባር ይሆናል
- ዛፍ እራሱን ያውቃል
- ዛፍ ዝናብ ያስጥላል ትልቅ ሰው ከዳ ያስጥላል
- ዛፍ ያለቅርንጫፍ አይደምቅም ሰው ያለሰው አይከበርም
- ዛፎች ቢጠፉ ቁጥቋጦች ተሰለፉ
- ዛፎች ቢጠፉ ቁጥቋጦች ዛፎች ነን አሉ
- ዛፎች አለቁ እና ግራሮች ዛፍ ሆኑ
- ዜማ በሀሌ ነገር በምሳሌ
- ዝሆኑ ሳለ ዱካውን
- ዝሆን ለቀንድ ባላባት ለትውልድ
- ዝሆን ማለት ከሞኝ ያስቆጥራል
- ዝሆንም ለሆዱ ድምቢጥም ለሆዱ ወደ ወንዝ ወረዱ
- ዝሆን ቂጡን ተማምኖ ግንድ ይውጣል
- ዝሆን ቢያንቀላፋ ዛፍ ተደግፎ ነው
- ዝሆን እንሆት ፍለጋው ወዴት
- ዝሆን እንሆ ፍለጋው ወዴት
- ዝሆን ጥርሱን አዝመራ ገብሱን
- ዝሆንና ዝሆን ቢጣሉ የሚጎዳው ሳሩ
- ዝሆን የዋለችበትን ትመስላለች
- ዝም ባለ አፍ ዝምብ አይገባበትም
- ዝም ብትል ባትከበርም ችላ ትባልበታለህ
- ዝምታ ለበግም አልበጃት አስራ ሁለት ሆና አንድ ነብር ፈጃት
- ዝምታ ራሱ መልስ ነው
- ዝምታ ራሱን የቻለ መልስ ነው
- ዝምታ ወርቅ ነው
- ዝምታ ወርቅ ነው መናገር ብር ነው
- ዝም አይነቅዝም
- ዝም ያለ ተንኮለኛ ይመስላል እንብላ ያለ ስስታም ይመስላል
- ዝርክርክ ከወንፊት የባሰ ዝክዝክ
- ዝቅ ቢል ከገብርዬ ከፍ ቢል ከዚያ ሰውዬ
- ዝባድን ከውሻ እምነትን ከባለጌ አትሻ
- ዝናር የሌለው ነፍጠኛ አለንጋ የሌለው ፈረሰኛ
- ዝናብ ለዘር ጠል ለመከር
- ዝናብ ለዘር ጠል ለመኸር
- ዝናብ ሊጥል ሲል ይነፋፍሳል
- ዝናብ ሊጥል ሲል ይነፍሳል
- ዝናብ ሲያባራ ከዋሻ ምን ሊሻ
- ዝናብ ሲያባራ ዋሻ ምን ያሻ
- ዝናብ ሳይመጣ ሁሉ ቤት እንግዳ ባይመጣ ሁሉ ሴት
- ዝናብ ሳይመጣ ገና የውሀን መንገድ መጥረግ ደህና
- ዝናብ ከደመና ነገር ከዋና
- ዝናብ ካልጣለ ሁሉ ቤት እንግዳ ካልመጣ ሁሉ ሴት
- ዝናብ ካባራ ወደ ዋሻ
- ዝናብና ልጅ ሲጠሉት ያከብር
- ዝናብ ዘነበ ቢለው ከደጅህ እየው
- ዝንብ ሩቅ አይበር ሜዳ አደግ ዱር አይደፍር
- ዝንብ ሩቅ አይበር የሜዳ ልጅ ዱር አይደፍር
- ዝንብ ሳያቆሙ ዝግን አይቅሙ
- ዝንብ ሳይቅሙ ዝግን አይቅሙ
- ዝንብ ቢሰበሰብ መግላሊት አይከፍትም
- ዝንብ ቢሰበሰብ ጋን አይከፍትም
- ዝንብ ካይን ጭራ ከዘባን
- ዝንጀሮ መቀመጫዬ ይብሳል አለች
- ዝንጀሮ የመቀመጫዬ ይቅደምልኝ አለች
- ዝንጀሮ ሰው ነበር ይላሉ ድሮ
- ዝንጀሮ ቢሰበሰብ ውሻን አይመክትም
- ዝንጀሮ እንሳሳቅ ካልሽ ነዶዬን መልሽ
- ዝንጀሮና ጥዋ ካፉ ነው የሚያዝ
- ዝንጀሮና ጥዋ ክፉ ነው የሚይዝ
- ዝንጀሮን በበግ ለውጠኝ ቢለው ጣፍጩን ትቼ አልማጩን
- ዝንጀሮ የራሷን ጠባሳ ሳታይ በባልንጀራዋ ሳቀች
- ዝንጀሮ የቂጧን መላጣ ሳታይ በባልንጀራዋ ትስቃለች
- ዝንጅብል ማን ቢሉህ ማነኝ ትል
- ዞር አሉ አልሸሹም
- ዞሮ ዞሮ መዝጊያው ጭራሮ
- ዞሮ ዞሮ እራቱ ጥሬ
- ዞሮ ዞሮ የዶሮ አንገት በማሰሮ
- ዞሮ ዞሮ የዶሮ አንገት ከማሰሮ
የ
- የሀምሌ ብራ የባልቴት ወብራ
- የሀምሌን ውሀ ጥም የህዳርን ራብ የሚያውቅ ያውቀዋል
- የሀምሌ ጭቃ ቅቤ ለጋ
- የሀር ገመድ የበቅሎ ክበድ
- የሀብታም ልጅ ሲጫወት የድሀ ልጅ ይሞታል
- የሀብታም ልጅ ወደ ቦሌ የድሀ ልጅ ወደ ባሌ
- የሀጢአት ክፉ ጉቦ የበሽታ ክፉ ተስቦ
- የሀጥኡ ዳፋ ጻድቁን ያዳፋ
- የሁለት ሴቶች ባል ይሞታል ይበላል ሲባል
- የሁለት አገር ስደተኛ
- የሁለት እዳ ከፋይ
- የኋላ የኋላ አይቀርም ዱላ
- የህልም ሩጫ የጨለማ ፍጥጫ
- የሆነ አይመለስ እሳት አይጎረስ
- የሆድ ማበድ ያስቃል በግድ
- የሆድ ምቀኛ አፍ ነው
- የሆድ ምቀኛው አፍ ነው
- የሆድ ብልሀት የጋን መብራት
- የሆድ ነገር ሆድ ይቆርጣል
- የለመነ መነመነ
- የለመነ ያገኛል የነገደ ያተርፋል
- የለመኑትን የማይረሳ የነገሩትን የማይረሳ
- የለመደ ለማኝ ቁርንጮዬን ቀማኝ
- የለመደ ልማድ ያሰርቃል ከማእድ
- የለመደ ልማድ ያሰድዳል ከማእድ
- የለመደ መደመደ
- የለመደ እጅ ጆሮ ግንድ ያስመታል
- የለመደ ፈረሰኛ ዛብ አይጨብጥ እርካብ አይረግጥ
- የለመደች ጦጣ ሁልጊዜ ሽምጠጣ
- የለማኝ ስልቻ ሲንከባለል ከለማኝ እጅ ይወድቃል
- የለማኝ ቅንጡ ይላል በወጥ አምጡ
- የለም ቀሪ ካለ ፈጣሪ
- የለበሰ የማንንም ጎረሰ
- የለበሱት ያልቃል የሰጡት ያጸድቃል
- የለጋስ ምስክሩ መስጠቱ
- የላሜ ልጅ ያውራዬ ውላጅ
- የላም መንጃ የሰማ መከንጃ የማር መቅጃ
- የላም ወተቱን የጌታ ከብቱን
- የላከ እንደ አፉ ያከከ እንደ እጁ አይሆንለትም
- የላይ ለምጡን የውስጥ እብጡን ባለቤቱ ያውቀዋል
- የላይ አልጋ የውስጥ ቀጋ
- የላይኛው ከንፈር ለክርክር የታችኛው ከንፈር ለምስክር
- የላጭ ልጅ ጸጉሩ ድሬድ ሆነ
- የላጭን ልጅ ቅማል በላት
- የላጭን ልጅ ቅማል በላው ያናጢን ልጅ ጅብ በላው
- የሌለው ልብም የለው
- የሌለው ልብ የለው ወዳጅ የለው
- የሌለው ሚስት የለው ወዳጅ የለው
- የሌሊት ግስገሳ የቀን ዘለሳ
- የሌላት እራት ደግሞ ምሳ አማራት
- የሌባ መኝታው አመድ መታሰሪያው ገመድ
- የሌባ ምኝታው ካመድ መታሰሪያው ገመድ
- የሌባ ሞኝ ከጎተራ ስር ይገኝ
- የሌባ አይነደረቅ መልሶ ልብ ያደርቅ
- የሌባ እጁን የፍየል ልጁን
- የሌባ ዋሻ የቀማኛ መሸሻ
- የሌባን ጠበቃ አደባልቀህ ውቃ
- የሌባን ጠበቃ ደርበህ ውቃ
- የልመና በሬ ትክክል አይሄድም
- የልመና እንጀራ ምንጊዜም ከልመና አያወጣም
- የልቡ ሳይደርስ እድሜ ይደርስ
- የልቡን ሲነግሩት የኮረኮሩትን ያህል ይስቃል
- የልቡን አድራጊ አይናደድም
- የልብህን ቢያናግሩህ አለ እዳ ቢለቁህ
- የልብህን ቢያናግሩህ አለ እዳ ቢሰዱህ
- የልብስ ቀላል ባለቤቱን ያቀላል
- የልጅ ልጅ እህል ፈጅ ኋላም ጅብ ያስፈጅ
- የልጅ ልጅ ጅብ አስፈጅ
- የልጅ መልከ ጥፉ በስም ይደግፉ
- የልጅ ሞት የእግር እሳት
- የልጅ ስጋ በናቷ ቅቤ
- የልጅ ቀላቢ የአህያ ጋላቢ
- የልጅ ብልጥ እየቀደመ ይውጥ
- የልጅ ብልጥ የፊት የፊቱን
- የልጅ ብልጥ የሰጡትን
- የልጅ እናት አባይ ናት
- የልጅ ተሟጋች በፊት ሰማይ ያያል ኋላ መሬት
- የልጅ ተሟጋች ጠዋት ሰማይ ማታ ምድር ምድር ያይ
- የልጅ ነገር ሁለት ፍሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ
- የልጅ ነገር ጥሬ በገል
- የልጅ ክፉ ዲቃላ የቤት ክፉ ሰቃላ የልብስ ክፉ ነጠላ
- የልጅ ክፋቱ አለመከማቸቱ
- የልጅ ጥፉ በስም ይደግፉ
- የልጅ ፍቅር የሴት ከንፈር እናትን አያስቀብር
- የልጅቷን ስጋ በእናቷ ቅቤ
- የልጅ ፍሬ አንዱ ብስል አንዱ ጥሬ
- የሎሌ አልቃሽ የሴት ቀዳሽ
- የሎሌ አልቃሽ የሴት ቀዳሽ የቄስ አውደሽዳሽ
- የመልኳን ሲሏት የጠባዩዋን
- የመሬት ሴሰኛ ከመንገድ ዳር ይተኛ
- የመሬት እርጥብ እሸቱን ደረቅ ምርቱን
- የመስከረም ውስጡ በጋ ያረመኔ ልቡ ቀጋ
- የመቀናጆ በሬ ሲመሽ ወደ ቤቱ ይስባል
- የመበደሪያ አፍ መክፈያ አይሆንም
- የመተሩበት እጅ ይወዛል የተማከሩት ዳኛ ያግዛል
- የመታሰር ምልክቱ መጋዝ የመዳኘት ምልክቱ መያዝ
- የመነነ ከዱር የሞተ ከመቃብር
- የመነነ ከዱር የሞተ ከመቃብር አይወጣም
- የመነኩሴ ሎሌ የክረምት አሞሌ
- የመንማና የለው ገናና
- የመንታ እናት ተንጋላ ትሞት
- የመንገድ ዳር እሸት ባል የሌላት ሴት
- የመንገድ ዳር እሸት ባል የሌላት ሴት ለማንም ናት
- የመንዝ ልጅ እራያ ሂዶ ብልቱን አያወዛውዝም
- የመከሩበት ሞተ የወርወሩበት ተሳተ
- የመከራ ልጅ ሁል ጊዜ መከራ መስሎ ይታያል
- የመከራ ሌሊት አያልቅም
- የመከራ ሎሌ መከራ መስሎ ይታያል
- የመከራ ውዝፍ ያለበት ነጋዴ ከሚወረር አገር ይደርሳል
- የመከራን ጉድጓድ ሚዳቋ አትዘለውም
- የመኮንን ልጅ በከተማ የድሀ ልጅ በውድማ
- የመኮንን ልጅ አዘን ቢነግሩት አደን
- የመዝሙር መጀመሪያ ሀሌታ የዘፈን መጀመሪያ እስክስታ
- የመጠጡት ቅልጥም ከብርንዶ ይጥም
- የመጣ ሳይመጣ የውሃ ቦይ ጥረግ
- የመጣው ቢመጣ ወይ ፍንክች ያባ ቢላዋ ልጅ
- የመጣ ቢመጣ ከቤቴም አልወጣ
- የመጥረቢያ ልጅ መዝለፊያ
- የመጥረቢያ ልጅ ጥልቆ አይደል የሚባለው
- የሙሽራ እድሜ ቢያጥር የሰርጉ ድግስ ሆነ ለተዝካር
- የሙት ቀናተኛ ሚስቴን አደራ ይላል
- የሙት አልቃሹ የቁም ወራሹ
- የሙት አልቃሹ የቁም ወራሽ
- የሙት የለውም መብት
- የሚሆን ቢሆን ዝሆን ይበላ ቢሆን
- የሚሉሽን በሰማሽ ገበያም ሳልወጣሽ
- የሚሉሽን በሰማሽ ገበያም ባልወጣሽ
- የሚመክተው ጋሻ የሚጠጋበት ዋሻ
- የሚመክተው ጋሻ የሚጠጋበት ዋሻ የለውም
- የሚመጣውን እንድታውቅ ያለፈውን እወቅ
- የሚሞት ልጅ አንገቱ ረጅም ነው
- የሚሮጡበት ሜዳ የሚወጡበት ቀዳዳ
- የሚሰራ ምንም አያወራ
- የሚሰርቀውን ያጣ ሌባ ሰላማዊ መስሎ ይገባ
- የሚሰርቀውን ያጣ ሌባ ሰላማዊ መስሎ ይገባል
- የሚሰርቅ ሰው አደራ ቢያስቀምጡት እጅ ይነሳል
- የሚክድ ሰው አደራ ቢያስቀምጡት እጅ ይነሳል
- የሚሰጥም እሾህ ይጨብጣል
- የሚሰጥም ገለባ ይጨብጣል
- የሚስት መናኝ የእናት አገር ለማኝ
- የሚስት አንባሻ የጎረቤት ውሻ የደጅ እርሻ
- የሚስት አሳቢ የጥንድ በሬ ሳቢ ይስጥህ
- የሚስት ወይዘሮ እርሻው ጋራ ዞሮ
- የሚስት ዘመድ የማር አንገት
- የሚስት ዘመድ የማር እንጎቻ
- የሚሸሹበት አምባ ሲሸሽ ተገኘ
- የሚበላው ካጣ ይበላለት ያጣ
- የሚበላው ካጣ ይበላበት ያጣ
- የሚበጀውን ባለቤት ያውቃል
- የሚከርመውም የማይከርመውም ባንድነት ዝናብ ይለምናል
- የሚከርመውም የማይከርመውም አንድነት ዝናብ ይለምናል
- የሚካኤል ስለት ለገብርኤል ምኑ ነው
- የሚካኤል እለት ለገብርኤል ምኑ ነው
- የሚወዱትን ሲያጡ የጠሉትን ይቀላውጡ
- የሚወዱትን አቅፎ የሚጠሉትን ነቅፎ
- የሚወዱትን እቅፍ የሚጠሉትን ንቅፍ
- የሚወጋ ጦር ከእጅ ሲወጣ ያስታውቃል
- የሚውል ሆድ ማለዳ ያረግዳል
- የሚውል ሆድ ማለዳ ይርበዋል
- የሚወጡበት ገደል የሚንጠለጠሉበት ቅጠል
- የሚጠጉበት ገደል የሚንጠለጠሉበት ቅጠል
- የሚዛንን አባይ ለእሳት የዳኛን አባይ ለሰንሰለት
- የሚያልቅ እህል ከማያልቅ ዘመድ ያጣላል
- የሚያልፍ ቀን የማያልፈውን ስም ያወርሳል
- የሚያልፍ ቀን የማያልፍ ስም ያወርሳል
- የሚያልፍ ነገር የማያልፍ ስም ይሰጣል
- የሚያልፍ ውሀ አደረገኝ ድሀ
- የሚያልፍ ውሀ አደረገኝ ድሀ አለች ልጅዋን ጎርፍ የወሰደባት
- የሚያልፍ ዝናም አይምታህ የሚሞት ሽማግሌ አይርገምህ
- የሚያልፍ ዝናም አይምታህ የሚያድግ ልጅ አይጥላህ
- የሚያማ ጠበኛ ዘወር ይበል ከኛ
- የሚያስፈራውን ለሚነግርህ የሚያስቀዝነውን ንገረው
- የሚያስፈሳውን ለሚነግርህ የሚያስቀዝነውን ንገረው
- የሚያብረቀርቅ ሁሉ ወርቅ አይደለም
- የሚያድግ ልጅ በእናቱ እጅ
- የሚያድግ ልጅ አትበድል የሚሞት ሽማግሌ አታቃልል
- የሚያድግ ልጅ አትበድል የሚሞት ሽማግሌ አታቅል
- የሚያድግ ልጅ አይጥላህ የሚሞት ሽማግሌ አይርገምህ
- የሚያድግ ልጅ አይጥላህ የሚያልፍ ዝናብ አይምታህ
- የሚያድግ ዛፍ በቁጥቋጦው ያስታውቃል
- የሚያድግ ዛፍ ከቁጥቋጦው ያስታውቃል
- የሚያጠግብ ቂጣ ከምጣዱ የሚወጣ ጥጃ ከገመዱ
- የሚያጠግብ ቂጣ ከምጣዱ የሚወጣ ጥጃ ከገመዱ ያስታውቃል
- የሚያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል
- የሚያፈስ ቤት ጨቅጫቃ ሚስት
- የሚዳቋ ብዛት ለነአቶ ውሻ ሰርግ ነው
- የሚዳቋ ብዛት ለውሻ ሰርግ ነው
- የሚዳቋ ግርግርታ ለውሻ ሰርጉ ነው
- የሚዳቋ ግርግርታ ለውሻ ሰርግ ነው
- የሚጣፍጥ ምግብ ምንድን ነው ቢሉት ሲርብ የበሉት
- የሚጣፍጥ ምግብ ሲርብ የበሉት ነው
- የሚጣፍጥ ምግብ ምንድን ነው ቢሉት ሲርብ የበሉት ነው
- የሚፈልግ ያገኛል የሚተኛ ያልማል
- የሚያፈስ ቤት ጨቅጫቃ ሚስት
- የሚፈርስ ከተማ ነጋሪት ቢመታ አይሰማ
- የሚፈታ ከተማ አዋጅ ቢነግሩበት አይሰማ
- የማህበር አሽከር በልቶም አይጠገን ታሞም አይድን
- የማሚቴን እጅ ያላየ በእሳት ይጫወታል
- የማሽላ ዘር ከነአገዳው ቸር
- የማታ ማታ እውነት ይረታ
- የማታ ማታ ጭምት ይረታ
- የማታ ምግብ ለእንግዳ የጠዋት ምግብ ለአገዳ የጠዋት መጠጥ ለእዳ
- የማታ ሩጫ እንቅፋት ትርፉ
- የማታርፍ ጣት አር ጠንቁላ ወጣች
- የማታድግ ውርንጫ እናትዋን ትመራለች
- የማታድግ ጥጃ እናቷ ን ትመራለች
- የማታ አፍ ከጋን ይሰፋል
- የማታድግ ፍየል አምስት ትወልዳለች ልጆቹዋም ያልቃሉ እሷም ትሞታለች
- የማታፍር ድመት ስሜ ገብረማሪያም ነው ትላለች
- የማትሄድ መበለት ዞራ ዞራ ትሰናበት
- የማትረባ ፍየል ዘጠኝ ትወልዳለች ዘጠኙም ያልቁና እሷም ትሞታለች
- የማትሰማው ስድብ ከቀረርቶ ይቆጠራል
- የማነው እህል ያሰኝሃል ክምር የማነው ቤት ያሰኝሃል አጥር
- የማን እርሻ ብለህ እረስ የማን ሚስት ብለህ ውረስ
- የማን ገበሬ ሹሩባ ይሰራል
- የማን ዘር ጎመን ዘር
- የማያልፍለት ዘበኛ ከዋርካ ስር አይጠፋም
- የማያልፍ ነገር የለም ምሽትም በማለዳ ይተካል
- የማያመሽ ባል ቅንድብ ይስማል
- የማያስተኛ ነግረውህ ተኝተው ያድራሉ
- የማያስተኛ ነግረውት ሳይተኛ አደረ
- የማያበላ ቢገላምጥ አያስደነግጥ
- የማያበድር ደመና የማይመልስ ቀማኛ
- የማያበድር ገዳይ የማይመልስ አባይ
- የማያዋጣ ማህበር በጠጅ ይጀመራል
- የማያዋጣ ባል ቅንድብ ይስማል
- የማያውቁት ስድብ ከዘፈን ይቆጠራል
- የማያውቁት አገር አይናፍቅም
- የማያውቁትን መስራት ከጥቅሙ ጉዳቱ ይብስ
- የማያውቁት ምን ያውቅ
- የማያዛልቅ ጸሎት ለቅስፈት
- የማያደርግ እንትን ከቤተክርስቲያን ይቆማል
- የማያድግ ልጅ ባራስ ቤቱ ዳንኪራ ይመታል
- የማያድግ ልጅ ታዝሎ ያፏጫል
- የማያድግ ልጅ ቅዘን ይበዛዋል የማያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል
- የማያድግ ጥጃ ከበሬ ፊት ይነጫል
- የማያግዙ በፈር ያግዛሉ በከንፈር
- የማያጠግብ እንጀራ ከምጣዱ ያስታውቃል
- የማያፍር እንግዳ ባለቤቱን ይጋብዛል
- የማይሆን ነገር የተገላቢጦሽ ያችን ላንቺ ማናለሽ
- የማይመለስ ማር ሹመኛ ይበደረዋል
- የማይመስል ነገር ለሚስትህ አትንገር
- የማይመስል ነገር ለሴት አትንገር
- የማይመቱት ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል
- የማይመቱት ልጅ ቢቆጡት ያለቅሳል
- የማይሰማ ሰው ልቤን አፈረሰው
- የማይሰማ ጆሮ ከጎረቤት ያጣላል
- የማይሰራ አይብላ የማይረዳ አይጥላ
- የማይስማሙ ዝንቦች ጥምብ ይልሳሉ የሚስማሙ ንቦች ማር ይጎርሳሉ
- የማይቀርልህን እንግዳ አጥበቀህ ሳመው
- የማይቀና ባይወለድ የማያስብ ባይነግድ
- የማይቀና ባይወለድ የማያስብ ባይነግድ ይሻላል
- የማይቀና ባይወልድ የማያስብ ባይነግድ
- የማይቀና ባይወልድ የማያስብ ባይነግድ ይሻላል
- የማይበሉት እህል ከአፈር እኩል ነው
- የማይበላ የለም የማይጠግብ ባሰ
- የማይተማመኑ ባልንጀሮች በየወንዙ ይማማላሉ
- የማይተማመኑ ባልንጀሮች እየወንዙ ይማማላሉ
- የማይተማመን ባልንጀራ በየወንዙ ይማማላል
- የማይተች አይፍረድ የማያተርፍ አይነግድ
- የማይቻል ጠላት ስለ ወዳጅ ይቆጠራል
- የማይቻል ጠላት ከወዳጅ ይቆጠራል
- የማይችሉት ድንጋይ ሲያወጡት ደረት ሲያወርዱት ጉልበት ይመታል
- የማይከፍል ባለእዳ የሰጡትን ይቀበላል
- የማይነጋ መስሏት እቋቱ ላይ አራች
- የማይዘልቅ ማህበር በጠጅ ይጀመራል
- የማይዘልቅ ማህበር አሜሪካ ይጀመራል
- የማይዘልቅ ባል ቅንድብ ይስማል
- የማይዘልቅ ጸሎት ለቅስፈት
- የማይደርሱበትን አያኩም
- የማይድን በሽተኛ በጥር እሸት አምጡ ይላል
- የማይድን በሽተኛ በበጋ እሸት አምጡልኝ ይላል
- የማይድን በሽተኛ የማይመለስ ሀጢአተኛ
- የማይድን ባህታዊ ወተት አምጡ የማይድን ፉቅራ ጠላ ስጡ
- የማይገባ ሱሪ የማይበቅል ዘሪ
- የማይጠረጥር ቤቱን አያጥር
- የማይጣሉ መላእክት የማይታረቁ አጋንንት
- የማይጽፍ ደብተራ ክንፍ የሌለው አሞራ
- የማይፈርስ ምሽግ የለም
- የማይፈወስ ድዉይ የማይመለስ ጊጉይ
- የሜዳ ንስንሱን የቤት ጉስጉሱን
- የሜዳ ንስንሱን የቤት ጉዝጓዙን
- የምህረት ጎደሎ የባሪያ ወይዘሮ
- የምላስ ወለምታ ሪፈር የለውም
- የምላስ ወለምታ በቅቤ አይታሽም
- የምላስ ጦር ቢታከም አይድንም
- የምመክተው ጋሻ የምጠጋበት ዋሻ
- የምሮጥበት ሜዳ የምወጣበት ቀዳዳ የለም
- የምስራች በቃሏ መላች
- የምስራች በቃሏ መጣች
- የምበላው ሳጣ ልጄ ጥርስ አወጣ
- የምበላው ሳጣ ማእቀብ ሊጣል ነው
- የምታሸንፈውን ምታ ቢሉት ወደ ሚስቱ ሮጠ
- የምትለብሰው የላት ሻንጣ ቆለፈች
- የምትለብሰው የላት የምትከናነበው አማራት
- የምትመክተው ጋሻ የምትሰወርበት ዋሻ
- የምትሮጥበት ሜዳ የምትገባበት ቀዳዳ
- የምትበላው እህል ከማታየው መሬት ይበቅላል
- የምትታጠቀው የሌላት የምትከናነበው አማራት
- የምትነቃነቅ ግንድና የምትስቅ ሴት ልብ ሩቅ ነው
- የምትኮነን ነፍስ ጎረቤት ያውቃታል
- የምትጠላው ሰው ፈሱ እሆዱ ውስጥ ሳለ ይሸታል
- የምትጠላውን የምትወደውን ሰጥተህ ሸኘው
- የምትጠባ ጥጃ አትጮህም
- የምትጠባ ጥጃ አትጮህም የማይደርሱበትን አያኩም
- የምኞት ፈረስ ልጓም አይገታውም
- የምናውቃትን ክምር በድባብ ሸፈኑዋት
- የምድሩን በአፍ የሰማዩን በመጣፍ
- የምጣዱ ሳለ የእንቅቡ ተንጣጣ
- የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጣጣ
- የምጣዱ እያለ የእንቅቡ ተንጫጫ
- የምጥ መድሀኒቱ አንድ እግር ማስቀደም ነው
- የሞላለት ድመት በሞዝቮልድ ይተኛል
- የሞላለት ድመት ሳንባ ያማርጣል
- የሞተ ልጅ አንገቱ ረጅም ነው
- የሞተ ቢሞት ያለን እንጫወት
- የሞተ አይከሰስ የፈስስ አይታፈስ
- የሞተው ባልሽ የገደለው ውሽማሽ
- የሞተው ባልሽ ገዳዩ ወንድምሽ (ሀዘንሽ ቅጥ አጣ ከቤትሽ አልወጣ)
- የሞተ ያልነበረ ይመስላል ያለ የማይሞት ይመስላል
- የሞተን አትርሳ የወደቀን አንሳ
- የሞተውን አያ ይለዋል
- የሞት በደለኛ አያይዞ በዳኛ
- የሞኝ ለቅሶ መልሶ መልሶ
- የሞኝ ልቅሶ መልሶ መልሶ
- የሞኝ ልጅ ባባቱ ምን ይጫወታል አሉ
- የሞኝ ሚስት በምልክት
- የሞኝ ምስጋና የግንቦት ደመና
- የሞኝ ቄስ ጸሎት ዘወትር አቡነ ዘበሰማያት
- የሞኝ በትር ሆድ ይቀትር
- የሞኝ እጁን ሁለት ጊዜ እባብ ነከሰው አንድ ጊዜ ሳያይ ሁለተኛው ሲያሳይ
- የሞኝ ዘመድ ያፍራል
- የሞኝ ዘፈን ሁልጊዜ አበባዬ
- የሞኝን ጠላ በለው በአንኮላ
- የሞኝ ጀርባ ሲመታ ለአዋቂ ይስማማል
- የሞኝን ጥርስ ብርድ ፈጀው
- የሞኝ ገበሬ እርሻ በሰኔ
- የረጋ ወተት ምርጫ ይደገምለታል
- የረጋ ወተት ቅቤ ይወጣዋል
- የራሷ ሲያርባት የሰው ታማስላለች
- የራስህን አትበላ ገንዘብ የለህ የሰው አትበላ ዐመል የለህ
- የራሷ አሮባት የሰው ታማስላለች
- የራስዋ እያረረባት የስው ታማስላለች
- የሰማ ያውራ ያየ ይናገር
- የሰካራም ግጥም ሁልጊዜ ቅዳ ቅዳ
- የሰው አመሉ ዳውላ ሙሉ መቼ ያስታውቃል አብረው ካልዋሉ
- የሰው አገሩ ምግባሩ የከብት አገሩ ሳሩ
- የሰው አገር ዝናብና የእንጀራ አባት አይምታህ
- የሰው እንጂ የቃል ውሸት የለም
- የሰው ወርቅ አያደምቅ
- የሰው ፈላጊ የራሱን ያጣል
- የሴት ምራቋ ወፍራም ነው
- የሴትን ብልሀት የጉንዳንን ጉልበት ይስጥህ
- የሴት አገር ባልዋ
- የሴት አጭር ወይዘሮ የወንድ አጭር አውራ ዶሮ
- የሴት ጠጭና የአህያ ፈንጪ አያድርስ ነው
- የሴት ልባም ያህያ ቀንዳም
- የሴት ልቧ እንጂ ሆዷ አይመርጥም
- የሴት መልኳ ምንድር ነው እጅዋን ታጥባ እንኩ ስትል ነው
- የሴት መጠጥ ደፋር የወንድ አይን አፋር
- የሴት ምክር ማሰሪያው አሽከቴ
- የሴት ምክር የሾህ አጥር
- የሴት ሞቷ በማጀቷ
- የሴት ረዥም የማቅ ውዥምዥም እንብዛም አያስጎመጅም
- የሴት ስካር ያጭር ሰው ኩራት አይታይም
- የሴት ብቻዋን ሂያጅ የቄስ አርፋጅ ሁለቱም ነገር ወዳጅ
- የሴት አመዳም የአህያ ሆዳም
- የሴት አመዳም የአሮጌ ሆዳም
- የሴት አገሩዋ ባሏ
- የሴት አገሩዋ ባሏ ማደሪያዋ አመሏ
- የሴት እንግዳ የመርፌ ጎዳ
- የሴት ቀበጥ የበቅሎ መድን ለመሆን ገበያ ትወጣለች
- የሴት ትንሽ የለውም
- የሴት ጉልበት ምላሱዋ
- የሴት ጠጪ የግመል ፈንጪ
- የሴት ዘበናይ የፊትዋን እንጂ የኋላዋን አታይ
- የሽማግሌ ፍቅር እና የክረምት አበባ አንድ ነው
- የሽሮ ድንፋታ እንጀራው እስኪመጣ ነው
- የሽሮ ድንፋታ እስኪቀርብ ድረስ
- የቀረ ይቀራል እንጂ ቀርቅር ብዬ አልጣራም
- የቀበሮ ባህታዊ የለም
- የቀበጠች አይጥ በድመት ጭራ ዘፈን ትዘፍናለች
- የቀበጠች አይጥ የድመትን አፍንጫ ታሸታለች
- የቀበጠ እንትን ቅቤ ቀቡኝ ይላል
- የቀበጡ እለት ሞት አይገኝም
- የቀን ጠማማን ሚዳቆ አትዘለውም
- የቀጣፊ እንባ ባቄላ ያክላል
- የቂጥ አጋሚ ፈስ ነው ወሮታው
- የቃመ ተጠቀመ ያልቃመ ተለቀመ
- የቃርያ እልክ አወፈረኝ
- የቄስ ጠበቃ ዳዊት ይጠቅሳል
- የቅርብ ጠበል የልጥ መንከሪያ ይሆናል
- የቅድሙ በዛ ያሁኑ ተንዛዛ
- የቆጡን አወርድ ብላ መሰላል አመጣች
- የቆጡን አወርድ ብላ ቤቷን ከርቸሌ አደረገች
- የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷን ጣለች
- የቆጡን አወርድ ብላ የብብቷ ጸጉር ታየ
- የቆጡን አወርድ ብላ የጣራውን አወረደች
- የበላ በለጠኝ የሮጠ አመለጠኝ
- የበላ ባይማታም ዱላ ይችላል
- የበላችው ያገሳታል በላይ በላዩ ያጎርሳታል
- የበላና የተደገፈ ወድቆ አይወድቅም
- የበሰበሰ ዝናብ አይፈራም
- የቡና ስባቱ መፋጀቱ
- የባለጌ ባለሟል ቂጥ ገልቦ ያያል
- የባሪያ ደግ የቁልቋል ዘንግ የለውም
- የባስ አለ ሚስትህን አትፍታ
- የባሰ አለና አገርህን አትልቀቅ
- የቤቴ መቃጠል ለትኌኔ በጀኝ! አለች አሉ!
- የባህር ዳር ሲታረስ ጓጉንቸር ሆድ ይብሳታል
- የባልቴት ወብራ የክረምት ብራ
- የባል ደግነቱ ውሽሜን መርሳቱ
- የባል ደግነቱ ውሽምን መርሳቱ
- የባሰ አለና አገርህን አትልቀቅ
- የባእድ ፍቅር የውሀ ጌጥ አንድ ነው
- የቤት ቀጋ የደጅ አልጋ
- የተለጎመ በሬ ከቀንበሩ ቢያመልጥ ቢላዋ ይጠብቀዋል
- የተመረረ ድሀ ይገባል ከውሀ
- የተማረና ታጥቦ የተቀመጠ ብርጭቆ ፈላጊ አያጣም
- የተጠማ ከፈሳሽ የተጠቃ ከነጋሽ
- የተናቀ ሰፈር በአህያ ይወረራል
- የተናቀ ብእር ይገነፍላል
- የተናቀ እንትን ያስረግዛል
- የተናቀ ያስረግዛል
- የተናገሩት ከሚጠፋ የወለዱት ይጥፋ
- የተናገሩት ከሚጠፋ ጽፎ ማስቀመጥ
- የተናጠ ወተት ቅቤ ይወጣዋል
- የተንቀለቀለች አፍሳ ለቀመች
- የተንቀዠቀዠች ውሻ ላፏ ሊጥ ለወገቧ ፍልጥ አታጣም
- የተከፋ ተደፋ
- የተገነዘች ነፍስ የተለጎመች ፈረስ
- የትም ፍጪው ዱቄቱን አምጪው
- የት ትሂጃለሽ ቢላት በታክሲ አለች
- የት ትሂጃለሽ ቢሏት በታክሲ
- የት አውቅሽ ብሎ አጥብቆ ሳመኝ
- የቸኮለ አፍስሶ ለቀመ
- የቸገረው እርጉዝ ያገባል ስትወልድበት ገደል ይገባል የባሰበት እመጫቷን
- የቸገረው ዱቄት ከንፋስ ይጠጋል
- የነሀሴ ውሀ ጥሩ ነው የሚጠጣው የለም የድሀ ነገር ፍሬ ነው የሚሰማው የለም
- የነብርን ጭራ አይዙም ከያዙም አይለቁም
- የነቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ሰንበሌጥ
- የነቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው ብሎኬት
- የነቶሎ ቶሎ ቤት ግድግዳው አስቤስቶስ
- የነቶሎ ቶሎ ቤት ግርግዳው ጭራሮ
- የነቶሎ ቶሎ ቤት በሊዝ ተሸጠ
- የነቶሎ ቶሎ ቤት ዘበኛው ቶሎሳ
- የነፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል
- የእናት እርግማን ወለምታ ነው
- የእናት ሞትና የግር እሳት እያደር ያንገበግባል
- የእናት ልጅ ቢጣላ እውነት ይመስላል ለሌላ
- የእናት ልጅ የሌለው አይበላ ሽሮ የሌለው ምንቸት አይፈላ
- የናት ሆድ ዥንጉርጉር
- የናት ሆድ ዥንጉርጉር ወላጅ ቀይና ጥቁር
- የናት ልጅ የጎን አሳጅ
- የናት ሞትና የድንጋይ መቀመጫ እያደር ይቆረቁራል
- የናትን ክፋት የደመናን ውሀ ጥማት ባለቤቱ ያውቀዋል
- የናት ድሀ የለውም
- የንግዳ አይን አፋር ባለቤቱን ይጋብዛል
- የአህያ ባል ከጅብ አያስጥልም
- የአህያ "እቃው" ሆዱ ውስጥ ነው
- የአሳ ግማቱ ከወደ አናቱ
- የአሳ ግማቱ ከወደ ጭንቅላቱ
- የ10 አለቃዬ ምክትሌ ሆይ አንተም እንደ መቶ ትኮራለህ ወይ
- የአባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ
- የአባይ ልጅ ኩሬ
- የአባይን ልጅ ወዳቂ የዞማ ልጅ ሳቂ
- የአባይን ልጅ ውሀ ጠማው የላጭን ልጅ ቅማል በላው
- የአንዱ ሀገር ዘፈን ለአንዱ ሀገር ለቅሶ ነው
- የአንድ ቀን መዘዝ ያለ ዘጠኝ ወር አይመዘዝ
- የአይጦች አድማ ምርጫ እስኪደርስ ነው
- የአገሬ ሰዎች ተጠንቀቁ የሰረቁት ስጋ ያስይዛል መረቁ
- የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም
- የአፍ ወለምታ በፖሊስ ይታሻል
- የእህል ክፉ አጃ የሳር ክፉ ሙጃ የነገር ክፉ እንጃ
- የእህል ጣም በጉረሮ የነገር ጣም በዦሮ
- የእብድ ገላጋይ ድንጋይ ያቀብላል
- የእናት ሞትና የድንጋይ መቀመጫ እያደር ይቆረቁራል
- የእንጨት ምንቸት እራሱ አይድን ሌላ አያድን
- የክፉ ሰው ተዝካር ውሀ ያስወስዳል በህዳር
- የክረምት ጥማትና የመከር ጊዜ ረሀብ አለባለቤቱ የሚያውቀው የለም
- የወረት ውሻ ስሟ ወለተኪሮስ
- የወረቀት ላይ ነብር የተግባር ስንኩል (አንሁን)
- የወንድ አልጫ የእንዶድ ሙቀጫ
- የወንድ አጭር ዝንጀሮ የሴት አጭር ወይዘሮ
- የወንድም ልጅ ባይወልዱትም ልጅ
- የወንዶች ባል አይተህ ማር
- የወንድ ልጅ ሞት ያደረገውን የዘነጋለት
- የወንድ አልጫ እንዶድ ሙቀጫ
- የወንድምህ ጢም ሲላጭ ጢምህን ውሀ አርስ
- የወጣ ቢገባ የገባ ይወጣል
- የወደቀ ዛፍ መንገዱን ዘጋ
- የወደደና የአበደ አንድ ነው
- የወደዱትን ሲያጡ የጠሉትን ይቀላውጡ
- የወጋ ቢረሳ የተወጋ አይረሳም
- የወጋ ቢረሳ ፖሊስ ያስታውሳል
- የወጌሻ ልጅ ዛፍ ላይ ያድራል
- የወደቀ ዛፍ ምሳር ይበዛበታል
- የዋኘ ይሻገራል የሰራ ይከብራል
- የውሀ ሽታ የእባብ ፍለጋ የለውም
- የውሀ ውሀ ምን አለኝ ቀሀ
- የውሀ ጡር በእድፍ ያስታጥባል
- የውድማ ዘንዶ ይቀጠቀጣል እንደበረዶ
- የዘመድ ዘመድ ወንዝ ያሻግራል
- የዘመድ ጥል የስጋ ትል
- የዘሬን ብለቅ ይቆማምጠኝ አለ ቆማጣ
- የዘንድሮውስ ብርድ ቆማጥ ያሳቅፋል
- የዘገነ አዘነ ያልዘገነ አዘነ
- የዝንጀሮ ለቅሶ መልሶ መላልሶ
- የዝንጀሮ ስብሰባ በውሻ ጩኸት ይበተናል
- የዝንጀሮ ንጉስ እሱ ይከምር እሱ ያፈርስ
- የየጁ ቄስ አንደዜ ቅኔው ቢጎልበት ቀረርቶ ሞላበት
- የየጁ ደብተራ ቅኔ ቢያልቅበት ቀረርቶ ጨመረበት
- የደላው ሙቅ ያኝካል
- የደላው ወርቅ ያስራል
- የደመና ውሀ ጥምና የእናት በደል አይታወቅም
- የደንቆሮ ለቅሶ መልሶ መልሶ
- የደንቆሮ ለቅሶ መልሶ መላልሶ
- የደንቆሮ ሰርግ በሽብሸባ ያልቃል
- የድመት ልጅ መቧጨሯን አትረሳም
- የድሮው ኮንጎዬ ካሁኑ ስቶኪንጌ ተሻለኝ
- የድፍድፍ ኩራቱ ውሀ እስኪገባበት
- የድፍድፍ ኩራቱ ውሀ እስኪገባ ነው
- የጅብ ችኩል ቀንድ ይነክሳል
- የጅብ ችኩል ቶሎ ያፏጫል
- የገበያ ሽብር ለሌባ ሰርጉ ነው
- የገበያ ግርግር ለሌባ ይበጃል
- የገንዘብን ነገር ካሰላሰሉት አባ ሀናም ሞቱ እንደጨበጡት
- የገጣጣ ሚስት ችግሩን አልቅሶ ካልነገራት አይገባትም
- የጉልበት ግማሹ አፍ ነው
- የጉድ አገር ገንፎ በጣም ይጣፍጣል
- የጉድ አገር ገንፎ እያደር ይፋጃል
- የጉሮሮን መታነቅ ያይን መደንቆል ያስጥለዋል
- የጎረምሳ መልኩ እንጂ አነጋገሩ አያምርም
- የጎጃም አዝመራ ሽንብራ ነው አሉ እኛም እንዳንበላ ተነቀለ አሉ
- የጊዜ ግልባጭ እግር ሰውነት ያካል
- የግመል ሽንት ይመስል ሁሌ ወደኋላ
- የግፍ ግፍ በእንቅርት ላይ ጆሮ ደግፍ
- የጥቅምት ቀን እና የቆንጆ ሳቅ አያታልልህ
- የጥንት ወዳጅክን በምን ሽኘኸው በሻሽ አዲሱ እንዳይሽሽ
- የጨለማ አፍጣጭ የእውር ገልማጭ
- የጨለማ አፍጣጭ የእውር ገልማጭ አይረባም
- የጨረቃ ሂያጅ የምስክር ፈራጅ
- የጨረቃ ሂያጅ የምስክር ፈራጅ
- የጨረቃ ንጋትና የእውር ሞት አይታወቅም
- የጨርቅ ነጩ የበራ ልጩ
- የጨነቀው እርጉዝ ያገባል
- የጨነቀው እርጉዝ ያገባል ስትወልድበት ገደል ይገባል
- የጨነቀው ይዋጋል ያልደረሰበት ያወጋል
- የጨዋ ልጅ ሁሉ አርግዟል ሆዱ
- የጨዋ ልጅ ሁሉ አርግዟል በሆዱ
- የጨዋ ልጅ ሲያዝን አሳ በወንዝ ይመክን
- የጨዋ ልጅ ሲያዝን ውሀ በወንዝ ይመክን
- የጨዋ ልጅ ሲፋታ ይጋባ ይመስላል
- የጨዋ ልጅ ከከተማ የድሀ ልጅ ከውድማ
- የጨዋ ልጅና ቅል ተሰባሪ ነው
- የጨው ገደል ሲናድ ሞኝ ይስቃል ብልህ ያለቅሳል
- የጨው ገደል ሲናድ ብልህ ያለቅሳል ሞኝ ይልሳል
- የጨውን ባለእዳ በጨው ቢያባብሉት ጨዌን ማለቱ አይቀርም
- የጨጌ ከብት በየወገኑ ይከተት
- የጫማ ጠጠርና የእንጀራ ልጅ እያደር መቆርቆሩ አይቀርም
- የጫማ ጠጠርና የእንጀራ እናት እያደር መቆርቆሩ አይቀርም
- የፈላ ጠጅ የደረሰ ልጅ
- የፈረሰኛ ማቅ ለባሽ የሴት ትምባሆ ቀማሽ
- የፈረሰኛ ማቅ ለባሽ የሴት ትምባሆ ጎራሽ
- የፈረሰ አልጋ የተሸበረ ዜጋ
- የፈረንጅ አሽከር ነጭ ለባሽ ሳህን አመላላሽ
- የፈሩት ይደርሳል የጠሉት ይወርሳል
- የፈሪ ዱላ ሰላሳ ነው
- የፈሪ ዱላ አያዳግምም
- የፈሪ በትር አስር
- የፈሪ ገዳይነት ለማታ
- የፈሰሰ ውሀን ማቆር ይጠቅማል
- የፈሰሰ ውሀ አይታፈስ
- የፈሰሰ አይታፈስ የሞተ አይመለስ
- የፈሲታ ተቆጢታ
- የፈሳ የጥጋብም አይደል ሲረሳ
- የፈስ ማደናገሪያው ዳባ
- የፈስ ማደናገሪያው ዳቦ
- የፈቷት ሴት ያጠቡት ወጪት የወጡበት ቤት አንድ ነው
- የፈቷት ሴት ያጠቡት ወጪት የወጡበት ቤት አንድ ናቸው
- የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል
- የፊተኛውን አሳረርሽ ቢሏት የኋለኛውን ጥሬ አወጣች
- የፊት መሪ የኋላ ቀሪ
- የፊት ምስጋና ለኋላ ሀሜት ያስቸግራል
- የፊት እድፍ በመስታወት የሀጢአት እድፍ በካህናት
- የፊት ከብት የእጅ ወረት
- የፊት ወዳጅህን በምን ቀበርከው በሻሽ የኋለኛው እንዳይሸሽ
- የፊት የፊቱን አለ ጓያ ነቃይ
- የፋቂ ልጅ ሰነፍ አንዱን ሳይፍቅ አንዱን ይዘፍቅ
- የፋቂ ሰነፍ አንዱን ሳይፍቅ አንዱን ይዘፍቅ
- የፋቂ ቆንጆ ቡድነቱን አይተውም
- የፌጦ መስሎሽ ሰናፍጭ ትቀምሽ
- የፌጦ ብቅል የብሳና ጌሾ የተልባ አሻሮ ይህን ጠምቆ ለማ የሰው ነገር ለማይሰማ
- የፍቅር ጣእሙ በመሳለሙ
- የፍቅር ጣእሙ አልጋ ላይ
- የፍቅር ጣእሙ ተቃቅፈው ሲተኙ
- የፍቅር ደስታው ከሴት ጭን መሃል ይገኛል ፈልጉ
- የፍየል ልጁን የሌባ እጁን
- የፍየል ጅራት ቂጥ አይከድን ከብርድ አያድን
- የፍየል ጅራት ብልት አይከድን ከብርድ አያድን
- የፍየል ጅራት ከብርድ አያድን ብልት አይከድን
- የፍየል ጅራት ከብርድ አያድን አፍረት አይከድን
- የፍየል ጅራት ከብርድ አያድን እፍረት አይከድን
- የፍየል ጭራና የሰው ሀሳብ ሁልጊዜ ወደ ላይ ነው
- የፍጅት ወራት እሳት በወንፊት
- የፖሊስ ዘመድና የቤንዚን አመድ
- የፖሊስ ዘመድ የቤንዚን አመድ የለውም
- ዪዪዪዪዪ .........አለ !አምቡላንስ (የቁጭት አባባል)
- ያህያ ስጋ አልጋ ቢሉት አመድ
- ያህያ ባል ቀለበት አያስርም
- ያህያ ባል ከጅብ ጉቦ በላ
- ያህያ ባል ከዥብ አያስጥል
- ያህያ ውሀ ጠጭ ሳይታወቅ መጣጭ
- ያህያ ልጅ ጥሎ ይረግጣል የፈረስ ልጅ ጥሎ ይደነግጣል
- ያህያ ስጋ ካልጋ ሲሉት ካመድ
- ያህያ ካልጋ ሲሉት እምድር
- ያህያ ስጋ ውርደተኛ አልጋ ላይ ቢያኖሩት እመሬት ይተኛ
- ያህያ ቀበጥ ከጅብ ጡት ይጣባል
- ያህያ ባል ከጅብ አያስጥል
- ያህያ እንግዳ የጅብ እራት ነው
- ያህያ ደግነት ጭነት ማብዛት
- ያህያ ውሀ ጠጭ ሳይታወቅ መጣጭ
- ያህያ ጀላፋ መስክ ያጠፋ የሹም ዘፋፋ አገር ያጠፋ
- ያህያ ፍለጋና የጥሬ እራት በግዜ ነው
- ያህያ ፍሪዳ የእባብ ለማዳ የለውም
- ያለባለቤቱ አይነድም እሳቱ
- ያለአንድ የላት በዘነዘና ትነቀስ
- ያለውን የሰጠ ንፉግ አይባልም
- ያለውን የወረወረ ንፉግ አይባልም
- ያለአዋቂ ተራች የራሱን አመልካች
- ያለ ዝናብ ነጎዳ ያለ ብድር እዳ
- ያለ ወጉ አህዮች ተዋጉ
- ያለ ባለቤቱ አይነድም እሳቱ
- ያለ የሚኖር ይመስላል የሞተ ያልነበረ ይመስላል
- ያለ ይበዛል (አለ ወፍጮ)
- ያለህ ምዘዝ የሌለህ ፍዘዝ
- ያለ መሰረት ቤት ያለ ትምህርት እውቀት የለም
- ያለ መከራ አይገኝም እንጀራ
- ያለ መከራ ጸጋ ያለ ድካም ዋጋ አይገኝም
- ያለ መጥረቢያ እንጨት ሰባሪ የቆማጣ ዘንግ ወርዋሪ
- ያለ ምቀኛ አይገኝ ፍቅረኛ
- ያለ ሴት ምን ያደርጋል ቤት
- ያለ ሴት ቤት ያለበሬ መሬት
- ያለ ስራ መብል ያለዳኛ ውል
- ያለ ስራ መብል ያለዳኛ ውል አይቻልም
- ያለ ስራ አይበላ እንጀራ
- ያለ ስራ አይበላ እንጀራ አለባል ቆጥ አይሰራ
- ያለስፍራው የተስበረ ሲጠግኑት አስቸገረ
- ያለስፍራው የተስበረ ሲጠግኑት ያስቸግራል
- ያለ በሬ ምን ያደርጋል ገበሬ
- ያለበት ይብላላበት
- ያለበት ይጉላላበት
- ያለ ባለቤቱ አይነድም እሳቱ
- ያላባቱ ቢዛቁን አባክኖ ያባክን
- ያለአቻ ጋብቻ ቆይ ብቻ ቆይ ብቻ
- ያለ እዳው መዝመት ዋ ብሎ መቅረት
- ያለ እዳው ዘማች ዋ ብሎ መቅረት
- ያለ ክንፍ መብረር ያለ ስራ መክበር
- ያለው ሳይዋደድ ለሞተው መናደድ
- ያለው ይምዘዝ የሌለው ይፍዘዝ
- ያለው ይመዛል የሌለው ይፈዛል
- ያለው ይበላል የሌለው ያፈጣል
- ያለውን ካልሰቱ በስም አይበሉ
- ያለ ዘዴ ጋሻ እንቅብ ነው
- ያለ ዘመድ ነግሶ ያለ አቡን ቀስሶ
- ያለ ዝናብ ነጎዳ ያለብድር እዳ
- ያለ የሚኖር ይመስላል የሞተ ያልነበረ ይመስላል
- ያለ ጊዜው የተወለደ ልጅ አባቱን ጥሎ አያቱን ያስረጅ
- ያለ ጎረቤት ቡና ያለ ሙያ ዝና
- ያለ ጎታ ደረባ ያለልብስ ካባ
- ያለ ጎተራ ደረባ ያለልብስ ካባ
- ያለ ጎታ ደረባ ምንድን ነው
- ያለ ይበዛል አለ ወፍጮ
- ያለ ጥርስ ቆሎ ያለ ጓድ አምባጓሮ
- ያለ ጨው በርበሬ ያለሞፈር በሬ
- ያለ ፊቱ አይቆርስ ያለባለቤቱ አይወርስ
- ያለ ፍርድ ማሰር በፈጣሪ ማማረር
- ያለ ፍቅር ሰላም ያለ ደመና ዝናብ
- ያለ ፍቅር ጸሎት ያለ እንጨት እሳት
- ያሉሽን በስማሽ ኖርዌይ ባልመጣሽ
- ያሉሽን በሰማሽ ገበያ ባልወጣሽ
- ያላማረ ሰርግ ጉልቻው ይሽረፋል
- ያላዋቂ ሳሚ ንፍጥ ይለቀልቃል
- ያላዩት አገር አይናፍቅም
- ያላረፈች ምላስ ሸማ ትልስ
- ያላረፈች እግር ከዘንዶ ጉድጓድ ትገባለች
- ያላሰብከውን አግኝ መረገመም ምርቃን አይደል
- ያላስደጉት ውሻ ቤት ዘግተው ቢመቱት ዞሮ ይናከሳል
- ያላባቱ ቢዛቁን አባክኖ ያባክን
- ያላዋቂ ሳሚ ምላስ ይነክሳል
- ያላወቁ አለቁ
- ያላዞረ ሲዞር አደረ
- ያላዋቂ ቆራሽ ማእድ አበላሽ
- ያላየ ልጅ ዳቦ ፍሪዳው
- ያላዩት አገር አይናፍቅም
- ያላዩት ነገር ክፉ አይደለም መልካምም አይደለም
- ያልሰማ ጆሮ ከጎረቤት ያጣላል
- ያልበላህን አትከክ
- ያልበላ ዳኛ አያሟግት ያልጠጣ እንግዳ አይጫወት
- ያልተመካ ግልግል ያውቃል
- ያልተማረ ዋናተኛ ከዳኛ ፊት እንቢተኛ
- ያልተነካ ግልግል ያውቃል
- ያልተገላበጠ ያራል
- ያልታደለ ቆዳ ሲላፋ ያድራል
- ያልታደለ በረዶ ከድንጋይ ላይ ያርፋል
- ያልታደለች ከንፈር ሳትሳም ታድራለች
- ያልታደለ ከንፈር ሊፕስቲክ ያበዛል
- ያልታደለ ከንፈር ሳይሳም ያረጃል
- ያልነበረ ያፈርሳል ቀዳዳ ያፈሳል
- ያልወለደ አጋድሞ አረደ
- ያልወለድኩት ልጅ አባባ ቢለኝ ሆዴን ባርባር አለኝ
- ያልወለድኩት ልጅ አባዬ ቢለኝ አፌን ዳባ ዳባ አለኝ
- ያልጠረጠረ ተመነጠረ
- ያልሟል ይተረጉሟል
- ያልሞላ ተርፎ አይፈስም
- ያልሞተና ያልተኛ ብዙ ይሰማል
- ያልሰማ ጆሮ ከጎረቤት ያጣላል
- ያልሰማ ጥኑ ነው ባልሽ ወዳጄ ነው
- ያልሰሙት ነገር ክፉም መልካምም አይደለም
- ያልሰጡት ተቀባይ ያልጠሩት አቤት ባይ
- ያልሳሉት አይላጭ ያላዩት አይቆጭ
- ያልቆረጠ እግብ አይደርስም
- ያልበሉት እዳ ያልጠሩት እንግዳ
- ያልበላ ሬሳ ያልለበሰ እንሰሳ
- ያልበላ ዳኛ አያሟግት ያልጠጣ እንግዳ አያጫውት
- ያልበላኝን ቢያከኝ አይገባኝ
- ያልበጀው እሳት ፈጀው
- ያልተማረ አይጸድቅ ያልተወቀረ አያደቅ
- ያልተማረ አይምርም ያልተወቀረ አያደቅም
- ያልተመታ ልጅ ሲቆጡት ያለቅሳል
- ያልተማረ ዋናተኛ ከዳኛ ፊት እንቢተኛ
- ያልተረታ አይረታ ያልጠገበ አይማታ
- ያልተሾመ አያዝ ያልቀሰሰ አያናዝዝ
- ያልተሾመ አያዝ ያልቀሰሰ አይናዝዝ
- ያልተቀጣ ልጅ ቢቆጡት ያለቅሳል
- ያልተቀጣ ልጅ ያልታጠበ እጅ
- ያልተነካ ግልግል ያውቃል
- ያልደረሰበት ግልግል ያውቃል
- ያልተገላበጠ ያራል
- ያልተገላበጠ ያራል ያለ ይበዛል አለ ወፍጮ
- ያልተገራ ፈረስ ይጥላል በደንደስ
- ያልተጠናከረ ድንገት ተሰበረ
- ያልተፈተነ ወዳጅ ያልተተኮሰ ሸክላ
- ያልተፈተነ ወዳጅ ያልተተኮሰ ሸክላ ነው
- ያልታረመ አፍ ከዋንጫ ይሰፋል
- ያልታየ እንጂ ያልተሰማ ያልተደረገ እንጂ ያልተባለ ነገር የለም
- ያልታደለ በረዶ ከድንጋይ ላይ ያርፋል
- ያልታደለ ከንፈር ሳይሳም ያረጃል
- ያልታደች ወፍ አይኗ በጥቅምት ይጠፋል
- ያልነበረ ያፈርሳል ቀዳዳ ያፈሳል
- ያልወለደ አንጀት ጨካኝ ነው
- ያልወለደ አይነሳ የሽምብራ ማሳ
- ያልወለደ አጋድሞ አረደ
- ያልወለዱ ሁሉ ጊደሮች ይባላሉ
- ያልወለደኩት ልጅ አባባ ቢለኝ አፌን ዳባ ዳባ አለኝ
- ያልወለደኩት ልጅ አባ አባ ቢለኝ አፌን ዳባ ዳባ አለኝ
- ያልዘሩት አይበቅልም
- ያልዘራሁት በቀለብኝ ዱባ ያልኩት ቅል ሆነብኝ
- ያልዘራውን የሚበላ ዝንጀሮ ነው
- ያልገደለ በሽታ ምስጋና የለውም
- ያልገደለ ዘማች ያልወለደ አማች
- ያልጋ ሴሰኛ ሶስት ያስተኛ
- ያልጠረጠረ ተመነጠረ
- ያልጠሩት መካሪ ያልሾሙት ፊታውራሪ
- ያልጠሩት ሰርገኛ በትረኛ
- ያልጫ ድንፋታ እንጀራ እስኪቀርብ
- ያልጫ ድንፋታ እንጀራ እስኪቀርብ ነው
- ያልፋል እስኪያልፍ ያለፋል
- ያመል ትንሽ ይጥላል በጭራሽ
- ያመሰገኗት ቅል ባፏ ታፈሳለች
- ያሞሌ ጥጃ በወንዙዋ ትናፋ
- ያመነታ ተመታ
- ያመኑት ሲከዳ ይቀላል እዳ
- ያመኑት ፈረስ ጣለ በደንደስ
- ያመጣሁት ውሻ ነከሰኝ ያነደድኩት እሳት ጠበሰኝ
- ያመጣል አንበሴ ይበላል ኮሳሴ
- ያማከሩት ዳኛ ያግዛል የመተሩበት እጅ ይወዛል
- ያምላክን ነገር ምኑን አውቀሽው ወይ እኔ እበላው አንቺ አርመሽው
- ያምላክን ነገር ስንቱን አውቀሽው ወይ እኔ እበላው አንቺ አርመሽው
- ያምራል ብለው ለነብር ልጅ አይድሩም
- ያምራል ብለው ከተናገሩት ይከፋል ብለው ያስቀሩት
- ያምራል ብለው ከመናገር ይከፋል ብሎ መተው
- ያምራል ብሎ ይሸልሟል ያውቃል ብሎ ይሾሟል
- ያምሩዋል ይታደሏል
- ያምና ሞኝ ዘንድሮም ደገመኝ
- ያምናውን ዘንድሮ የአዋጁን በጆሮ
- ያሞላቀቁት ልጅ አይሆንም ወዳጅ
- ያሞሌ ጥጃ በወንዙዋ ትነፋ
- ያረረበት ያማስል
- ያረሮ ልጅ ጠለፋ
- ያረሰ እንደ ልቡ ጎረሰ
- ያረገዘች ታስታውቅ ከደረቷ ትታጠቅ
- ያረጀን ሹም ገባር ይከሰዋል ያረጀን ጅብ አህያ ይጥለዋል
- ያራስ ክፉ መበለት ያደጋ ክፉ እሳት
- ያራሷን በርጉዙዋ
- ያራሷን ገንፎ እርጉዙዋ ውጣ ሞተች
- ያርጋጅ አናጋጅ
- ያርጋጅ አንጓጅ
- ያሳደግሁት ውሻ ነከሰኝ ያነደድሁት እሳት ጠበሰኝ
- ያስረ ይፈታል የሰጠ ይረታል
- ያስለመዱት ሰው ሁልጊዜ እጅ ያያል
- ያሰቡት አይገድም ጎኔን ላርገው ጋደም
- ያሳደግኋት ጥጃ አለችኝ በርግጫ
- ያሳደኩት ውሻ ነከሰኝ ያነደድኩት እሳት ጠበሰኝ
- ያስታርቀኛል ሙተራ እያንዳንዱ እየኮራ
- ያሽላል ያሉት ኩል አይን ያጠፋል
- ያቀረቡልህን ጉረስ የተረፈህን መልስ
- ያበረ ወገኑን አስከበረ
- ያበራሽን ጠባሳ ያየ በእሳት አይጫወትም
- ያ በሬ ባላገደደ ያ በሬ ገደል ባልገባ
- ያ በሬ ባገደደ ያ በሬ ገደል ገባ
- ያ በሬ ባገደደ ያ በሬ ገደል ገባ ያበጠው ይፈንዳ
- ያበደ ለኑሮው የፈረደ ለጉሮሮው
- ያበደች ጋለሞታ እናቷን ትመታ
- ያበደና የወደደ አንድ ነው
- ያበጠው ይፈንዳ
- ያባ ሆይ መቋሚያ ላዩ ባላ ታቹ ዱላ
- ያባ ጎፍናኔ ቤቱ በሪድ
- ያባትህ ቤት ሲዘረፍ አብረህ ዝረፍ
- ያባት ወዳጅ የድንጊያ ገድጋጅ
- ያባቱን ቢሰጡት ህይወቱ ያባቱን ቢነሱት ሞቱ
- ያባቱን ያገኘ ህይወቱ ያባቱን ያጣ ሞቱ
- ያባት ልጅ የደንደስ ስጋ
- ያባት ልጅና ጆሮ አንድ ነው
- ያባት ምርቃት አያስገባም ጥቃት
- ያባት ልጅ የማድጋ ዶሮ ነው
- ያባት ልጅ የማድጋ ዶሮ አንድ ነው
- ያባት ሞቱን አይወዱ ረጃቱን አይሰዱ
- ያባት ሞቱን አይወዱ ረድኤቱን አይሰዱ
- ያባት ሲቀር ምሰህ ቅበር
- ያባት አገር ከሞት አያስጥልም
- ያባት እርግማን ሲዳሩ ማልቀስ
- ያባት እዳ ለልጅ ያፍንጫ እድፍ ለእጅ የወፍጮ እዳ ለመጅ
- ያባት ወርቅ ባለዝና እህል ለቀጠና
- ያባት ያምራል የባእድ ያናግራል
- ያባት ያምራል የባእድ ያኖራል
- ያባት ደግ ይደልላል ያባት ክፉ ለእንጀራ ልጅ ያደላል
- ያባትህ ቤት ሲበዘበዝ አብረህ ዝረፍ
- ያባትህና የናትህ ወገኖች ሲጣሉ ጥግህን ያዝ
- ያባያ ልጅ ወዳቂ ያራኝ ልጅ አጥባቂ
- ያባያ እናት አትታረድም
- ያባያ ወንድሙ አይታረድም
- ያባይ ምልክቱ አንደበቱ የገዳይ ምልክቱ ሽልማቱ
- ያባይ እንባ አይታገድም
- ያባይን እናት ውሀ ጠማት
- ያባይ ውሀ ተለያየ ሲሉ ተገናኘ
- ያባይን ልጅ ውሀ ጠማው የላጭን ልጅ ቅማል በላው
- የአብሮ አደግ ልብ በቁና ይሰፈራል
- ያብዬን እከክ ወደ እምዬ ላከከ
- ያብዬን እከክ ወደ እምዬ ልክክ
- ያተር ክምር የጭሰኛ ክብር
- ያናጢን ልጅ ጅብ በላው የላጭን ልጅ ቅማል ፈጀው
- ያንበሳ ልመና ጋማ ይዞ ነው
- ያንበሳ ልመና ጋማ ይዞ የቄስ ልመና አናዞ
- ያንበሳ ማላጅ ጋማ ይዞ ጅብን መውጋት አህያን ተጎዝጉዞ
- ያንበሳ ማላጅ ጋማ ይዞ ጅብን መውጋት አህያን ተገን ይዞ
- ያንበሳ አማላጅ ጋም ይዞ ጅብን መውጋት አህያን ተገን ይዞ
- ያንበሳ ኮርዲዳና የጨዋ ልጅ ሞግዚት ከመሆን ይሰውርህ
- ያንበሳ ገራም ይውላል ከላም
- ያንተን የሚመስል የኔም አለኝ ቁስል
- ያንቺን አትበይ ገንዘብ የለሽ የሰው አትበይ ምግባር የለሽ
- ያንካሳ ልቡ ኢየሩሳሌም
- ያንዱ በሬ ሲሞት ላንዱ አጋዘኑ ፍስሀው ላንዱ ሀዘኑ
- ያንዱ ቤት ሲቃጠል ላንዱ ቋያው ነው
- ያንዱ ቤት ሳይጠፋ ያንዱ ቤት አይለማ
- ያንዱ ቤት ካልጠፋ ያንዱ ቤት አይለማም
- ያንዱ ነገር ላንዱ የእንጀራ ልጁ ነው
- ያንዱ አገር መልከኛ ላንዱ አገር ገባር ነው
- ያንዱ ላም ወተት ያንድ እርሻ እሸት
- ያንድ ሚስቱን የሺ ከብቱን
- ያንድ ሰው ፍቅር ባንድ እጅ እንደማጨብጨብ ያለ ነው
- ያንድ ሰው ነገር ሰምተህ አትፍረድ
- ያንድ በሬ እሸት ያንድ ላም ወተት
- ያንድ እርሻ እሸት ያንድ ላም ወተት
- ያንድ ቀን ስህተት ለዘላለም እውቀት ነው
- ያንድ ቀን ስህተት የዘላለም ጸጸት ነው
- ያንድዋ እለት አንድዋ ባልቴት
- ያንጎርጓሪ ጉልበት የተራጋጭ ወተት
- ያኖሩት እንቅርት መለያ ይሆናል
- ያኖሩት እንቅርት ያገለግላል
- ያኩራፊ ምሳ እራት ይሆነዋል
- ያኩራፊ ምሳው የነበረ እራት ይሆነዋል
- ያኮረፈ ልብሱን አራገፈ
- ያኮረፈ ምሳው እራቱ ነው
- ያወረደ መአቱን ያመጣ ምህረቱን
- ያወቀ ተጠነቀቀ የዘነጋ ተነጠቀ
- ያወቀ ተጠነቀቀ የዘነጋ ተወጋ
- ያወቀ ተጠነቀቀ ያላወቀ ተነጠቀ
- ያወቀ ናቀ
- ያወቀ ዘለቀ ያላወቀ አለቀ
- ያወቁ ሲታጠቁ ያላወቁ ተሳቀቁ
- ያዋቂ ሴት ቤት አለው ውበት
- ያዋቂ አጥፊ የእስራኤል ጣፊ
- ያዋቂ አጥፊ የጾመኛ ገዳፊ
- ያዋጁን በጆሮ የእለቱን በቀጠሮ
- ያውሬ ስጋ ለወሬ
- ያውቃል ብሎ ያሟል ያምራል ብሎ ይሸልሟል
- ያውቃል ብሎ ይሾሟል ያምራል ብሎ ይሸልሟል
- ያው እንዳያችሁኝ ቅዳሜ የወጣሁ ይቆጡኛል ብዪ አርብ ማታ መጣሁ
- ያዙኝ ልቀቁኝ
- ያዛዥ ቤተ ክርስቲያን ሳሚ ያጋፋሪ ራስጌ ቋሚ
- ያየ ላውራ ቢል ያልሰማ አወራ
- ያየ ላውራ ቢል የሰማ አወራ
- ያየ ልናገር ቢል የሰማ ላውራ አለ
- ያየ ቢሄድ የሰማ ይመጣል
- ያየ ቢሄድ ያልሰማ ይመጣል
- ያየ ይናገራል የተወለደ ይወርሳል
- ያዩትን ሊሰሩ አይናቸውን ታወሩ
- ያዩትን ቢያጡ ያላዩትን ይቀላውጡ
- ያያን ጨንቋራ ሁሉ ያየዋል
- ያይጥ ምስክሯ ድንቢጥ
- ያይጥ ሞት የድመት ሰርግ
- ያይጥ እርዳታ በጭራንፎ ያልቃል
- ያይጥ ፉከራ ለመከራ ድመት ምን ሊበላ
- ያይጦች ዝላይ ለነአቶ ውሮ ሲሳይ
- ያደረገችውን ታስታውቅ ከደረቷ ትታጠቅ
- ያደፈ በእንዶድ የጎለደፈ በሞረድ
- ያደፈውን በእንዶድ የጎለደፈውን በሞረድ
- ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይለቅም
- ያዳቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይቀርም
- ያዳቆነ ሰይጣን የግል ኮሌጅ ከፈተ
- ያዛቆነ ሰይጣን ሳያቀስ አይቀርም
- ያዳኝ ውሻ ጠጉር ባፉ ብትር ትርፉ
- ያገሩን ሰርዶ ባገሩ በሬ
- ያገሩን ሰርዶ ያገሩ በሬ ይወጣዋል
- ያገር ልማት የገበሬ ሀብት
- ያገር ልጅ በምን ይመታል በኩበት ያም እንዳይሄድ ያም እንዳይሞት
- ያገር ልጅ በምን ይማታል በኩበት ያ እንዳይሄድ ያ እንዳይሞት
- ያገር ልጅ የማር እጅ
- ያገር ልጅ የማር ጠጅ
- ያገር እድር ለንጉስ ያስቸግር
- ያገር እድር ጦም ያሳድር
- ያገርህ ልጅ ብታገባት ሚስትህ ብትፈታት እህትህ
- ያገርህ ልጅ ብታገባት ሚስትህ ብትፈታት እትህ
- ያገርህ ዱር ፍራትን ያስወግዳል እንጂ ከሞት አያድንም
- ያገርን ሰርዶ ያገር በሬ ያወጣዋል
- ያገባሽስ ይፈታሻል ይብላኝ ለወለደሽ
- ያገባሽ ይፈታሻል ይብላኝ ለወለደሽ
- ያገባሽ ይፈታሻል ወዮለት ለወለደሽ
- ያገኘ ከራሱ ያጣ ከዋሱ
- ያጓኑት ድንጋይ ተመልሶ ራስን
- ያጓኑት ድንጋይ ተመልሶ ራስን ይመታል
- ያጣ ለማኝ ተሳድቦ ይሄዳል
- ያጣጣመ የቆረጠመ
- ያጣ ሰው ያገኝ አይመስለውም
- ያጥንት ፍላጭ የስጋ ቁራጭ
- ያፍ እማኝ አደረገኝ ለማኝ
- ያፌን እስክውጥ እድሜ ይስጠኝ ይላል እርኩም
- ያፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም
- ያፍ ዘመድ በመንገድ አይገድ
- ያፍላ ለማኝ አደረገኝ ለማኝ
- ያፍላ የለው ቀርፋፋ
- ያፍላ የለው ቀፋፋ
- ይሄ እንግዳ ቸኮለ ሊያድር ነው መሰለኝ
- ይህ ሁሉ ከርከሬሻ ባንቺ የተነሳ
- ይህ ሁሉ ጠባሳ ባንቺ የተነሳ
- ይህ አንበሳ ደም ደም አገሳ
- ይህ እንግዳ ቸኮለ ሊያድር ነው መሰለኝ
- ይህ ከርከሬሻ ዳቦዬን ለማንሻ
- ይህን ብሰጥ ምን እውጥ
- ይህን ብትሰጥ ምን ትውጥ
- ይህንን ፈርቼ ደጄን በቀን ዘግቼ
- ይህን ፈርቼ ደጄን በቀን ዘግቼ
- ይህች ባቄላ ካደረች አትቆረጠምም
- ይህች ተፍተፍ እኔን ለመመንተፍ
- ይሆናል ብዬ ጎሽ ጠመድኩ የማይሆን ቢሆን ፈትቼ ሰደድኩ
- ይሆን ቢሆን ዝሆን ይበላ ቢሆን
- ይሉሽን በሰማሽ ገበያም ባልወጣሽ
- ይሉሽን ባልሰማሽ ገበያም ባልወጣሽ
- ይሉሽን ባወቅሽ ገበያም ባልወጣሽ
- ይሉ አይሉ የት አለ ቅሉ
- ይሉሽን ብትሰሚ ጎንደር ላይ ክረሚ
- ይሉኝ አይል ውሽማ ዶሮ ሲጮህ ይማለላል
- ይሉኝ አይል የኋላውን አያይ
- ይሉኝ አይል ጸሀፊ ከሙሴ ይገድፋል
- ይሉኝታ ተፈርቶ እስከመቼ ተቆራምቶ
- ይሉኝታና መጠቀም ባንድነት አይገኙም
- ይሉኝታ የራስ አሊን ቤት ፈታ
- ይመሰክረዋል ለነፍሱ ይፈተፍተዋል ለከርሱ
- ይመስል አይመስል የጠይብ እጅ ተከሰል
- ይመታሉ የሚጠሉ ይመስል ይስማሉ የሚወዱ ይመስል
- ይሙት የገደለ ይካስ የበደለ
- ይማሩኝ እያልክ ከምትታማበት አትገኝ
- ይማሰላል ካሉ ይዛመዳል አይገድም
- ይሰጠኝ መስሎ ሊሸጠኝ
- ይሰጡኛል ብሎ ከሰጠ ቆጥቦ የበላ በለጠ
- ይስጡ ብሎ ከሰጠ ቆጥቦ የበላ በለጠ
- ይሰጣል መስሎ ይሸጣል
- ይስብረኝ ይሰንጥረኝ የሚሉ የሰውን ልብ ሊሰብሩ
- ይቅር ለእግዜር ወድቆ እማይሰበር
- ይቅር ለእግዜር ወድቆ አይሰበር ሞቶ አይቀበር
- ይቅደም ደግነት ይከተል ቸርነት
- ይበላ እንደ ቤቱ ይሰራ እንደ ጉልበቱ
- ይበላ እንደ ቤቱ ይሰራ እንደ ጎረቤቱ
- ይበላው ካጣ ይበላበት ያጣ
- ይበጃል ያሉት መድሀኒት አይን አጠፋ
- ይበጃል ያሉት ኩል አይን አጠፋ
- ይብላ እንደ ቤቱ ይስራ እንደ ጎረቤቱ
- ይብላኝ ለወለደሽ ያገባሽስ ይፈታሻል
- ይብራና ይብራ ተጣሉ በሰው ሽንብራ
- ይታደሏል እንጂ ይታገሏል
- ይታደሉታል እንጂ አይታገሉትም
- ይቺ ባቄላ ያደረች እንደሆን አትቆረጠምም
- ይቺ ጎንበስ ጎንበስ አንድም ለመፍሳት አንድም እቃ ለማንሳት
- ይቺን ለኛ ጥሬን ለጌኛ
- ይቺም ቂንጥር ሆና ቡታንታ አማራት
- ይቺን በላህ ብለህ ጦሜን አታሳድረኝ አለ አሉ
- ይውደደኝ የጀርባዪ ቅማል አለች አንዷ
- ይገርማል አህያ ከዥብ ይከርማል
- ይደንቃል ይገርማል አህያ ከዥብ ይከርማል
- ይኖሩዋል በደጋ ይተኙዋል በአልጋ
- ይወልደዋል ካሉ ይመሰለዋል አይገድም
- ይውጋሽ ብሎ ይማርሽ
- ይጥሉህ አትጥላቸው ይበድሉህ አትበድላቸው
- ይጠላኝ ይመስል ይመታኛል ይወደኝ ይመስል ይስመኛል
- ይወደዋል ካሉ ይመክሩዋል ይወልደዋል ካሉ ይመስሏል
- ይውጋህ ብሎ ይማርህ
- ይውጋህ ብሎ ይማርክህ
- ይገርመኛል ገንፎ ከራቴ ተርፎ
ደ
- ደሀ ሰው ዶሮ ካረደ ከሁለት አንዳቸው ቢታመሙ ነው
- ደህና ሲታጣ ይመለመላል ጎባጣ
- ደህና ወገን ያጣ ወየው ያለበት ጣጣ
- ደህና ጦር ያለው ለግምብ ይሞክረው
- ደመና ለዝናብ ድግስ ለሆዳም
- ደመና በሰማይ የጨዋ ልጅ በአደባባይ
- ደመናን የጨበጠ ሰማይን የቧጠጠ የለም
- ደመወዙ ስንዴ ስራው ምን ግዴ
- ደመወዝ ያጣ ሎሌ ይኮበልላል በሀምሌ
- ደም ቢያለቅሱ ድንጋይ ቢነክሱ
- ደም ተቀብቶ ዝንብ አይፈሩም
- ደም ተቃብቶ ዝንብ አይፈሩም
- ደም ተበክለህ ዝንብን አትጥላ
- ደም ከውሀ ይቀጥናል
- ደም ካልፈሰሰ ስርየት የለም
- ደሞዝተኛ አርፈህ ተኛ
- ደረስሁ ልጅ ፈላሁ ጠጅ
- ደረቅ ይቀመጠላል እርጥብ ይጎብጣል
- ደረቴን ቢያመኝ እግሬን አገመኝ
- ደረቴን ሲያመኝ እግሬን አገመኝ
- ደረጃ ለፍቶ መሄጃ
- ደስታና መከራ ቀኝና ግራ
- ደስታና መከራ ቀኝና ግራ ናቸው
- ደባ ራሱን ስለት ድጉሱን
- ደባ ራሱን ስለት ድጉሱን አያጣውም
- ደባል ሲስነብት ይሆናል ባለቤት
- ደባልና ሹመት ያለሰበብ አይሄድ
- ደብር ለላስታ ድግድግታ ለጌታ
- ደብተራ ሲኮራ እቤት ክርስቶያን ገብቶ ጭራ ይይዛል
- ደብተራ የዘኬ ጎተራ
- ደብተራ የዘኬ ጎተራ ዘኬውን ሲቋ ጥር አነቀው ነብር
- ደብተራና ተማሪ ሰናፊልና ሱሪ
- ደንቆሮ ከሚያጫውተኝ የሚሰማ ያውጋኝ
- ደንቆሮ የሰማ ለት ያብዳል
- ደወል ላንበሳ ባማረለት ታዲያ ማን ይሰርለት
- ደወል እንደ ጠዋቱ ትጮሀ ለች
- ደጃቸውን አይዘጉ ሰውን ሌባ ይላሉ
- ደጃቸውን ከፍተው ሰውን ሌባ ይላሉ
- ደጃፉን ጥሎ በጓሮ ይመጣል
- ደገኛ ሲያርስ ቆለኛ ያነፍስ
- ደጉ ነገር ሳያልቅ ክፉ መናገር
- ደግ ሰው ከንጀራው ቆርሶ ከወጡ አጥቅሶ
- ደግ ሳይበላ ክፉ ይመራ
- ደግ ጌታ ሲለግስ እንደ ፏፏቴ ያርስ
- ደግ ጎረቤት ውሻና ድመት ያሳድጋል
- ደግና ማለፊያ ትግልና ልፊያ
- ደግ አማችን መጦር ክፉ አማችን በጦር
- ደግ አባት እርስት ያቆማል ክፉ አባት እዳ ያቆያል
- ደግነት አይታረስ ልጅነት አይመለስ
- ደግ ጎረቤት እቃ አያስገዛም
- ደግ ጎረቤት ያወጣል ከመአት
- ደካማ ቀበሌ በአህያ ይወረራል
- ደፋር ሴት ጉልቻ ረግጣ ትወጣለች
- ደፋር ወጥ ያውቃል
- ደፋርና ጭስ መውጫ ቀዳዳ አያጣም
- ደፋርና ጭስ መውጫ አያጣም
- ደፋርና ጭስ ምን ያመጣሉ
- ደፋርና ጭስ ዝዋይ ገቡ
- ዱርዬ ያገባ በሬው በሰኔ ገደል የገባ
- ዱላ ለባለጌ ምርኩዝ ለአሮጌ
- ዱላ የሚጠላው ሸክላ ብቻ ነው
- ዱላን ይዞ ሌባን መጠየቅ
- ዱላ ይዞ ሌባን መጠየቅ
- ዱባ ባገሩ ጋን ያህላል አሉ
- ዱባና ቅል አበቃቀሉ ለየቅል
- ዱባና ቅል አበቃቀሉ አንድ ይመስላል አበላሉ ለየቅሉ
- ዱባና ቅል አብሮ ይበቅል አበላሉ ለየቅል
- ዱቄት ባመድ ይስቃል
- ዱጨት ባመድ ይስቃል
- ዲያቆን ሲጠግብ በጧፍ ይማታል ወይፈን ሲቦርቅ ድንበር ያፈርሳል
- ዲያቆን ከዘፈነ ፍየል ከቀዘነ
- ዲያቆን ከዘፈነ ፍየል ከቀዘነ መዳኛም የለው
- ዲያቢሎስ በክፋቱ ተወጋ ዳቢቱ
- ዳሩ ምን ይሆናል ሆነና ሆነና
- ዳር ሲፈታ መሀል ዳር ይሆናል
- ዳር ዳር ያለ በመሀል የከበረ
- ዳቦ ሲበሉ ልብ ልቡን ዳገት ሲወጡ ጥግ ጥጉን
- ዳቦ በገና ቡና በጀበና
- ዳቦ በወጥ በግዜር ማምለጥ
- ዳቦ ካልበሉት ድንጋይ ሎሚ ካልመጠጡት እንቧይ
- ዳቦ ያለ ቅርፊት ጠላ ያለ ምርጊት
- ዳቦውን ጎርሶ ደሙን አብሶ
- ዳተኛ በሬ ሀብታም ነው
- ዳኛ ለዳኛ ያወርሳል ጉም ተራራ ያለብሳል
- ዳኛ ምን ያደላ ከተረታ ሊበላ
- ዳኛ ምን ያደላ ከተረታው ሊበላ
- ዳኛ ሲመረምር ከራስ ይዞ እስከ እግር
- ዳኛ ሲቆጣ ማር ይዞ ከደጁ
- ዳኛ ሲያዳላ በዳኛ አህያ ሲያጋድል በመጫኛ
- ዳኛ ሳለ ተናገር ውሀ ሲጠራ ተሻገር
- ዳኛ ሲገኝ ተናገር ውሀ ሲጠራ ተሻገር
- ዳኛ ስበር በእጅ ክበር
- ዳኛ ቢንቁ የተያዘ እህልን ይወቁ
- ዳኛ ቢንቁ የተያዘ እህል ይወቁ
- ዳኛ ቢያዳላ በዳኛ አህያ ቢያጋድል በመጫኛ
- ዳኛ ቢያጋድል በዳኛ አህያ ቢያጋድል በመጫኛ
- ዳኛ አውጥቼ ዘንግ አቅንቼ
- ዳኛ አይነቀፍ እሳት አይታቀፍ
- ዳኛ ካዳላ ጭነት ቀላል
- ዳኛ የወል ምሰሶ የመካከል
- ዳኛ የወል ምሰሶ የማሃል
- ዳኛ የፈረደበት መርከብ የተሰበረበት
- ዳኛ የፈረደው ስለት የቀደደው
- ዳኛ ያደላበት እሳት የበላበት
- ዳኛ ያፈሰሱለት ፈረስ የከሰከሱለት
- ዳኛ ይመረምራል ጣዝማ ይሰረስራል
- ዳኛና በሬ ሀብታም ነው
- ዳኛ ፍርድ አይከላ እህል ጎታ ይሞላ
- ዳኛን ቢንቁ የተያዘ እህልን ይወቁ
- ዳኞች ከመረመሩ ይናገራል ምድሩ
- ዳኞች ከመረመሩ ይናገራል ምድሩ ይገናል ነገሩ
- ዳኞች ከመረመሩ ይገኛል ነገሩ
- ዳዊትን ያህል መዝሙር ጨለማን ያህል ጥቁር (የለም)
- ዳክዬን ከውሀው ፈረስን ከገለባው
- ዳኛ ሲገኝ ተናገር ውሀ ሲጠራ ተሻገር
- ዳገት ሲወጡ ጥግ ጥጉን ዳቦ ሲበሉ ልብ ልቡን
- ዳገት እርሙ ሜዳ ወንድሙ
- ድሀ ለወዳጁ አይሰንፍ ሀብታም ካለወዳጁ አይተርፍ
- ድሀ ሲቀልጥ አመድ አመድ ይሸታል
- ድሀ ሲቀመጥ እጁን ይዘህ አወዛውዘው
- ድሀ ሲቀማጠል ከወገቡ ቀምጠል
- ድሀ ሲቀማጠል ከወገቡ ቅምጥል
- ድሀ ሲቆጣ እግሩ ይፈናጠራል
- ድሀ ሲቆጣ እግሩ መንገድ ያሰልጣል
- ድሀ ሲቆጣ ከንፈሩ ያብጣል መንገዱን ያሰልጣል
- ድሀ ሲቆጣ መንገድ ያፈጥነዋል
- ድሀ ሲናገር ሬት ኮሶ ሀብታም ሲናገር የማር በሶ
- ድሀ ሲንቀባረር ያለቀሰ ይመስላል
- ድሀ ሲያገኝ ያጣ አይመስለውም
- ድሀ ቅቤ ወዶ ማን ሊሸከም ነዶ
- ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኑሮ እከክ ይወረው ነበር
- ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ እከክ ይጨርሰው ነበር
- ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ ኖሮ እከክ በወረሰው
- ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ እከክ ይጨርሰው ነበር
- ድሀ በህልሙ ቅቤ ባይጠጣ እከክ በፈጀው
- ድሀ በሽታ አያውቅም ሀብታም ጤና የለውም
- ድሀ ተበድሎ ማሩኝ ይላል ቶሎ
- ድሀ ውሃውን ጠጥቶ እሳቱን ይሞቃል ሀብታም ስለገንዘቡ ይጨነቃል
- ድሀና ድመት ሊሞት ሲል ያምርበታል
- ድሀና ገበያ ሳይገናኙ ይሞታል
- ድሀ በአመዱ ንጉስ በዘውዱ
- ድሀ በጉልበቱ ባለጸጋ በሀብቱ
- ድሀ ቢናገር አያደምቅ ቢጨብጥ አያጠብቅ
- ድሀ ባይ አይኔን አመመኝ
- ድሀ ተበድሎ ማሩኝ ይላል ቶሎ
- ድሀ ተበድሎ ራሱ ይታረቃል ሀብታም በድሎ ተመልሶ ይስቃል
- ድሀ ከንቡ ይዳላ
- ድሀ ከንቡ ይዳራ
- ድሀ ካለቀሰ ቀኑ መች አነሰ
- ድሀ ካልሰራ ዶሮ ካልጫረ
- ድሀ ካልጋረ ዶሮ ካልጫረ
- ድሀ ካልዘራ ዶሮ ካልጫረ
- ድሀ ካልዘራ ዶሮ ካልጫረ (ማን ያበላው ነበረ)
- ድሀ ከርሻ ዳቦዬን ለማንሻ
- ድሀ የሚበላው እንጂ የሚከፍለው አያጣም
- ድሀ በጉልበቱ ባለጸጋ በሀ ብቱ
- ድሀ በጉልበቱ ባለጸጋ በከብቱ
- ድሀ ያልፍልኛል ይላል ጌታ ቀኑን ይቆጥራል
- ድሀ ያመልክት ዳኛ ያሟግት
- ድሀና ሹም ተሟግቶ ድንጋይና ቅል ተማትቶ የማይሆን ነው ከቶ
- ድሀና ጌታ ተሟግቶ ድንጋይና ቅል ተማትቶ የማይሆን ነው ከቶ
- ድሀ ምን ትሰራለህ እንጂ ምን ትበላለህ የሚለው የለም
- ድሀ ሲያስለቅሱ ከስላሴ ይወቀሱ መንግስተ ሰማያትን አይወርሱ
- ድሀ ቢያስለቅሱ ከስላሴ ይወቀሱ መንግስተ ሰማያትን አይወርሱ
- ድሀን ካስለቀሱ በስላሴ ዘንድ ይወቀሱ
- ድሀን ፈርቼ ደጄን በቀን ዘግቼ
- ድህነት ከአምላክ መስማማት
- ድህነት ከአምላክ መስተካከል
- ድል በመታደል ሙያ በመጋደል
- ድል የባለ እድል
- ድል እድል በአንድ ድልድል
- ድል ድል እድልህ እንዳይጎድል
- ድመት ላመሏ ዛፍ ላይ ትወጣለች
- ድመት መንኩሳ መናከሷን አትረሳ
- ድመት መንኩሳ አመሏን አትረሳ
- ድመት በታች ከሆነች ውሻ ታሸንፋለች
- ድመትና ቁንጫ ባዶ ቤት ይወዳል
- ድመትና አይጥ እሳትና ጭድ
- ድመትን በቆሎ መጠርጠር
- ድመትን አይጥ ገደለቻት ወይ ጥቃት ወይ ጥቃት
- ድመት ውስጥ ውስጡን አውሬ ናት
- ድምቢጥ እንደ አቅሟ በብር ትታገማለች
- ድምቢጥ እንደ አቅሟ በብእር ትታገማለች
- ድምጽና ቁንጫ ባዶ ቤት ይወዳል
- ድሪቶ ከነቅማሉ መጥፎ ሰው ከነአመሉ ወዲያ በሉ
- ድሪያ የዝሙት ዋዜማ
- ድር ቢያብር አንበሳ ያስር
- ድርብርብ እንደ ደጋ ንብ
- ድርና ማግ ለሀጭና ልጋግ
- ድር ቢያብር ጋቢ ይሰራል
- ድር ቢያብር አንበሳ ያስር
- ድርጎ ራቱ ድርጎ ቢቀር ሞቱ
- ድርጎ የለመደች መበለት ወተት ያየች ድመት
- ድርጭት ፈንጠር ምዝግዝግ ጎንደር
- ድሮም እንዳይሆን ነው የቄስ ልጅ መኮነን (አለ)
- ድሮም እንዳይሆን ነው የቄስ ልጅ መኮንን (አለ)
- ድሮ ካያታችን ካጤ ነው ትውልዳችን
- ድሮም ሌባ ሲሰርቅ እንጂ ሲካፈል አይስማማም
- ድስት ግጣሙን አያጣም
- ድበላ አንዳንድ ጊዜ ይበላ
- ድንቢጥ እንደ አቅሟ በብእ ር ትታገም
- ድንቀኛ ተኳሽ ድር ይበጥሳል
- ድንቁርና ከልብህ መካከል ተራራ ያህል
- ድንኳን ያየ ባለጌ
- ድንኳን ገልጦ ዙፋንን ረግጦ
- ድንኳን ገልጦ ዙፋን ረግጦ
- ድንኳን ገልጦ ዙፋን አጊጦ
- ድንገተኛ ስህተት የቁልቁለት ውድቀት
- ድንጋይ ለረገጠ ፍለጋ የለውም ውሀ ለጠጣ ሽታ የለውም
- ድንጋይ ላይ ተቀማጭ የባለጌ ተለጣጭ
- ድንጋይ በድንጋይ ላይ ትልቅ ቤት ይሆናል
- ድንጋይ ቢያጎኗት ተመልሳ ካናት
- ድንጋይ ወርዶ እዘብጥ ያርፋል ያገኘው ይተርፋል
- ድንጋይ ሲያረጅ መጭ ያበቅላል
- ድንጋይ ወደ ሰማይ ቢወርወር ተመልሶ ምድር
- ድንጋይ ወደ ሰማይ ቢወርወር ተመልሶ ወደ ምድር
- ድግርና ገባር ሲተካከል ያምር
- ድግስ የሌለው ዋዜማ ምልክት የሌለው ዜማ
- ድጥ ማንሸራተቱን ባለጌ ማሽሟጠጡን አይተውም
- ዶማ ለመማሻ ማረሻ ለመፈለሻ
- ዶሮ ላትበላው ታፈስ
- ዶሮ ልጆቹዋን ይዛ ጓሮ ለጓሮ
- ዶሮ ባሏ ሲሞት ሞተች እጢስ ገብታ
- ዶሮ ሲሉ ሰምታ ሞተች እጢስ ገብታ
- ዶሮ ሲቀጣጥቧት በመጫኛ ጣሏት
- ዶሮ ሲደልሏት በመጫኛ ጣሏት
- ዶሮ በልቶ ብስና ጎመን በልቶ ጤና
- ዶሮ በልቶ ከብስና ጎመን በልቶ በጤና
- ዶሮ በልጅዋ አንጀት ትጫወታለች
- ዶሮ በማሰሮ ገደል ለዝንጀሮ
- ዶሮ በጋን
- ዶሮ ቢጠፋ ከቤቱ መነኮሰች እናቱ
- ዶሮ ቢጠፋ ካባቱ መነኮሰች እናቱ
- ዶሮ ቢያማት በሬ ተሳሉላት
- ዶሮ ብታልም ጥሬዋን
- ዶሮ ብትታመም በግ አረዱላት
- ዶሮና ቀበሮ ተገናኝተው ጓሮ
- ዶሮና ቀበሮ ተገናኝቶ ጓሮ
- ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጠልፈው ጣሏት
- ዶሮን ሲያታልሏት በመጫኛ ጣሏት
- ዶሮን ሲያታልሏት አንቺ እሩጭ እኛ እንከተልሽ አሏት
- ዶሮን ሲያታልሏት ጥምር መንግስት አሏት
- ዶሮን ሲያታልሏት ፎቶ አነሷት
- ዶሮ አንዱን እንቁላል በወለደችበት ወታቦ ትሞላለች
- ዶሮ እቤት ውላ ዝናብ ትመታለች
- ዶሮ እኔ ባልበላው ጭሬ አላፈሰውም ወይ አለች
- ዶሮ እኔ ባልበላ ጭሬ አላፈስም ወይ አለች
- ዶሮ ከቆጥ በሬ ከጋጥ
- ዶሮ ከቤት ሆና ዝናም ይመታታል
- ዶሮ ከቤት ውላ ዝናብ ይመታታል
- ዶሮ ከጋጥ አህያ ከቆጥ
- ዶሮ ከጋጥ በሬ ከቆጥ
- ዶሮ ከጮኸ ሌሊት የለም ከደብረ ታቦር ወዲያ ክረምት የለም
- ዶሮ ከጮኸ ሌሊት ከደብረ ታቦር ወዲያ ክረምት የለም
- ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት ከቡሄ ወዲያ የለም ክረምት
- ዶሮ ካልበሏት አሞራ ናት
- ዶሮ ጭራ ማረጃዋን አወጣች
- ዶሮ ጭራ መታረጃዋን አወጣች
- ዶሮ ጭራ የምታወጣው ምስጢር
- ዶሮ ጭራ ጭራ አወጣች ማረጃዋን ካራ
- ዶክተር ሲበዛ በሽተኛ ይሞታል
ጀ
- ጀማሪ ይጥፋ ሰካራም ይትፋ
- ጀምሮ የማይፈጽም ፈጭቶ የማያልም
- ጀምሮ ይጨርሳል ለጉሞ ይተኩሳል
- ጀምሮ ይጨርሳል አልሞ ይተኩሳል
- ጀምበር ሳለ እሩጥ አባት ሳለ አጊጥ
- ጀርባ ለባለቤቱ ባእድ ነው
- ጀርባዬን አሳከከኝ ተንጠራርቼ ማከክ ተሳነኝ
- ጀርባዬን እከከኝ ለኔ ራቀኝ
- ጀርባዬን እከክልኝ ለኔ ራቀኝ
- ጀግና የሚታወሰው ወይም ከሞተ ወይም ከተለየ በኋላ ነው
- ጀግናን ከደረቱ አበባን ከአናቱ
- ጃርት ያስደነገጠው ዱባ ይመስላል
- ጅል ስለላ ላይ ሄዶ ምግብ ቢቀርብለት ስለላ ላይ ነኝ ብሎ .እርፍ
- ጅምርን ለነገ አያሳዩም
- ጅምር ይጨረሳል ልጉም ይተኩሳል
- ጅራትና ሀሜት በሰተኋላ ነው
- ጅራትና ጉድ በስተኋላ ነው
- ጅራትና ጉድ ከወደኋላ ብቅ ይላል
- ጅራቷ ታደርሰኝ ካናቷ
- ጅራቷ ታደርሳለች ከናቷ
- ጅራፍ መትቶ ያለቅሳል ባለጸጋ በድሎ ተመልሶ ይወቅሳል
- ጅራፍ እራሱ ገርፎ እራሱ ይጮሃል
- ጅራፍ እሱው ይገርፍ እሱው ይለፍ
- ጅራፍ እሱው ይገርፍ እርሱው ይለፈልፍ
- ጅብ ምን ይመስላል እግሩ ያነክሳል አፉ ይነክሳል
- ጅብ ሲበላህ በልተሀው ተቀደስ
- ጅብ ባጥንት የተገደገደ በጅማት የተማገረ ቤት አለ ቢሉት ወዴት ነው ሳይል ገደል ገብቶ ሞተ
- ጅብን ለመግደል ከአህያ ተጠለል
- ጅብን ሲወጉ በአህያ ይጠጉ
- ጅብ ከላይ ውሀ ሲጠጣ ከታች ያለችውን አህያ አታደፍርሽብኝ አለ
- ጅብ ከማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ ይላል
- ጅብ ኪበላህ ጅብ በልተህ ተቀደስ
- ጅብ አጥንት ባየበት ይመላለሳል
- ጅብ አያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ
- ጅብ እማያቁት አገር ሄዶ ሩም ሰርቪስ ያዛል
- ጅብ እማያቁት አገር ሄዶ ቴሌ ሴንተር ከፈተ
- ጅብ እሰር ብሎ ተሰሮ ገባ
- ጅብ እስኪነክስ ያነክስ
- ጅብ እንኳን ጓደኛውን ይጣራል
- ጅብ እንኳን ጓደኛውን ይጠራል
- ጅብ እንደቁመቱ ልብ የለውም
- ጅብ እንዳባቱ ይዘርጥጥ
- ጅብ እንዳባቱ ይዘርጥጥ አህያ እንደአባቱ ይፈርጥጥ
- ጅብ እንዳገሩ ይጮሀል
- ጅብ እንዳገሩ ይጮሀል የደላው ሙቅ ያኝካል
- ጅብ እንደጉልበቱ ልብ የለውም
- ጅብ ታኮተኮተ ሰው ከተከተተ
- ጅብ ከሚበላህ በልተህ ተቀደስ
- ጅብ ካኮተኮተ ሰው ከተከተተ
- ጅብ ውሀ ሲጠጣ ታች ያለችውን አህያ አታደፍርሽብኝ አለ
- ጅብ የማያውቁት አገር ሄዶ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ
- ጅብ የኔ ነው ስለው ወናፌን ቀማኝ
- ጅብ ጥጆቹን ጠብቅ ሲባል ይጠፉብኛል አለ
- ጅብና ሸማኔ ከጉድጓድ አይወጡም
- ጅብና እህል ሳይተዋወቁ ይኖራሉ
- ጅብን ሊወጉ ካህያ ይጠጉ
- ጅብን ሲወጉ ባህያ ይጠጉ
- ጅብን ከምን መታኸው ከአፉ አሰፋሁለት
- ጅብን ፈርቼ ከዛፍ ብወጣ ነብር ቆየኝ
- ጆሮህ የት ነው ቢሉት እዚህ አለ አሉ
- ጆሮ ለባለቤቱ ተቃዋሚ ሆነ
- ጆሮ ምነው አታድግ ቢሉት ጉድ እየሰማሁ በየት ልደግ አለ
- ጆሮ ለባለቤቱ ባዳ ነው
- ጆሮ በላ ሆድ ጦሙን አደረ
- ጆሮ ባይጦም ይመስላል ሆዳም
- ጆር አይጦምም አይን አይጠግብም
- ጆሮ እዳውን አይሰማም
- ጆሮ ካያት ያረጃል
- ጆሮ ካያቱ ያረጃል
- ጆሮ የሰማውን ለማየት ይሄዳል አይን
- ጆሮ የሰማውን ለማየት አይን ይንከራተት
- ጆሮ የሰማውን ልብ ያውቀዋል
- ጆሮ የሰማውን ልብ ያውቃል
- ጆሮ የቀድሞዎቹ እኩያ ነው
- ጆሮውን ቢቆርጡት መስሚያው ይቀራል
- ጆሮ ያለው ይስማ የሰማ ያሰማ
- ጆንያን ያቆመው እህል ነው
ገ
ጠ
- ጠላትህን ውሀ ሲወስደው እንትፍ ብለህ ጨምርበት
- ጠርጥር በገንፎ ውስጥ እንዳለ ስንጥር
- ጠበንጃ ራሱ መቶ ራሱ ይጮሀል
- ጠንቋይ ለራሱ አያቅም
- ጡጥም ከፈስ ተቆጠረች
- ጤፍ ከአቅሙ እንክርዳድ ከፈለ
- ጤፍ ከዘመዷ ጎታ ትሞላ
- ጥልቅ ብዬን ውሀ ወሰዳት
- ጥርሴስ ልማዱ ነው አይኔን አታስቀው
- ጥርስና ከንፈር ሲደጋገፍ ያምር
- ጥርስ የሌላት ጥርስ ያላትን ነክሳ አነካከስ ታስተምራለች
- ጥቂት ያለው ሁሉ ብርቁ ነው
- ጥንቸል ጥላው ጠላት ይመስለዋ
- ጥንቸልም ለሆዷ ዝሆንም ለሆዱ አብረው ውሀ ወረዱ
- ጥይትና ማጣትን ተኝቶ ማሳለፍ ነው
- ጥጃ ቢፈነጭ በሜዳ ውሀ ቢሄድ በጎድጓዳ
- ጥጃ ቢፈነጭ በሜዳ ውሀ ቢሮጥ በጎድጓዳ
- ጥጋበኛ ከርከሮ የነፍጠኛ ጎጆ ይታከካል
- ጥጋበኛንና ውሀ ሙላትን ቁመህ አሳልፈው
- ጦር ሲመጣ ዛቢያ ቆረጣ
- ጦጣ መጀመሪያ የመቀመጫዬን አለች አሉ
- ጦጣ ባለቤቱን ታስወጣ
ጨ
ጸ
- ጸሀይ ሳለ ሩጥ አባት ሳለ አጊጥ
- ጸሀይ ብልጭ ወፍ ጭጭ ሲል
- ጸሀይ ካልወጣ ከሰፈረበት አይነሳ አንበጣ ሴት ምክንያት አታጣ
- ጸሀይ የጠዋት አዱኛ የሽበት
- ጸሀይ ያየውን ሰው ሳያየው አይቀርም
- ጸሀይና ንጉስ ሳለ ሁሉም አለ
- ጸሎት በጽሞና ነገር በደመና
- ጸሎት በፍቅር ሀይማኖት በምግባር
- ጸሎት ከፍቅር ሀይማኖት ከምግባር ይበጃል
- ጸሎት ከፍቅር ሀይማኖት ከግብር
- ጸሎት ያለፍቅር ሀይማኖት ያለግብር አይረባም
- ጸጸት እያደር ይመሰረት
- ጻድቃን ሳይቀጣጠሩ ይገናኛሉ
- ጻድቃን ሳይቀጣጠሩ ይገናኛሉ ሀጥአን ግን በተቃጠሩበት ይተጣጣሉ
- ጽዋ በተርታ ስጋ በገበታ
- ጽድቁ ቀርቶብኝ በቅጡ በኮነነኝ
- ጽድቁ ቀርቶብኝ በውሉ በኮነነኝ
- ጽድቅ ለመንኳሽ ቀኝ ለከሳሽ
- ጽድቅ እንደ ላሊበላ እድሜ እንደ ማቱሳላ ይስጥህ
- ጽህፈት በብራና ዘፈን በበገና
- ጾማ ጾማ ለጸሎተ ሀሙስ እርጎ ትልስ
- ጾም ገዳፊና ሰው ጠባቂ ለጥቂት ይሳሳታል
ፈ
- ፈላ ገነፈለ ተሞላ ጎደለ
- ፈረሰኛ ሲሮጥ እግረኛን ምን አቆመው
- ፈረሰኛ ሲሸሽ እግረኛን ምን አመጣው
- ፈረሰኛ የወሰደውን እግረኛ አይመልሰውም
- ፈረሱም ይኸው ሜዳውም ይኸው
- ፈረስ ሲያጠብቅ ልጓም አይለቀቅ
- ፈረስ በራሪ በቅሎ ሰጋሪ
- ፈረስ ቢያነክስ አህያ ታጉዝ
- ፈረስ ቢጠፋው ኮርቻውን ገልቦ አየ
- ፈረስ አውቃለሁ ስገታ እወድቃለሁ
- ፈረስና ገብስ ያጣላል
- ፈረስ ያደርሳል እንጂ አይዋጋም
- ፈረስ ጥሎ ይደነግጣል በቅሎ ጥሎ ይረግጣል
- ፈረስ ጥሎ ይደነግጣል አህያ ጥሎ ይረግጣል
- ፈረንጆች እንደመርፌ ይገቡ እንደዋርካ ይሰፉ
- ፈሩ ፈሩ ማጀት አሩ
- ፈሩ ፈሩ ማጀት አደሩ
- ፈሪ ለናቱ
- ፈሪ ለናቱ ይገባል
- ፈሪ ለናቱ ጀግና ለጀግንነቱ
- ፈሪ በገዛ ጠቡ ገላጋይ ይሆናል
- ፈሪ ቢሸፍት እስከ ጓሮ
- ፈሪ እንዳይሉኝ አንድ ገደልሁ ጀግናም እንዳይሉኝ አልደገምሁ
- ፈሪ ከውሀ ውስጥ ያልበዋል
- ፈሪ ካልጋ ላይ ይወድቃል
- ፈሪ ካልጋ ላይ ወድቆ ይሞታል
- ፈሪን ውሀ ውስጥ ያልበዋል
- ፈሪ ውሀ ውስጥ ሆኖ ያልበዋል
- ፈሪ ውሀ ውስጥ ያልበዋል
- ፈሪ የሚያባርረው ሳይኖር ይሸሻል
- ፈሪ የናቱ ልጅ ነው
- ፈሪ ፈራና እጉድባ ቢኛ ጆሮውን በላው ያይጥ ቀበኛ
- ፈሪ ፈራና እጉድባ ቢተኛ ጆሮውን በላው ያይጥ ቀበኛ
- ፈርተው ድንጋይ ሲጥሉ ጅብ ወጣ ከዱሩ
- ፈርተው ድንጋይ ቢጥሉ ጅብ ወጣ ከዱሩ
- ፈርተው ድንጋይ ቢወረውሩ ጅብ ወጣ ከዱሩ
- ፈሷን ፈስታ ቂጧን ጨበጠች
- ፈስ በወረንጦ እየተለቀመ ነው
- ፈስቶ ቂጥን መያዝ
- ፈስ ያለበት ቂጥ ዝላይ አይችልም
- ፈስ ያለበት ዝላይ አይችልም
- ፈትል ሲረዳዳ አንበሳ ያስራል
- ፈትል ሲረዳዳ አንበሳ ያስቀራል
- ፈክሮ መሽሽ ታሪክ ያበላሻል
- ፈዛዛ እያንቀላፋ ይገባል ፈፋ
- ፈጅቶ ከሚያጠግበኝ እስቲበርድ ይራበኝ
- ፈጅቶ ከሚያጠግበኝ እስኪበርድ ይራበኝ
- ፈገግታ የልብ አለኝታ
- ፈጣሪን የሚያህል ጌታ ርስትን ያህል ቦታ
- ፈጣሪን የሚያህል ጌታ ገነትን ያህል ቦታ
- ፈጥነው የገመዱት ፈጥኖ ይበጠሳል
- ፈጥኖ መስጠት ኋላ ለመጸጸት
- ፈጥኖ መስጠት ቶሎ ለመጸጸት
- ፈጥኖ መስጠት በኋላ መጸጸት
- ፈጭታ የነበረች ላመልማሎ ኮራች
- ፊት ያሞጠሙጧል ኋላ ያፏጩዋል
- ፍሪክና ጻድቅ አይቀጣጠርም
- ፍሬ በመስጠቱ ባልታወቀ ሾላ የወፎች ዝማሬ ቀደመ አሉ
- ፍቅር ሲጠና ቆሎ ያጓርሳል
- ፍቅርና ጉርሻ ካላስጨነቀ አያምርም
- ፍቅር ካለ ዘጠኝ ቂጣ ለባልና ሚስት ይበቃል
- ፍቅር ፍቅር ሲሉ ደሀ ሆነው ቀሩ
- ፍየል ሁለት ወልዳ አንዱ ለመጽሀፍ አንዱ ለወናፍ
- ፍየል ላምስት ዶሮ ለባልና ለሚስት
- ፍየል መንታ ወልዳ አንዱ ለመጽሀፍ አንዱ ለወናፍ
- ፍየል መንታ ትወልድና አንዱ ለወናፍ አንዱ ለመጽሀፍ
- ፍየል ሲሰባ ሾተል ይልሳል
- ፍየል በልታ በበግ አበሰች
- ፍየል በልታ በበግ አሳበበች
- ፍየል ሲቀናጣ እናቱን ይሰራል
- ፍዬል በግርግር እናቱን ይሰራል
- ፍዬል በግርግር እናቱን ይሰር
- ፍየል ከመድረሷ ቅጠል መበጠሷ
- ፍየል ከቀዘነ ዲያቆን ከዘፈነ
- ፍየል የለኝ ከነብር ምን አጣላኝ
- ፍየልና ቀበሮ ምጥማጥና ዶሮ
- ፍየሏን እንደበግ
- ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ
- ፍዳ ለሀጥአን እሴት ለጻድቃን
- ፍጥም አያናግር የጎርፍ ሙላት አያሻግር
- ፍጥም አፍራሽ ቤተክርስቲያን ተኳሽ
- ፍጥም ያቆማል እርቅ ይጠቀልላል
- ፍጥም ያዋውላል አቧራ ያስላል
- ፎክሮ መሸሽ ታሪክ ያበላሽ

Post a Comment